Discover millions of ebooks, audiobooks, and so much more with a free trial

Only $11.99/month after trial. Cancel anytime.

ቅባቱን ያዝ
ቅባቱን ያዝ
ቅባቱን ያዝ
Ebook96 pages44 minutes

ቅባቱን ያዝ

Rating: 5 out of 5 stars

5/5

()

Read preview

About this ebook

ቅባት ወደ ተሳካ እና ፍፃሜው ያማረ አገልግሎት ውስጥ ለመግባት የሚያስፈልግ ዋነኛ ቁልፍ ነው፡፡ ብዙ ሰዎች በፍጹም ቅንነት በራሳቸው ጥረት የእግዚአብሔርን ሥራ ለመሥራት ሞክረው መንገድ ቀርተዋል፡፡ እነኚህ ሰዎች ያልተገነዘቡት ነገር “በመንፈሴ (በቅባት) እንጂ በኃይልና በብርታት አይደለም” (ዘካሪያስ 4፡6) የሚለውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ መርህ ነው፡፡ “ይህ ቅባቱን ያዝ” በሚል ርዕስ በቢሾፕ ዳግ ሂዋርድ-ሚልስ የተጻፈ ልዩ መጽሐፍ ቅባቱን መያዝ ማለት ምን ማለት እንደሆነ እና እንዴት ተደርጐ እንደሚያዝም ተግባራዊ በሆነ መልኩ ያስተምራል ! የዚህን መጽሐፍ ገጾች ስታነብ በውስጥህ ቅባቱን የመያዝ መሻትህ ይቀጣጠል !

Languageአማርኛ
Release dateJul 27, 2016
ISBN9781613954294
ቅባቱን ያዝ
Author

Dag Heward-Mills

Bishop Dag Heward-Mills is a medical doctor by profession and the founder of the United Denominations Originating from the Lighthouse Group of Churches (UD-OLGC). The UD-OLGC comprises over three thousand churches pastored by seasoned ministers, groomed and trained in-house. Bishop Dag Heward-Mills oversees this charismatic group of denominations, which operates in over 90 different countries in Africa, Asia, Europe, the Caribbean, Australia, and North and South America. With a ministry spanning over thirty years, Dag Heward-Mills has authored several books with bestsellers including ‘The Art of Leadership’, ‘Loyalty and Disloyalty’, and ‘The Mega Church’. He is considered to be the largest publishing author in Africa, having had his books translated into over 52 languages with more than 40 million copies in print.

Related to ቅባቱን ያዝ

Related ebooks

Reviews for ቅባቱን ያዝ

Rating: 5 out of 5 stars
5/5

1 rating0 reviews

What did you think?

Tap to rate

Review must be at least 10 words

    Book preview

    ቅባቱን ያዝ - Dag Heward-Mills

    መቀባትህ የግድ ነው

    ለአገልግሎት የሚያበቃኝ ምንም ዓይነት መሰረታዊ ስልጠናም ሆነ የመፅሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤት እውቀት ወይም ደግሞ አሉ ከሚባሉ የእግዚአብሔር ሰዎች ጋር የጠበቀና እዚህ ግባ የሚባል ግንኙነት ያለው ሰው አልነበርሁም። ለአገልግሎት ከወጣሁ በኋላ የተገናኘኋቸው አንዳንድ የእግዚአብሔር ሰዎችም ቢሆኑ ጌታ በሕይወቴ ላይ የነበረውን ጥሪ ከመጠራጠርም አልፈው ተዋጉኝ። ስለዚህም አንድ የነበረኝ ብቸኛ ምርጫ በሌሎች ማለትም እኔ ካለሁበት በጣም ርቀው በሚገኙ የጌታ አገልጋዮች የተዘጋጁ መጽሐፍቶችንና ካሴቶችን በመከታተል የእነርሱን ቅባት መካፈል ብቻ ነበር።

    እግዚአብሔር በሰጠኝ የአገልግሎት ስፍራዬ ጸንቼ እንድቆም የሚያደርገኝ የመንፈስ ቅዱስ ቅባት በላዬ ላይ እንዳለ ሙሉ የሆነ እምነት ነበረኝ። በሕይወቴ ላይ ያለውን የመንፈስ ቅዱስ ቅባት እንዳልጠራጠር የሚያደርጉኝ ከበቂ በላይ የሆኑ ብዙ መረጃዎች በዙሪያዬ ነበሩ። ቢሆንም ከዚህ በተጨማሪም ዘመናዊው የኤሌክትሮኒክስና የቴክኖሎጂ እድገት ለእግዚአብሔር መንግሥት መስፋፋት ጥቅምና ለአገልግሎት መዳበር ጠቃሚ እንደሆነ በሚገባ የማምን ሰው ነኝ። የቴክኖሎጂ እድገት እና ስልጣኔ የተቀቡ የጌታ ሰዎችን በቅርብ እንድናገኝ አስችሎልና።

    የሚያስፈልግው መቀባት ነው

    እግዚአብሔር ቀብቶ ያስነሳውን አገልጋዩን ወደ አንተ ሲልክ፣ በእርሱ ያለውን ቅባቱን ትካፈል እና ትይዝ ዘንድ ለአንተም እድል እየሰጠህ ነው። ቅባት የእግዚአብሔርን ሥራ ለምንሠራ እንደ እኔና እንደ አንተ ላለን ሰዎች የሚያስፈልገን ዋነኛ ነገር ነው። ነቢዩ ዘካርያስ እጅግ በጣም አስፈላጊው ነገር ቅባት እንደሆነ በደንብ የገባው ሰው ነበር። ለዚህም ነው እንዲህ ያለው፣ . . . በመንፈሴ እንጂ በኃይልና በብርታት አይደለም፥ . . (ዘካርያስ 4፡6)

    ኤልሳዕ የኤልያስ አገልገሎት የተሳካ የሆነበት ዋናው ምክንያት ቅባት እንደሆነ በሚገባ ተገነዘበ። አጋጣሚው በተመቻቸለት ጊዜም የጠየቀው አንድ ነገር ቢኖር ይህንኑ ቅባት ብቻ ነበር። ሌሎች ሰዎች የኤልያስን የገንዘብ አቅም፣ የትምህርት ደረጃ ወይም ደግሞ ሙያ ሊጠይቁ ይችሉ ይሆናል። የኤልሳዕ መሻት ግን አንድና አንድ ብቻ ነበር እርሱም ቅባት!

    ከተሻገሩም በኋላ ኤልያስ ኤልሳዕን፦ ከአንተ ሳልወሰድ አደርግልህ ዘንድ የምትሻውን ለምን አለው፤ ኤልሳዕም፡- መንፈስህ በእኔ ላይ ሁለት እጥፍ ይሆን ዘንድ እለምንሃለሁ አለ።

    2ኛ ነገሥት 2፡9

    በዚህ መጽሐፍ ውስጥ፣ ብዙውን ጊዜ ስለማይነገር የቅባት መተላለፊያ መንገድ ላካፍልህ እወዳለሁ። ምን አልባት ለአንተ አዲስ ነገር ሊሆንብህ ይችል ይሆናል፣ ይሁን እንጂ ይህ ጉዳይ ትልቅ እውነታ ነው። ቅባቱን ለመጨበጥ፣ የሚያስችልህ እስከሆነ ድረስ የትኛውንም መንገድ ቢሆን ተጠቀምበት! ይህንን ስል ግን እግዚአብሔር የሚቀባው በዚህ መንገድ ብቻ ነው ማለቴ አይደለም። እያደረግሁ ያለሁት ከጌታ የተቀበልሁትን ለአንተ ደግሞ ማካፈል ነው። የማካፍልህ እውነት ትክክለኛና መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረት ያለው ነው።

    ብዙ ሰዎች መንፈሳዊ መልእክቶችን በካሴት በመስማት እና መጽሐፍ በማንበብ ተቀብተዋል፤ ይሁን እንጂ በወቅቱ ምን እየተካሔደ እንደነበር ላይገባቸው ይችላል። እነዚህ ቅባቱን በዚህ ማስተላለፊያ መንገድ የተቀበሉ ሰዎች ያንኑ ቅባት መልሰው ማስተማር አይሆንላቸውም። የዚህ ዋና ምክንያቱም ሙሉ ለሙሉ አልገባቸውምና ነው። እኔ ግን ለአገልግሎት መሰረታዊ ግብአት የሆነውን ቅባት ለመያዝ ቀላልና እውነተኛ የሆነ ዘዴ የማስተማር ኃላፊነት እንዳለብኝ አምናለሁ።

    ምዕራፍ 2

    ከታላላቅ የእግዚአብሔር ሰዎች ጋር መተባበር

    በሌላ አንድ መጽሐፌ፣ ከእግዚአብሔር ሰው ጋር መቀራረብና ኅብረት ማድረግ በሕይወቱ ላይ ካለው ቅባት ለመቀበል ያለውን ጠቀሜታ አካፍያለሁ። ከተቀቡ የእግዚአብሔር ሰዎች ጋር ኅብረት ማድረግ ለምን አስፈለገ? ከዚህ ኅብረት በትክክል የምታተርፈውስ ምንድር ነው? በመጀመሪያ ከእግዚአብሔር ሰው ጋር የጠበቀ ኅብረት ስታደርግ ያ ሰው በተደጋጋሚ የሚያደርገውን ንግግር ትሰማለህ። ያ የተቀባ ሰው የሚናገራቸው ቃላቶች ደግሞ በውስጣቸው ቅባትን ይዘዋል። ኤልሳዕ ከኤልያስ ጋር የቀረበ ግንኙነት ስለነበረው የሚናገረውን በተደጋጋሚ ይሰማው ነበር።

    ሲሄዱም፣ እያዘገሙም ሲጫወቱ፥ . . .

    2ኛ ነገሥት 2፣11

    ቃላት ኃይል አላቸው!

    ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ ከአፉ የሚወጡት ቃላቶች ሁለት እጅግ ጠቃሚ ነገሮችን በውስጣቸው እንደያዙ ነገራቸው። እነዚህም ሁለት ነገሮች ሕይወት እና መንፈስ ናቸው! ይህ መንፈስ ማለት ምን ማለት ነው? መንፈስ ቅባቱ ነው! መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስና በኃይል ቀባው ይላል (ሐዋሪያት ሥራ 10፡38)። ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ተቀባ፣ እንግዲህ ይህ መንፈስ ቅዱስ ቅባቱ ነው ማለት ነው።

    . . . እኔ የነገርኋችሁ ቃል መንፈስ ነው ሕይወትም ነው።

    ዮሐንስ 6፤63

    ብዙ ሰዎች በተለያየ ምክንያት ከመንፈሳዊ መጽሐፍት እና ካሴቶች አማኻኝነት ካልሆነ በቀር በቀጥታ ከእግዚአብሔር ሰው ጋር የቀረበ ግንኙነት ማድረግ አይችሉም። መንፈሳዊ መጽሐፍቶችና ካሴቶች የተቀቡ የእግዚአብሔር ሰዎችን ቃል በውስጣቸው ይዘዋል። እነዚህ ቃላቶች ደግሞ በውስጣቸው ሕይወት እና መንፈስ አለባቸው።

    በተቀቡ ሰዎች መጽሐፍት መመሰጥ ከእነርሱ ጋር ኅብረት ለማድረግ ተወዳዳሪ የሌለው ዘዴ ነው። መንፈሳዊ መጽሐፍ ለማንበብ ጊዜ ሰጠህ ማለት ከመጽሐፉ ጸሐፊ ጋር ኅብረት አደረግህ ማለት ነው። በግል ቤትህ ውስጥ ሆነህ ከታዋቂ የእግዚአብሔር ሰው ጋር ለሦስት ሰዓት መጨዋወት መቻል እንዴት ያለ ትልቅ መታደል ነው!

    ይህን መጽሐፍ ስታነብ ከእኔ ጋር ኅብረት እያደረግህ ሲሆን፣ እኔም

    Enjoying the preview?
    Page 1 of 1