Discover millions of ebooks, audiobooks, and so much more with a free trial

Only $11.99/month after trial. Cancel anytime.

የመከተል ጥበብ
የመከተል ጥበብ
የመከተል ጥበብ
Ebook307 pages2 hours

የመከተል ጥበብ

Rating: 5 out of 5 stars

5/5

()

Read preview

About this ebook

እግዚአብሔርን መከተል አስደሳች የአዳዲስ ግኝት ጉዞ ነው፡፡ሌሎችን ሰዎች መከተልና መቅዳት ኢየሱስ ክርስቶስ ዋና የስልጠና ዘዴ አድርጎ የመረጣቸው ጥንታዊ የመማሪያ ጥበቦች ናቸው፡፡ከዚህ በጊዜ ከተፈተነ የስልጠና ዘዴ አፍሮ ከመሸሽ ይልቅ የመከተልን ጥበብ ውበትና ያለበትን ጭምትነት ለመረዳት ጊዜው አሁን ነው፡፡ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ማንን፣ ምንን እና እንዴት በሚገባ መከተል እንደሚገባህ ትማራለህ፡፡ይህ የዳግ ሂዋርድ ሚልስ ድንቅ መጽሐፍ ለመከተል ጥበብ በክርስትና ልምምዳችን ውስጥ ተገቢውን ቦታ ይሰጠዋል፡፡

Languageአማርኛ
Release dateJul 27, 2016
ISBN9781613954485
የመከተል ጥበብ
Author

Dag Heward-Mills

Bishop Dag Heward-Mills is a medical doctor by profession and the founder of the United Denominations Originating from the Lighthouse Group of Churches (UD-OLGC). The UD-OLGC comprises over three thousand churches pastored by seasoned ministers, groomed and trained in-house. Bishop Dag Heward-Mills oversees this charismatic group of denominations, which operates in over 90 different countries in Africa, Asia, Europe, the Caribbean, Australia, and North and South America. With a ministry spanning over thirty years, Dag Heward-Mills has authored several books with bestsellers including ‘The Art of Leadership’, ‘Loyalty and Disloyalty’, and ‘The Mega Church’. He is considered to be the largest publishing author in Africa, having had his books translated into over 52 languages with more than 40 million copies in print.

Related to የመከተል ጥበብ

Related ebooks

Reviews for የመከተል ጥበብ

Rating: 5 out of 5 stars
5/5

1 rating0 reviews

What did you think?

Tap to rate

Review must be at least 10 words

    Book preview

    የመከተል ጥበብ - Dag Heward-Mills

    የመከተል ጥበብ ምንድን ነው?

    የመከተል ጥበብ ገለፃ

    1. የመከተል ጥበብ ማለት የመቅዳት ጥበብ ነው፡፡

    2. የመከተል ጥበብ አንድን ሰው የመምሰል ጥበብ ነው፡፡

    3. የመከተል ጥበብ አንድን ነገር የመቅረጽ ጥበብ ነው፡፡

    4. የመከተል ጥበብ እንደ አንድ ሰው ለመሆን የመሞከር ጥበብ ነው፡፡

    5. የመከተል ጥበብ የመባዛት ጥበብ ነው፡፡

    6. የመከተል ጥበብ የክሎኒንግ ጥበብ ነው፡፡

    7. የመከተል ጥበብ ድርብ የመሆን ጥበብ ነው፡፡

    8. የመከተል ጥበብ መንታ የመሆን ጥበብ ነው፡፡

    9. የመከተል ጥበብ በቅርብ የመከተል ጥበብ ነው፡፡

    10. የመከተል ጥበብ ወደፊት የመስፈንጠር ጥበብ ነው፡፡

    ስኬታማ በሆነ መልኩ የመከተልን ጥበብ የተገበሩት

    1. ሕፃናት የመከተልን ጥበብ ይጠቀማሉ፡፡

    ህፃናት እጅግ በአጭር ቆይታዎች ብቻ በቅርብ ተከትለው ውስብስብ ቋንቋዎችን መናገር እስኪችሉ ድረስ በታላላቅ እርምጃዎች ወደፊት ለመስፈንጠር የመከተልን ጥበብ ይጠቀማሉ፡፡ ሕጻናት ሁሉንም የሚማሩት በመከተል፣ በመቅዳት ወይም በመምሰል ጥበብ ነው፡፡

    2. የመከተልን ጥበብ በመጠቀም አገራት በመቶዎች ለሚቆጠሩ ዓመታት ሀብታም ሆነዋል፡፡

    አውሮፓና አሜሪካ አንጋፋዎቹ የዓለማችን ሀብታም ሀገራት ለመሆን የመከተልን ጥበብ ተጠቅመዋል፡፡ በመምሰል /የበለጠ ለመሥራት በመሞከር ሁሉም አውሮፓዊ አገራት እንደጎረቤቶቻቸው በመሆን አንድ ዓይነት ከበርቴ አገራት ወደመሆን አድገዋል፡፡ መንገዶቻቸው ህንፃዎቻቸውና ሌሎች መሠረተልማቶቻቸው ተመሳሳይ ናቸው፡፡ የባንክና የኢኮኖሚ ሥርዓቶቻቸው አንድ ዓይነት ናቸው ማለት ይቻላል፡፡ የጦር ብቃታቸውም ተመሳሳይ ነው፡፡ በእነዚህ አገራት የህዝቦቹ የሕይወት ዘዬና የኑሮ ሁኔታ ተመሳሳይ ነው፡፡ በእርግጥም የበለጠ አድርጎ ለመሥራት ባለ ጥረት አማካኝነት እያንዳንዱ አገር በብልጽግና እሽቅድምድም ኋላ መቅረትን አሻፈረኝ በማለት ጎረቤቱ ላይ ደረሰ፡፡

    3. በቅርቡ ሀብታም የሆኑ ሀገራት የመከተልን ጥበብ ይጠቀማሉ፡፡

    ታይዋን፣ ቻይናና ኮርያ በመከተልና በመቅዳት ችሎታቸው እጅግ የታወቁ ናቸው፡፡ በእርግጥም በቅርቡ ባለጠጎች የሆኑ አብዛኞቹ ሀገራት የመከተልን ጥበብ ተጠቅመዋል፡፡ ባለፉት አምሳ አመታት የበለፀጉት ሀገራት በመቅዳት ችሎታቸው በሚገባ የታወቁ ናቸው፡፡ በእርግጥም አብዛኞቹ ምርቶቻቸው በቀላሉ፣ ቅጅ ተብለው ነበር የሚጠሩት፡፡ እጅግ ታዋቂ የሆኑ የአውሮፓ ሞዴሎች አምሳያ የሆኑ መኪኖችን አመረቱ፡፡ ኮርያውያኑ ዴዉ መኪኖቻቸውን ኦፔልን ተመርኩዘው፣ ሳንግዮንግን ደግሞ መርሴዴስ ቤንዝን፣ ሃዩንዳይን ደግሞ ቶዮታን አስመስለው መስራቱ ምንም አያሳፍራቸውም ነበር፡፡ እፍረት አልባ በሆኑ ቅጂዎቻቸው ከሌላው ጋር ከመተካከል አልፈው ግንባር ቀደም መኪና አምራቾች እስኪሆኑ ድረስ ወደፊት ተስፈነጠሩ፡፡

    በሁሉም የቴክኖሎጂና የጥረት መስክ ማለት ይቻላል፣ ሌሎች ሊያልሙት ብቻ የሚችሉትን ሀብት በመፍጠር ሌላው ላይ ከመድረስ አልፈው ወደፊት መጥቀዋል፡፡ ለመቅዳት እፍረት የያዛቸው ጥጋቸውን ይዘው ቆመው እነዚህ የቅጅ ባለሙያዎች ወደፊት መጥቀው ሚሊዮነሮች፣ቢሊዮነሮችና ትሪሊዮነሮች ሲሆኑ ማየት ብቻ ነበር የሚችሉት፡፡

    4. የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ የመከተልን ጥበብ ተጠቅሟል፡፡

    ኢየሱስ መሀይም ዓሳ አጥማጆችን የዓለምአቀፍ እንቅስቃሴ መሪዎችና አስተዳዳሪዎች አድርጎ ለመቀየር የመከተልን ጥበብ ተጠቅሟል፡፡ የእግዚአብሔር ልጅ የመከተልን ጥበብ እንደ ብቸኛ የማሰልጠኛ ዘዴ የሚጠቀም ከሆነ እጅግ ከፍተኛና የላቀው የመማር፣ የስልጠና እና የማስተማር ዘዴ መሆን አለበት፡፡

    የመከተል ጥበብ አንድን ሰው የመቅዳት ጥበብ ነው፡፡ የመከተል ጥበብ እንደምታደንቀው ሰው የመሆን ጥበብ ነው፡፡ የመከተል ጥበብ ከፊትህ ያለ የአንድ ነገር አምሳያ የመሆን ጥበብ ነው፡፡ በመከተል ጥበብ አማካኝነት በአገልግሎትህ መስተካከልና መጥቀህ መሄድ ትችላለህ፡፡

    ምዕራፍ 2

    በመከተል ጥበብ ስኬታማ መሆን የሚቻልበት መንገድ

    …እንድትመስሉ እንጂ ዳተኞች እንዳትሆኑ፥…

    ዕብራውያን 6፡11-12

    ሰዎችን እንድንከተል የሚነግሩን በርካታ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትዕዛዛት አሉ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንዴት ሰዎችን መከተል እንደሚገባን በሚያሳዩ ምሳሌዎች የታጨቀ ነው፡፡ በዚህ ምዕራፍ በመከተል፣ በመቅዳት፣ የበለጠ ለመስራት በመሞከርና የቀደሙህ ላይ በመድረስ ስኬታማ ለመሆን የሚያስፈልጉህን መርሆች ትማራለህ፡፡

    ዘጠኝ የመከተል መርሆች

    1. ራሱን እግዚአብሔርን ለመከተል በመምረጥ በመከተል ጥበብ ስኬታማ መሆን ትችላለህ፡፡

    እንግዲህ እንደ ተወደዱ ልጆች እግዚአብሔርን የምትከተሉሁኑ፥

    ክርስቶስም ደግሞ እንደ ወደዳችሁ ለእግዚአብሔርም የመዓዛ ሽታ የሚሆንን መባንና መሥዋዕትን አድርጎ ስለ እናንተ ራሱን አሳልፎ እንደ ሰጠ በፍቅር ተመላለሱ።

    ኤፌሶን 5፡1-2

    እግዚአብሔርን ስኬታማ በሆነ መልኩ የምንከተለው በፍቅርና በመስዋዕትነት በመመላለስ ነው፡፡ እግዚአብሔርን መከተል ይቻል እንደነበር ታውቅ ነበር? ከእግዚአብሔር ይልቅ የምትከተለው የሚሻል ሰው የቱ ነው? የእግዚአብሔር ቃል እግዚአብሔርን መከተል የምፈልግ ከሆነ በእርግጥ ምን ማድረግ እንዳለብን ያሳየናል፡፡ ማድረግ የሚጠበቅብን ማፍቀርንና መስዋዕት መሆንን መማር ብቻ ነው፡፡ እነዚህን ሁለት ነገሮች ማድረግ እግዚአብሔርን ራሱን እየተከተልክ መሆንህን ያረጋግጣሉ፡፡ እግዚአብሔርን እየተከተልኩ ነው የምትል ከሆነ እግዚአብሔር ፍቅር ነውና፣ በመለኮታዊ ፍቅር ውስጥ የምትመላለስ ሰው መሆን አለብህ፡፡

    2. ክርስቶስን እየተከተለ ያለን የእግዚአብሔር አገልጋይ ሰውን በመከተል ጥበብ ስኬታማ መሆን ትችላለህ፡፡

    እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እኔን ምሰሉ።

    1ኛ ቆሮንቶስ 11፡1

    ጳውሎስ የቆሮንቶስን ቤተክርስቲያን እንዲከተሉት አስተምሯቸዋል፤ ነገር ግን ክርስቶስን እስከተከተለ ድረስ ብቻ እንዲከተሉት አስጠንቅቋቸዋል፡፡ በእርግጥም የእግዚአብሔር ተከታዮች ከመሆን ይልቅ የሚሊዮነሮች፣ የቢዝነስ ሥራ አስኪያጆችና የፖለቲከኞች ተከታይ ናቸው፡፡ እነዚህን ዓለማዊ ሰዎች እንደሚከተሉና ከኢየሱስ ይልቅ በይበልጥ እንደነርሱ ለመሆን እንደሚመኙ ከሚያነብቧቸው መጻሕፍት ታስተውላለህ። ዛሬ ዛሬ መጋቢያን የአሜሪካን ፕሬዘዳንቶች፣ የሚሊዮነሮችንና የስኬታማ ሥራ ፈጣሪዎችን የህይወት ታሪክ የሚያወሩ ጽሑፎችን ነው የሚያነቡት፡፡

    3. በእርግጥ ልትከተል የምትፈልገውን ሰው የተከተለን ሰው በመከተል፣ የእግዚአብሔርን ሰው በመከተል ስኬታማ ልትሆን ትችላለህ፡፡

    ወንድሞች ሆይ፤ የእኔን አርኣያነት በመከተል ከሌሎች ጋር ተባበሩ፤ እኛ በሰጠናችሁ ምሳሌነት መሠረት የሚኖሩትንም አስተውሉ።

    ፊልጵስዮስ 3፡17 (አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

    ከአመታት በፊት በተአምራት አገልግሎት ውስጥ መሆን እፈልግ ነበር፡፡ ከእኔ ቀድሞ በተአምራት አገልግሎት ውስጥ የነበረን ሰው መከተል እንደሚኖርብኝ አውቅ ነበር፡፡ ከሰማኋቸው ሁሉ ታላቁ የተአምራት አገልግሎት ስለነበራት ካትሪን ኩልማንን ለመከተል ወሰንኩኝ፡፡ እንደ ሐኪምነቴ በምታደርጋቸው ተአምራት በጣም እደነቅ ነበር፡፡ ግን አንድ ችግር ነበረኝ፡፡ ስለሞተች በዚህ ምድር ላይ ላገኛት አልችልም፡፡ ኪሳራ ላይ ሆንኩ፤ የሞተን ሰው እንዴት ልከተል እንደምችል አላውቅም ነበር፡፡ ለሞተ ሰው እንዴት መባ መስጠት እችላለሁ? የሞተን ሰው እንዴት ላናግር እችላለሁ? መንፈሷን ከሙታን መጥራት ሊኖርብኝ ነው?

    በድንገት መንፈስ ቅዱስ ይህን ነገረኝ፣ በእርግጥ ካትሪን ኩልማንን መከተል የምትፈልግ ከሆነ ቤኒ ሂንን ተከተል፡፡ በድንገት በመንገዴ ላይ ብሩህ መብራት በራ፤ ምን ማድረግ እንዳለብኝ አወቅሁ፡፡ ቤኒ ሂንን ለመከተልና ስለ አገልግሎት፣ ፈውስና ተአምራት የምችለውን ሁሉ ለመማር ፈጅመን ጉዞዬን ጀመርኩ፡፡ ጳውሎስ ከፊልጵስዮስ ሰዎች ጋር ሲካፈል የነበረው እውነት ይህ ነው፡፡ የእኔን ምሳሌ የተከተሉትን በመከተል ልትከተሉኝ ትችላላችሁ፡፡

    4. በጌታ ፀጋ የሚመላለሱ የሰዎች ጉባዔ ተከታይ መሆን ትችላለህ፡፡

    ደግሞ እናንተ ቃሉን በብዙ መከራ ከመንፈስ ቅዱስ ደስታ ጋር ተቀብላችሁ፥ እኛንና ጌታን የምትመስሉ ሆናችሁ፤

    1ኛ ተሰሎንቄ 1፡6

    አንድን ሰው ብቻ በመከተል ፈንታ በአንድ ልዩ መንገድ የሚመላለሱ የሰዎች ጉባዔ መከተል ትችላለህ፡፡ ለምሳሌ የአንድን ቤተክርስቲያን ወይም አገልግሎት መሪዎች ልትከተል ትችላለህ። እግዚአብሔርን አብረው የሚያገለግሉ ጓደኛሞችን ቡድንም ልትከተል ትችላለህ፡፡

    ከብዙ አመታት በፊት ከኬነት ሔገን ጋር ሰው አስተዋወቀኝ፤ አብሯቸው የሚሆናቸውን ሰዎች አስተዋልኩ፡፡ እንደ ኬነት ኮፕላንድ፣ ጄሪ ሳቬል፣ ፍሬድ ፕሪንስ፣ ቻርልስ ካፕስ እና ጆን ኦስቲን ያሉ ሰዎች በኮንፍረንሶቹ ላይ እና በመጽሔቶቹ ውስጥ ይገኙ ነበር፡፡ ይህ የእምነት ሰዎች ቡድን እኔን ሳበኝና ስከተላቸው ራሴን አገኘሁት፡፡ ልከተላቸው የምችላቸው ተለይተው የሚታዩ ቡድን ስለነበሩ መጻሕፍቶቻቸውን ሳነብብና ከእነርሱ ስማር ራሴን አገኘሁት፡፡

    5. የአንድ ቤተክርስቲያን ተከታይ በመሆን በመከተል ጥበብ ስኬታማ ልትሆን ትችላለህ፡፡

    እናንተ፥ ወንድሞች ሆይ፥ በይሁዳ የሚኖሩትን በክርስቶስ ኢየሱስ ያሉትን የእግዚአብሔርን ማኅበሮች የምትመስሉ ሆናችኋልና፤ እነርሱ ከአይሁድ መከራ እንደ ተቀበሉ፥ እናንተ ደግሞ ያንን መከራ ከአገራችሁ ሰዎች ተቀብላችኋልና።

    1ኛ ተሰሎንቄ 2፡14

    የአንድን ቤተክርስቲያን መሪዎች፣ ታሪክ፣ እምነት፣ ድሎች፣ ችግሮች፣ ስህተቶችና የመሳሰሉትን በማጥናት አንድን ቤተክርስቲያን መከተል ትችላለህ፡፡ አንድን ቤተክርስቲያን በአግባቡ ለመከተል በየትኛውም መልኩ ቢሆን ታሪኳን ማጥናት አለብህ፡፡ በርካታ አብያተክርስቲያናት አመታት ባለፉ ቁጥር አስገራሚ ለውጦችን ያካሂዳሉ፡፡ በአብዛኛው ዛሬ ያለችን ቤተክርስቲያን ከመቶ አመታት በፊት ከነበረችው ጋር ልታጻጽር አትችልም፡፡

    ከመቶ አመታት በፊት የስዊዝ ቤተክርስቲያን በሩቅ የተልዕኮ መስኮች እንዲሞቱ እስክትልክ ድረስ እጅግ ንቁ ነበረች፡፡ በስዊዝ ቤተክርስቲያን ጥረት አማካኝነት ድነትና ክርስትና እንደ ጋና እና ናይጄሪያ ወዳሉ ድፍን ሀገራት ደረሰ፡፡ ዛሬ የስዊዝ ቤተክርስቲያን ከመሞቷ የተነሳ አብዛኞቹ ጉባኤዎች ተዘግተዋል ክርስትናም ከሌላ አገር የመጡና የስደተኞች እንቅስቃሴ ተደርጎ ነው የሚታየው፡፡

    ዛሬ ሚስዮናውያንን ወደ ዓለም ይልክ የነበረው የስዊዝ ማህበር ሕንፃ ወደ ሆቴልነት ተቀይሮ የታላላቅ የሚስዮን ሥራዎቻቸው ማህደራት ከሆቴሉ ሥር ካለ ምድር ቤት ውስጥ ተቀምጠዋል!

    ከሜተዲስት ቤተክርስቲያን እጅግ ብዙ ተምሬአለሁ፡፡ በርካታ መልካም ምሳሌዎቻቸውን ተከትያለሁ፣ የመስራቻቸውንም ሕይወት አጥንቻለሁ፡፡ ያችን ቤተክርስቲያን በመከተል፣ እግዚአብሔር ታላቅ እይታና የአገልግሎቴን አቅጣጫ ሰጥቶኛል።

    6. መንፈስ ቅዱስ የሚያሳይህ በጎ ነገሮች ተከታይ መሆን አለብህ፡፡

    በጎንም ለማድረግ ብትቀኑ የሚያስጨንቃችሁ ማን ነው?

    1ኛ ጴጥሮስ 3፡13

    በጎ ነገሮችን መከተል አለብህ፡፡ መንፈስ ቅዱስ በአንድ ሰው አገልግሎት ውስጥ ስላለ ስለአንድ ነገር ልብህን ከነካው እግዚአብሔር ትኩረትህን ማድረግ ወደሚገባህ አንድ ነገር እየሳበ እንደሆነ መቁጠር አለብህ፡፡ መንፈስ ቅዱስ ሁልጊዜ መከተል ያለብንን ጥሩ ነገሮች እያሳየን ነው፡፡ ስለሌሎች አብያተክርስቲያናትና አገልግሎቶች በጎ ነገሮችን ለማስተዋል ልብህን መክፈት ያንተ ድርሻ ነው፡፡

    ምናልባት በአንዱ ቤተክርስቲያን ያለው ሙዚቃ እንዴት ጥሩ እንደሆነ ልታስተውል ትችላለህ፡፡ ምናልባትም ኳየሩ እንዴት ግሩም እንደሆነ ልታጤን ትችላለህ፤ ምናልባት በአንድ ሰው ቤተክርስቲያን ያለው ሽንት ቤት ምን ያህል ንጹሕ እንደሆነ ልታይ ትችላለህ፡፡ ምናልባት የአንዱ ቤተክርስቲያን ሕንፃ አሰራር እንዴት ግሩም እንደሆነ አይተህ ሊሆን ይችላል፡፡ የአንድ ሰው ስብከት እንዴት መልካም እንደሆነ አጢነህ ሊሆን ይችላል፡፡ ምልባት የአንድ ሰው ዝማሬ እንዴት ቆንጆ እንደሆነ አስተውለህ ሊሆን ይችላል፡፡ እነዚህ የምታስተውላቸው በጎ ነገሮች ሁሉ መከተል የሚገባህን ነገሮች በተመለከተ ከመንፈስ ቅዱስ የሚመጡ መልዕክቶች ናቸው፡፡

    7. የሚልኳቸውንና የሚሾሟቸውን ሰዎች በመከተል የእግዚአብሔርን ሰው በመከተል ስኬታማ መሆን ትችላለህ፡፡

    ስለዚህ እኔን እንድትመስሉ እለምናችኋለሁ፡፡ እንግዲህ በጌታ የተወደደውንና የታመነውን ልጄን ጢሞቴዎስን የላክሁላችሁ በዚህ ምንክንያት ነው፤ እርሱም በየስፍራው በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ከማስተምረው ትምህርት ጋር የሚስማማውን፣ በክርስቶስ ኢየሱስ ያለውን የሕይወት አካሄዴን ያሳስባችኋል፡፡

    1ኛ ቆሮንቶስ 4፡16-17 (አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

    ጳውሎስ ቆሮንቶሳውያኑ እርሱን በቅርበት እንዲከተሉት ፈልጎ ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት ጢሞቴዎስን ሾመውና ከቆሮንቶሳውያን ጋር እንዲሆን ላከው፡፡ ከጳውሎስ ጋር መዛመድ የፈለገ ማንኛውም ሰው ከጢሞቴዎስ ጋር መዛመድ ነበረበት፡፡

    ከተላኩና ከተሾሙ ሰዎች ጋር መዛመድ የማይችሉ ሰዎች የመማርና የመከተል አጋጣሚ እያመለጣቸው እንደሆነ አያስተውሉም፡፡ ታላላቅ ሰዎች በአብዛኛው ከአንተ ጋር እንዲገናኝና እንዲነጋገር አንድን ሰው መላክ ግድ ይሆንባቸዋል። ከራሱ ከዋናው ሰውዬ ጋር ስላልተገናኘህ መግባባትና መዛመድ ካቃተህ በርካታ በረከቶች ያመልጡሃል፡፡ የመከተል ጥበብ የተላኩ ሰዎችን የመከተል ጥበብ ነው፡፡

    ከዴቪድ ዮንጊ ቾ ጋር ለመገናኘት ብዙ ጊዜ ኮሪያ ሄጃለሁ፡፡ እኔን እንዲንከባከቡኝ ከሾማቸው ሰዎችና ከሌሎች የቦርድ አባላት ጋር መዛመድ ነበረብኝ፡፡ እርሱ የሾማቸውን ሰዎች በደስታ መቀበሌ ከእርሱ ጋር ካለኝ ግንኙነት ለመጠቀሜ ቁልፍ ነበር፡፡ ከተላኩ ባለሥልጣናት ጋር ለመስራት እጅግ ትልቅ የሆነ ሰው ለመከተል እጅግ ትልቅ ነው!

    8. እምነቱንና ትዕግሥቱን ከተከተልክ የእግዚአብሔርን ሰው በመከተል ስኬታማ መሆን ትችላለህ፡፡

    በእምነትና በትዕግሥትም የተስፋውን ቃል የሚወርሱትን እንድትመስሉ እንጂ ዳተኞች እንዳትሆኑ፥ ተስፋ እስኪሞላ ድረስ እያንዳንዳችሁ ያን ትጋት እስከ መጨረሻ እንድታሳዩ እንመኛለን።

    ዕብራውያን 6፡11-12

    በምትከተለው ሰው ውስጥ ልትፈልጋቸው የሚገቡ ሁለት ቁልፍ ነገሮች እምነቱና ትዕግሥቱ ናቸው፡፡ ለምን ይህን አልኩኝ? የእግዚአብሔርን የተስፋ ቃሎች እንዲወርስ ያስቻሉት የሰውየው እምነትና ትዕግሥት መሆናቸውን መጽሐፍ ያስተምረናል፡፡

    ኬኔት ሔገን ያለውን አይነት ዓለምአቀፍ አገልግሎት የሰጡት እምነቱና ትዕግሥቱ ናቸው፡፡ ዮንጊ ቾ ያለው እምነትና ትዕግሥት ነው በዓለማችን ትልቁን ቤተክርስቲያን የሰጠው፡፡ ቤኒ ሂን ያሉትን የተአምራት ክሩሴዶች ያስገኙለት እምነቱና ትዕግሥቱ ናቸው፡፡ የፍሬድ ፕሪንስ እምነትና ትዕግሥት የነበረውን ዓይነት አገልግሎት ሰጥቶታል፡፡ ሬይንሃርድ ቦንኬ የነበረው እምነትና ትዕግሥት ነው በአፍሪካ ያደረጋቸውን ታላላቅ ክሩሴዶች ያስገኘለት፡፡

    እነዚህ ሰዎች የነበሯቸውን ነገሮች ያስገኘላቸው ገንዘብ፣ ትውውቅ ወይም ማስታወቂያዎች አይደሉም፡፡ የተቀበሉትን የሰጣቸው እምነታቸውና ትዕግሥታቸው ነው፡፡

    ወዳጄ ሆይ የእግዚአብሔርን ሰው በመከተል ስኬታማ መሆን ትፈልጋለህ? እንግዲያውስ እምነቱንና ትዕግሥቱን ተከተል! የአንድን ሰው እምነት መከተል ምን ማለት ነው? የአንድን ሰው እምነት መከተል ማለት፣ ምን ያምን ነበር፣ ያመናቸውን ነገሮችስ ለምን አመነ!? ብሎ መጠየቅ ነው፡፡ የቢሊ ግርሃምን እምነት እያጠናሁ ሳለሁ እያንዳንዱ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የእግዚአብሔር ቃል እንደሆነ ለማመን መሠረታዊ ውሳኔ እንደወሰነ አስተዋልኩ፡፡ በዚህ እምነት ምክንያት ለኃጢአተኞች ሲሰብክ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን ይጠቅሳል፡፡ የእግዚአብሔር ቃሎች ከሆኑ ለሰዎች ሲነበቡ ቃሎቹ ታላቅ የማዳን፣ የመፈወስና ነፃ የማውጣት ኃይል እንደሚኖራቸው ያምናል፡፡ ብታነብብና ብታጠና ስለታላላቅ ሰዎች እምነት በርካታ ነገሮችን ታውቃለህ።

    ከዚህ ውጭ ስለታላቅ ሰው እምነት እንዴት ልታውቅ ትችላለህ? አንድ ሰው ቀደም ሲል በአገልግሎቱ ላይ የተናገራቸውን ነገሮች በማየትና በመስማት! በአንድ ሰው ቀጣይ የአገልግሎት ክፍል ውስጥ ያመናቸው ነገሮች አስገራሚ ፍሬዎችን ታገኛለህ፡፡ በቀዳሚው የአገልግሎቱ ክፍል ግን ሰውየው ከእግዚአብሔር ለሚገኙ ታላላቅ ነገሮች እምነትን ሲለማመድ ልታይና ሊሰማህ ይችላል፡፡ በመጀመሪያው የአገልግሎቱ ምዕራፍ ጥቂት የሚታይ ነገር እና ብዙ እምነትና አዋጅ አለ፡፡

    የታላላቅ ሰዎችን እምነትና ትዕግሥት ስተከተል፣ ያኔ ትክክለኛ ነገሮችን ትከተላለህ፡፡ ዛሬ አንዳንድ ሰዎች የእግዚአብሔር ሰዎች የሚለብሱትን ዓይነት መልበስ፣ ተመሳሳይ ጫማዎች ማድረግና እንድ ዓይነት መኪኖችን መንዳት ይፈልጋሉ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የተስፋ ቃላቸውን በመኪኖቻቸው፣ በቤቶቻቸው እና በልብሶቻቸው አማካኝነት ወረሱ አይልም! የተስፋ ቃላቸውን የወረሱት በእምነታቸውና በትዕግሥታቸው ነው!

    ታዲያ የአንድን ሰው ትዕግሥት እንዴት መከተል ትችላለህ? አንድ ሰው በሆኑ ነገሮች መቼ ማመን እንደጀመረና እውን መቼ እነርሱን መለማመድ እንደጀመረ በማወቅ የአንድን ሰው ትዕግሥት ማጥናት ትችላለህ፡፡ አንዳንድ ሰዎች በአንድ አቅጣጫ አምነው መሥራት የጀመሩባቸውን የአመታት ቁጥር አስልተህ ስትደርስበት ምን ያህል ታጋሽ እንደሆኑ ትደነቃለህ፡፡

    ብዙ የእግዚአብሔር ሰዎች ጥቂት ውጤቶችን ብቻ እያገኙ ለበርካታ ዓመታት ሲለፉ ቆይተው እግዚአብሔር ታላላቅ ነገሮችን በሕይወታቸውና በአገልግሎታቸው ማብቂያ ላይ ሲሰራ አይተዋል፡፡ በእርግጥም የሰዎች እምነትና ትዕግሥት የአገልግሎታቸው ምሥጢር ነው፡፡

    9. አንድን ሰው ስኬታማ በሆነ መልኩ ለመከተል ስንፍናን፣ ዳተኝነትንና መለገምን ማሸነፍ አለብህ፡፡

    በእምነትና በትዕግሥትም የተስፋውን ቃል የሚወርሱትን እንድትመስሉ እንጂ ዳተኞች እንዳትሆኑ፥ ተስፋ እስኪሞላ ድረስ እያንዳንዳችሁ ያን ትጋት እስከ መጨረሻ እንድታሳዩ እንመኛለን።

    ዕብራውያን 6፡11-12

    ስንፍና በርካቶች መከተል የማይችሉበት ምክንያት መሆኑን ታምናለህ? መከተልና መማር የማይፈልጉ ሰነፍ ሰዎችን ቃላት ሰምቻለሁ፡፡ ሁሉም የሚሉት፡-

    አቤት! የእግዚአብሔር ጸጋ በሕይወትህ ላይ አለ፡፡

    እንዲህ ይላሉ፣ እነዚህ ቤተክርስቲያኖች እንዲኖሩህ መሆኑ እግዚአብሔር ለአንተ የሰጠህ ጸጋ ነው፡፡

    አቤት እያሉ ያደንቃሉ፣ ነገሮችን የምታከናውንበት መንገድ ደስ ይለኛል፡፡ የተሰጠህ ጸጋ ነው፡፡ አንተ ያለህ ጸጋ የለኝም፡፡ ጥሪዬ አይደለም ይላሉ፡፡ አዎን የእግዚአብሔር ጸጋ በሥራ ላይ መሆኑ እውነት ሊሆን ይችላል፡፡ በአብዛኛው ግን ሰዎች እንዲሁ አዲስን ነገር ለመማር እጅግ ሰነፍ ስለሆኑ ነው! ሲሰሩ የሚያዩአቸውን ሃሳቦችና መርሆች ለመተግበር መጨነቅ አይችሉም፡፡

    በእርግጥ ከአንተ ቀድሞ እንዳለ ሰው ለመሆን ብዙ ኃይል ይጠይቃል፡፡ የአንድን መሪ ምሥጢራት ለማግኘትና እነርሱን ለመቅዳት ብዙ ሰአትና ያላሰለሰ ጥረት ይጠይቃል፡፡ ሰነፍ ሰዎች በመከተል ጥበብ ስኬታማ ሊሆኑ አይችሉም፣ አይሆኑምም፡፡

    ምዕራፍ 3

    ለመከተል ጥበብ የሚያስፈልጉ ሰባት ቁልፎች

    1. ሰዎችን በአስተምህሮቶቻቸው ውይም በአድራጎቶቻቸው ተከተላቸው፡፡

    ቴዎፍሎስ ሆይ፥ ኢየሱስ የመረጣቸውን ሐዋርያትን በመንፈስ ቅዱስ ካዘዛቸው በኋላ እስከ ዐረገበት ቀን ድረስ፥ ያደርገውና ያስተምረው ዘንድ ስለ ጀመረው ሁሉ መጀመሪያውን ነገር ጻፍሁ፤

    የሐዋርያት ሥራ 1፡1

    አንድ ሰው የሚያስተምራቸው ነገሮችና የሚያደርጋቸው ነገሮች እኩል ጠቃሚ ናቸው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስን ለመከተል አስተምህሮቶቹንም ያደረጋቸውንም ነገሮች መከተል አለብህ፡፡ እያንዳንዱ ወንጌል የክርስቶስን አስተምህሮዎች፣ እንዲሁም ያደረጋቸውን ነገሮች ታሪክ ያካተተ ነው፡፡ የክርስቶስ አስተምህሮቶች በቀይ ሲሆኑ ያደረጋቸው ደግሞ በጥቁር ተፅፈዋል፡፡

    እነዚህ ሁለት ገጽታዎች እጅግ የተለያዩ ግን ደግሞ እጅግ ወሳኝ መሆናቸውን መረዳት ጠቃሚ ነው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ያላስተማራቸው በርካታ ነገሮች አሉ፡፡ በእርግጥም እያደረገ ያለው ምን እንደሆነ ሳያብራራ ያደርጋቸው የነበሩ በርካታ ነገሮች አሉ፡፡ ለዚህ ነው ቴዎፍሎስ ኢየሱስ ያደርግና ያስተምር ከነበረው እንዲማር የተመከረው፡፡

    2. አስተምህሮቶቻቸውን በመከተል የእግዚአብሔርን ሰዎች ተከተል፡፡

    አንዳንድ ሰዎች የሚያውቁትን በማስተማር ሥጦታ እንዳላቸው መረዳትህ አስፈላጊ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት አንዳንድ ሰዎች ብዙ የሚያካፍሏቸው ትምህርቶች፣ አስተምህሮዎች፣ ሕግጋት እና ሃሳቦች ይኖሯቸዋል፡፡ ለምሳሌ ታላቅ ነብይና የፈውስ አገልጋዩ ኬነት

    Enjoying the preview?
    Page 1 of 1