Discover millions of ebooks, audiobooks, and so much more with a free trial

Only $11.99/month after trial. Cancel anytime.

የተቀባው ሰው እና ቅባቱ
የተቀባው ሰው እና ቅባቱ
የተቀባው ሰው እና ቅባቱ
Ebook155 pages36 minutes

የተቀባው ሰው እና ቅባቱ

Rating: 5 out of 5 stars

5/5

()

Read preview

About this ebook

የቅባቱ ቦታው የተቀባው ሰው ጋር ነው። ቅባት ከተቀባው ሰው ጋር አይለያይም። ቅባቱ በእግዚአብሔር ሰው ውስጥ ነው! ቅባቱ ከእግዚአብሔር ሰው ጋር ነው! ቅባቱ በእግዚአብሔር ሰው ላይ ነው!
ይህ በዳግ ሂዋርድ ሚልስ የተጻፈው ማራኪ አዲስ መጽሐፍ ቅባቱን ለሚፈልጉ ሁሉ ልባቸውን ቅባቱ ወዳለበት የሚጎትት ነው።

Languageአማርኛ
Release dateJun 1, 2018
ISBN9781641348058
የተቀባው ሰው እና ቅባቱ
Author

Dag Heward-Mills

Bishop Dag Heward-Mills is a medical doctor by profession and the founder of the United Denominations Originating from the Lighthouse Group of Churches (UD-OLGC). The UD-OLGC comprises over three thousand churches pastored by seasoned ministers, groomed and trained in-house. Bishop Dag Heward-Mills oversees this charismatic group of denominations, which operates in over 90 different countries in Africa, Asia, Europe, the Caribbean, Australia, and North and South America. With a ministry spanning over thirty years, Dag Heward-Mills has authored several books with bestsellers including ‘The Art of Leadership’, ‘Loyalty and Disloyalty’, and ‘The Mega Church’. He is considered to be the largest publishing author in Africa, having had his books translated into over 52 languages with more than 40 million copies in print.

Related to የተቀባው ሰው እና ቅባቱ

Related ebooks

Reviews for የተቀባው ሰው እና ቅባቱ

Rating: 5 out of 5 stars
5/5

2 ratings0 reviews

What did you think?

Tap to rate

Review must be at least 10 words

    Book preview

    የተቀባው ሰው እና ቅባቱ - Dag Heward-Mills

    እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም ቀባው፥ እርሱም መልካም እያደረገ ለዲያብሎስም የተገዙትን ሁሉ እየፈወሰ ዞረ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረና፤

    ሐዋርያት ሥራ 10፣38

    ባቱ መንፈስ ቅዱስ ነው።  ስለ መንፈስ ቅዱስ የምትሰሙት ትምህርት በሙሉ ስለ ቅባቱ ነው።  ቅባት የተሰኘው ቃል ግስም፣ ስምም ነው።  ቅባት  ማለት ሰውን ለመቀባት የምንጠቀምበት ነገር ሊሆን ይችላል፣ ለምሳሌ የቅባት ዘይት።

    ቅባት፣ አንድ ሰው ላይ ቅባት የሚፈስስ ተግባርም ሊሆን ይችላል

    እኔ ስለ ቅባት ሳወራ የእግዚአብሔርን ሥራ እንድትሰራ ስለተሰጠህ የእግዚአብሔር መንፈስ እያወራሁ ነው።  ቅባቱን ለማየት ከተቀባው ሰው ባሻገር መመልከት ይጠይቃል።  የተቀባ ሰው በቅባቱ የተጠቀለለ ሰው ነው። 

    የናዝሬት ኢየሱስ ክርስቶስ በመንፈስ ቅዱስ እና በኃይል የተቀባ ስለነበር መልካምን እያደረገ ዞረ።  ኢየሱስ በወይራ ዘይት፣ በሞተር ዘይት፣ በዘንባባ ዘይት ወይንም በቫዝሊን ሊቀባ ይችል ነበር፤ ከእነዚህ በአንዱ ተቀብቶ ቢሆን ኖሮ የቅባቱ የወይራ ዘይት፣ የዘንባባ ዘይት፣ የሞተር ቅባት ወይንም ቫዝሊን ነው ለማለት እንችል ነበር።  ኢየሱስ ክርስቶስ ግን የተቀባው በመንፈስ ቅዱስ እና በኃይል ነበር።  ስለዚህ ኢየሱስ የቀባበት ዋናው ነገር መንፈስ ቅዱስ ነው፤ ልንል እንችላለን።  ምስጢራዊው መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር በቀባው ሰው ላይ ለመኖር ይመጣል።

    አንድ ሰው ሲቀባ፣ ሁሉን ቻይ እግዚአብሔር በሰውየው ላይ ለማረፍ፣ በውስጡ ለመኖር ወይንም በተለየ መንገድ አብሮት ለመሆን ይመጣል።  ሰውየውን የተቀባ እና ኃይለኛ የሚያደርገው ይህ ነው።  ከተቀባ ሰው ጋር ስትነካኩ የምትነካኩት ከእግዚአብሔር ጋር ነው። ከተቀባ ሰው ጋር ስትነካኩ የምትነካኩት ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ነው።

    ለዚህም ነው የተቀቡትን እና ቅባቱን በአግባቡ በማይዙ ሰዎች ላይ ከባድ ምላሽ የሚሰጠው ሰው ሳይሆን ለእግዚአብሔር ነው።  ሐናኒያና ሰጲራ ሐዋርያ እንዲሆኑ ለተቀባው ለጴጥሮስ ውሽት ሲናገሩ በቅፅበት ሞቱ።  ይህም ከባድ ምላሽ በመሆኑ ሌሎች የቤተክርስቲያን አባላትን አስፈራቸው።  ጴጥሮስ ግን አናኒያስ እና ሰጲራ የፈፀሙትን ስህተት አስረዳ።  እንዲህ አለ፣ "ጴጥሮስም፦ ሐናንያ ሆይ፥ መንፈስ 

    ቅዱስን ታታልልና ከመሬቱ ሽያጭ ታስቀር ዘንድ ሰይጣን በልብህ ስለ ምን ሞላ? ሳትሸጠው የአንተ አልነበረምን? ከሸጥኸውስ በኋላ በሥልጣንህ አልነበረምን? ይህን ነገር ስለ ምን በልብህ አሰብህ? እግዚአብሔርን እንጂ ሰውን አልዋሸህም አለው። ሐናንያም ይህን ቃል ሰምቶ ወደቀ ሞተም፤ በሰሙትም ሁሉ ላይ ታላቅ ፍርሃት ሆነ" (ሓዋርያት ሥራ 5፡3-5)

    አያችሁ?  አናኒያስ እና ሰጲራ የዋሹት ለመንፈስ ቅዱስን ነበር።  የዋሹት ጴጥሮስን ሳይሆን መንፈስ ቅዱስን ስለነበር ከባድ እና የከፋ የሚመስል ምላሽ አስከተለ።  ከተቀቡ ሰዎች ጋር ስትነጋገር(ስትጨቃጨቅ) ተጠንቀቅ። እነርሱ የተሸከሙትን ቅባት ታላቅነት ዝቅ አድርገህ ብትመለከት እና ሚዛንህ ቢሳሳት የሕይወትህንና የአገልግሎትህን ዘመን ልታሳጥር ትችላለህ።

    እንዲህ ብለህ ልትጠይቅ ትችላለህ፣ ታዲያ በዚህ ዘመን ብዙ ሰዎች ለመጋቢዎች እየዋሹ ለምንድነው በቅፅበት የማይሞቱት? መጋቢዎች ስላልተቀቡ ነው? መልሱ ቀላል ነው። በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ የመንፈስ ቅዱስ መገለጫዎች አሉ። በጴጥሮስ አገልግሎት እንኳን ሌላ ማንም ሰው በመዋሸቱ አልሞተም።  የእግዚአብሔር ኃይል በየትኛው ሰዓት በምን መንገድ እንደሚገለጥ በፍጹም አይታወቅም።  ሌሎች ብዙ ሰዎች መንፈስ ቅዱስን በመዋሸታቸው እንደሞቱ እርግጠኛ ነኝ።  ቅፅበታዊ ሞት አይሆን ይሆናል፣ ሞት ግን ያው ሞት ነው።

    ምዕራፍ 2

    በእርግጥ ቅባቱ ያለው የት ነው?

    ቅባቱ ሐብት የሚገኘው ከተቀባው ዘንድ አብሮ ነው። ቅባቱና ሰውየው አይለያዩም። የእግዚአብሔር ሰው፣ በውስጡ ከእርሱ ጋር እና በእርሱ ላይ ቅባቱ አለ።

    ዛሬ አንተና እኔ በእዚህ ሕይወት ፈውስን፣ ድልን፣ አርነትን የሚያመጣውን ነገር እየፈለግን ነው። ይህም ቅባቱ ነው! ቀንበርን የሚሰብረው ቅባቱ ነው።

    ስለዚህ ቅባቱ በትክክል ያለው የት ነው?  ቅባቱን ከምዕራብ ተራራ ገበያ ልናገኝ እንችላለን? ቅባቱን በአውሮፕላን ማረፊያ ልናገኘው እንችላለን? ቅባቱን ቢሮ ውስጥ ልናገኘው እንችላለን? ቅባቱን ሱቅ ውስጥ ሊገኝ ይችላል? በፍጹም ቅባቱ ከእነዚህ ሥፍራዎች በአንዱም አይገኝም።

    ቅባቱ የሚገኘው በተቀባው ሰው ውስጥ ነው!

    ቅባቱ የሚገኘው ከተቀባው ሰው ጋር ነው!

    ቅባቱ የሚገኘው በተቀባው ሰው ላይ ነው!

    ኃይል ያለው የቱ ነው፣ ቅባቱ ወይንስ የተቀባ ሰው

    ቀንበርን የሚሰብረው ቅባቱ በመሆኑ የቅባቱን ትክክለኛ አድራሻ ማወቅ አስፈላጊ ነው።  ከዓመታት በፊት ብርቱካን በሽታን እንደሚፈውስ ተደረሰበት።  ከጥቂት ጊዜ በሃላ ሳይንስ ከብርቱካን ውስጥ ፈውስን የሚያመጣውን ንጥረ ነገር ደረሰበት።  ቫይታሚን ሲን አገኙ! ዛሬ ሰዎች ቫይታሚ ሲን ብቻ መውሰድን ያተኩራሉ።  ፈውሱን የሚያመጣውን ሚስጢር ደርሰውበታል።

    ልክ እንደዚሁ፣ በተቀቡ ሰዎች ውስጥ ተዓምራትን የሚሰራ ንጥረ ነገር አለ፤ ያም ንጥረ ነገር ቅባቱ ነው። አለመታደል ሆኖ ቫይታሚን ሲን ከብርቱካን ተለይቶ እንደወጣ፣ ቅባቱን ከተቀባው ሰው ለይቶ ለማውጣት የሚያስችል የኬሚካል አሰራር የለም።  ከቅባቱ ጋር ለመድረስ ከፈለግህ ወደተቀባው ሰው መምጣት አለብህ።  የተቀባው ሰው ጋር ሳትመጣ ትክክለኛ ቅባትን በጠርሙስ እያሸገ የሚያወጣ ቤተ ሙከራም ሆነ ፋብሪካ የለም።  

    እግዚአብሔር ቅባቱን ያኖርበት ዘንድ ጥቁሩን፣ ነጩን፣ የተማረውን፣ ፉዞውን ሰው ሳይቀር መርጦታል።  በእርሱ ውስጥ ቅባቱ ስላለ ቅባቱን ስለሚሸከም ወደ ሰውየው መሄድ ይኖርባችኋል።  የተቀባ ሰው እና ቅባቱ በእንዲህ መልኩ የተቆራኙ መሆናቸው 

    ለኩራተኛ ክርስቲያኖች ችግር ነው።  እግዚአብሔር እንዲጠቀምብኝ እፈልጋለሁ ነገር ግን ቅባቱን ለማግኘት ወደ የተቀባ ሰው ለመቅረብ አልፈልግም።

    ቅባቱ በሶስት ሥፍራዎች

    1. ቅባቱ ከተቀባው ሰው ጋር ነው

    እርሱም ዓለም የማያየውና የማያውቀው ስለ ሆነ ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው፤ ነገር ግን ከእናንተ ዘንድ ስለሚኖር በውሥጣችሁም ስለሚሆን እናንተ ታውቃላችሁ።

    ዮሐንስ 14፣17

    2. የተቀባ ሰው የእግዚአብሔር መንፈስ ይሸከማል

    የነቢዩንም የኢሳይያስን መጽሐፍ ሰጡት፥ መጽሐፉንም በተረተረ ጊዜ፦ የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ቀብቶኛልና፤ ለታሰሩትም መፈታትን ለዕውሮችም ማየትን እሰብክ ዘንድ፥ የተጠቁትንም ነጻ አወጣ ዘንድ የተወደደችውንም የጌታን ዓመት እሰብክ ዘንድ ልኮኛል ተብሎ የተጻፈበትን ስፍራ አገኘ።

    ሉቃስ 4፣18

    3. የተቀባ ሰው በውስጡ የእግዚአብሔርን መንፈስ ይይዛል

    እናንተስ ከእርሱ የተቀበላችሁት ቅባት በእናንተ ይኖራል፥ ማንም ሊያስተምራችሁ አያስፈልጋችሁም፤ ነገር ግን የእርሱ ቅባት ስለ ሁሉ እንደሚያስተምራችሁ፥ እውነተኛም እንደ ሆነ ውሸትም እንዳልሆነ፥ እናንተንም እንዳስተማራችሁ፥ በእርሱ ኑሩ።

    1ኛ ዮሐንስ 2፣27

    የመንፈስ ቅዱስ ቅባት በሰው ውስጥ፣ ከሰው ጋር፣ ወይንም በሰው ላይ ነው።  የቅባቱ ትክክለኛ አድራሻ ይህ ነው።  የተቀባ ሰው ለአንተ አስፈላጊ የሚሆነው ለዚህ ነው።  ለአንተ አስፈላጊ የሆነውን ነገር ተሸካሚ ነው።  እርሱ በራሱ ደካማ ኃይል የሌለውና የማይጠቅም ሰው ነው።  ነገር ግን ከመንፈስ ቅዱስ የተወሰነ መጠን ከእርሱ ጋር በውስጡ ወይንም በእርሱ ላይ እንዲሸከም ተመርጧል።  ቅባቱ ከሰውየው ጋር የተያያዘ እና የሰውየው አካል በመሆኑም ሰውየው እራሱ አንዳች ኃይል ያለው ይመስለንና እንሳሳታለን።

    ቅባቱን እና የተቀባ ሰውን በአግባቡ ለመያዝ ያለህ ችሎታ ቅባቱ ዘንድ የመድረስ ችሎታህን ይወስነዋል።  የሚያስፈልግህ ቅባቱ እንደሆነ ልብ በል።  የብርቱካን ጭማቂን በጠርሙስ የመያዝ ችሎታህን አስብ።  የምትፈልገው ጭማቂውን ነው፣ ነገር ግን ጭማቂውን የያዘው ጠርሙሱ ስለሆነ ጠርሙሱን በጥንቃቄ ልትይዘው ይገባል።

    ብዙ ሰዎች የተቀባ ሰውንና ቅባቱን በተመለከተ መንፈሳዊ ስህተት ይሰራሉ።  ቅባቱን ይፈልጋሉ ከተቀባው ሰው ጋር ግን ግንኙነት አይፈልጉም በተቀባው ሰው ላይ የተበላሸ አመለካከት ከቅባቱ እየለያቸው እና ወደ ውድቀት እየመራቸው እንደሆነ አያውቁም።

    Enjoying the preview?
    Page 1 of 1