Discover millions of ebooks, audiobooks, and so much more with a free trial

Only $11.99/month after trial. Cancel anytime.

የአገልግሎት ጥበብ
የአገልግሎት ጥበብ
የአገልግሎት ጥበብ
Ebook292 pages1 hour

የአገልግሎት ጥበብ

Rating: 3 out of 5 stars

3/5

()

Read preview

About this ebook

ጥበብን ማዳበር ችሎታን ወይንም ክህሎትን ማዳበር ማለት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር ሞገስ አዋቂ ለሆኑት ትመጣለች ይላል። የአገልግሎትም ሥራ ትልቅ ችሎታን ይጠይቃል። ይህ « የአገልግሎት ጥበብ » በመባል የወጣው አዲስ መጽሐፍ የአገልግሎትን ሥራ መስራት ለሚፈልጉ በጣም አስፈላጊ ነው። ስለ አገልግሎት ትክክለኛና ትክክል ያልሆነ አስተሳሰብ ምን እንደሆነ፣የአገልግሎት ሥራ ምንድን ነው፣ በአገልግሎቱ ሥራ ውስጥ ካንተ የሚጠበቀው ምንድን ነው እና የአገልጋይነቴን ተግባር እንዴት ነው የምወጣው የሚሉትን በማብራራት በግልጽ ያስቀምጠዋል። በአገልግሎት ውስጥ ያንተን ተግባር እንዴት መሥራት እንዳለብህ ያሳስብሃልን? ይህ ልዩ የሆነ የዳግ ሂዋ

Languageአማርኛ
Release dateJul 27, 2016
ISBN9781613954515
የአገልግሎት ጥበብ
Author

Dag Heward-Mills

Bishop Dag Heward-Mills is a medical doctor by profession and the founder of the United Denominations Originating from the Lighthouse Group of Churches (UD-OLGC). The UD-OLGC comprises over three thousand churches pastored by seasoned ministers, groomed and trained in-house. Bishop Dag Heward-Mills oversees this charismatic group of denominations, which operates in over 90 different countries in Africa, Asia, Europe, the Caribbean, Australia, and North and South America. With a ministry spanning over thirty years, Dag Heward-Mills has authored several books with bestsellers including ‘The Art of Leadership’, ‘Loyalty and Disloyalty’, and ‘The Mega Church’. He is considered to be the largest publishing author in Africa, having had his books translated into over 52 languages with more than 40 million copies in print.

Related to የአገልግሎት ጥበብ

Related ebooks

Reviews for የአገልግሎት ጥበብ

Rating: 3 out of 5 stars
3/5

5 ratings0 reviews

What did you think?

Tap to rate

Review must be at least 10 words

    Book preview

    የአገልግሎት ጥበብ - Dag Heward-Mills

    ካልተገለፀ በቀር፣ በዚህ መፅሐፍ ውስጥ ያሉ ጥቅሶች ሁሉ የተወሰዱት በ1954 ዓ.ም. ከታተመው የአማርኛ መፅሐፍ ቅዱስ  ነው፡፡

    ይህ መጽሐፍ የሁለት ከዚህ በፊት የታተሙ መጽሐፎች ጥምር ሆኖ በአዲስ መልኩ በ2007 ፣ታተም፡፡ እነዚህም ፡- የቤተክርስቲያን ሥራ ሕግጋት እና የሙሉ ጊዜ አገልግሎት ሕግጋት መቢል አርዕስት ከጸሐፊው መጽሐፎእ ተተርጉመው በ2004 የታተሙ ነበሩ፡፡

    Find out more about Dag Heward-Mills

    Healing Jesus Crusade

    Write to: evangelist@daghewardmills.org

    Website: www. daghewardmills.org

    Facebook: Dag Heward-Mills

    Twitter: @EvangelistDag

    ላይትሃውስ ቻፕል ኢንተርናሽናል

    መ.ሳ ቁጥር 15134

    አዲስ አበባ

    ኢትዮጵያ

    ይህንን መፅሐፍ በሙሉም ሆነ በከፊል ያላሳታሚው ፈቃድ ማባዛት የተከለከተለ ነው፡፡

    Table of Contents

    ምዕራፍ 1. እግዚአብሔር በጸጋው ስጦታና በመጥራቱ አይጸጸትም

    ምዕራፍ 2. የገሀዳዊው አለም ሥራና በአገልግሎት ሥራ ውስጥ ያለው ልዩነት

    ምዕራፍ 3. ጥሪህን ይዘህ በሚገባው አካሄድ መቀጠል ማለት ምን ማለት ነው

    ምዕራፍ 4. አስር ዓይነት ሠራተኞች

    ምዕራፍ 5. የተልእኮህ አስር ሕግጋት

    ምዕራፍ 6. እንዴት መልካም እረዳት መሆን እንደሚቻል

    ምዕራፍ 7. የምደባ ሕግጋት

    ምዕራፍ 8. ዋጋህ እንዴት እንደሚመዘን

    ምዕራፍ 9. በሥራህ እንዴት መደሰት እንደምትችል

    ምዕራፍ 10. የሕይወት ዘመን ሥራህን እንዴት ማግኘት እንደምትችል

    ምዕራፍ 11. የማይጠቅሙ ሥራዎችን ማስወገድ

    ምዕራፍ 12. ከአለቃህ ጋር እንዴት እንደምትግባባ

    ምዕራፍ 13. የሙሉ ጊዜ ወይስ የትርፍ ጊዜ አገልግሎት፣ እንዴት መምረጥ ይቻላል?

    ምዕራፍ 14. የሙሉ ጊዜ የአገልግሎት ወቅት ተቀበል

    ምዕራፍ 15. ስለ ሙሉ ጊዜ አገልግሎት ሰባት የተሳሳቱ አመለካከቶች

    ምዕራፍ 16. የሙሉ ጊዘአ አገልግሎትን ለምን መምረጥ አለብህ

    ምዕራፍ 17. እግዚአብሔር ራስሴን በሙላት እንድሰጥ እንዴት እንደጠራኝ

    ምዕራፍ 18. የሙሉ ጊዜ አገልግሎት ሚስጢራዊ ዓላማዎች

    ምዕራፍ 19. ከመሉ ጊዜ አገልግሎት ጀርባ ያለ መርህ

    ምዕራፍ 20. ለሙሉ ጊዜ አገልግሎት የሚቀርቡ የተሳሳቱ ምክንያቶች

    ምዕራፍ 21. በሙሉ ጊዜ አገልግሎት ውስጥ ለመሆን ትክክለኛ ምክንያቶች፡፡

    ምዕራፍ 22. ለሙሉ ጊዜ አገልገሎት ያለህን ዝግጁነት እንዴት መገምገም አለብን

    ምዕራፍ 23. የሙሉ ጊዜ አገልግሎትን መምረጥ ማለት ምን ማለት ነው

    ምዕራፍ 24. ሙሉ ጊዜ አገልግሎት ልዩ ጥቅም

    ምዕራፍ 25. ለምን አንዳንዶች የአገልግሎቱን ሥራ ተዉ

    ምዕራፍ 1

    እግዚአብሔር በጸጋው ስጦታና በመጥራቱ አይጸጸትም

    የመጀመሪያው ጥሪ

    የእግዚአብሔርም ቃል ወደ አማቴ ልጅ ወደ ዮናስ እንዲህ ሲል መጣ። ተነሥተህ ወደዚያች ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፥ ክፋታቸውም ወደ ፊቴ ወጥቶአልና በእርስዋ ላይ ስበክ።

    ዮናስ 1፡1-2

    ሁለተኛው ጥሪ

    የእግዚአብሔርም ቃል ሁለተኛ ወደ ዮናስ እንዲህ ሲል መጣ። ተነሥተህ ወደዚያች ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፥ የምነግርህንም ስብከት ስበክላት አለው።

    ዮናስ 3፡1-2

    እግዚአብሔር የምሕረት አምላክ ነው! ትታዘዘው ዘንድ ሁለተኛ ዕድል ይሰጥሃል፡፡ ዮናስ እግዚአብሔርን ይሰማና ይታዘዝ ዘንድ ሁለተኛ እድል የተሰጠው ሰው ዓይነተኛ ምሳሌ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ግን አንድ እድል ብቻ ሊኖረን ይችላል፡፡

    የሁለተኛ እድል አምላክ

    ምናልባት እግዚአብሔር ሁልጊዜም በቤተክርስቲያን እንድታገለግለው ይፈልግ ይሆናል፡፡ ለዚህም ምክንያት ፈጥሮሃል፡፡ ምናልባትም ከእግዚአብሔር ጥሪ ስትሸሽ ቆይተሀል፡፡ ነገር ግን ዳግመኛ እግዚአብሔር እየተናገረህ ነው፡፡ እግዚአብሔር ለዮናስ ሁለት ጊዜ ተናግሮታል፡፡ በመጀመሪያውና በሁለተኛው ጥሪ መካከል ዮናስ በርካታ ልምምዶችን አሳልፏል፡፡ በሕይወት ማዕበል ተመትቷል፡፡ በአሳ ነባሪ ሆድ ውስጥ ቆይቷል፡፡ ምናልባት እግዚአብሔርን ለመስማት ጆሮህን የምታቀናው በብዙ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ካለፍህ በኋላ ነው፡፡

    ምናልባት ይህን መጽሐፍ በእጅህ በያዝህበት ጊዜ እንኳ፤ እግዚአብሔር በቤቱ እንድታገለግል ሁለተኛ እድል እየሰጠህ ይሆናል፤ ለመጨረሻው ፍልሚያ ሰራዊቱን ትቀላቀል ዘንድ ጊዜው አሁን ነው

    ጥሪው አልተለወጠም

    በዮናስ ሕይወት ውስጥ የመጀመሪያውና ሁለተኛው ጥሪ ተመሳሳይ መሆኑን መገንዘብ ትችላለህ፡፡ በሁለቱም ጥሪዎች ዮናስ ተመሳሳይ መልእክት ይዞ ወደዚያችው ከተማ (ነነዌ) እንዲሄድ ተልኳል፡፡ እግዚአብሔር ስለ ጸጋ ስጦታዎቹና ስለ መጥራቱ አይጸጸትም (ሮሜ 11፡29)፡፡

    እግዚአብሔር በጊዜ ብዛት ሐሳቡን አይቀይርም፡፡ በከፍተኛ ማዕበልና በአሳ ነባሪ ሆድ ውስጥ በጭንቀት ካለፍህ በኋላ እንኳ አሁንም ሊጠቀምብህ ይችላል፡፡ እግዚአብሔር ከጠራህ ምናልባት አስር ዓመታት አልፈው ይሆናል፡፡ አሁንም ግን ልትታዘዘው አልረፈደብህም፡፡ ሁለተኛ እድል የሚሰጠውን አምላክ በማገልገሌ ደስተኛ ነኝ፡፡

    የእግዚአብሔርን ጥሪ መቀበል ማለት በራስህ አንተ ልትሆን የማትችለውን ነገር መሆንን መቀበል ማለት ነው፡፡ ጴጥሮስ በራሱ ሊሆን የማይችለውን ይሆን ዘንድ ኢየሱስ ጥሪ አቀረበለት - የሰዎች አጥማጅ ይሆን ዘንድ፡፡

    ወደ አገልግሎት መምጣት ማለት በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ታላቅ አስተዋጽዖ ማድረግ ማለት አይደለም፡፡ በአንተ ማንነት ምንም ነገር አይመሠረትም፡፡ አገልግሎቱንም ችላ በማለትህ ምንም የሚከስም ነገር እንዳለ አታስብ፡፡ ሁላችንም በሌሎች ልንተካ የምንችልና አላፊ ሰዎች ነን፡፡

    ለእውነት እንጂ በእውነት ላይ ምንም ለማድረግ አንችልምና።

    2ኛ ቆሮ 13፡8

    ይህ ቃል በእግዚአብሔር ቃል እውነት ላይ ምንም ዓይነት አሉታዊ ነገር ማድረግ እንደማንችል ያስተምረናል፡፡ ታላላቅ ስሕተቶቻችን የወንጌልን እውነት አያግዱትም፡፡ ጥሪያችንን ክፉኛ መዘንጋታችንም የእግዚአብሔርን ሰራዊት የአሸናፊነት ብቃት አይቀለብሰውም፡፡ ለአገልግሎት ሥራ መጠራታችን ትልቅ እድል ነው፡፡ የሥራው ተሳታፊ መሆንም ክብር ነው፡፡ እናም ለእግዚአብሔር ያልተለመደን ነገር ለማድረግ ማሰብህን የምታቆምበት ወቅት ላይ ትገኛለህ፡፡

    በአግልግሎት ውስጥ መሆን ማለት ስለ እግዚአብሔር የምትማርበትና ምሕረቱንም የምትቀበልበት የትሕትና ልምምድ ነው፡፡ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እንዲከተሉትና በመጨረሻም አንድ ነገር ሊያደርጋቸው እንደሚፈልግ ነገራቸው፡፡ በሙሉ ጊዜ አገልግሎት ውስጥ እግዚአብሔር የሚጠቀምብህ ዕቃ ሆነህ ትሠራለህ፡፡

    ኢየሱስም፦ በኋላዬ ኑና ሰዎችን አጥማጆች እንድትሆኑ አደርጋችኋለሁ አላቸው።

    ማርቆስ. 1፡17

    በሙሉ ጊዜ አገልግሎት ውስጥ በአእምሮ መታደስ ትሁት ሊያደርጉህ በሚችሉ ብዙ ልምምዶች አማካኝነት ትለወጣለህ፡፡ የሙሉ ጊዜ አገልግሎት ወደ እግዚአብሔር የምትቀርብበት ጉዞ ጅማሮ ነው፡፡ በየጊዜው እየተለወጥህ ትሁት እየሆንህ ትመጣለህ፡፡ ይህ በሌሎች ዘንድ የተናቀ ሥራ፣ ከክርስቲያኖች ጋር በሚኖርህ ግንኙነት ዝቅ እንድትል በማድረግ የተሻልህ ሰው ወደ መሆን ያመጣሀል! በተጨማሪም የሙሉ ጊዜ አገልግሎት ምን እንደሆነ ከማይረዱ ከውጪ ሰዎች ጋር በሚኖርህ ግንኙነት ከእግዚአብሔር ጋር ወደ ጠለቀ ኅብረት እንድትገባ ከፍተኛ ግፊት ያሳድርብሃል፡፡

    የሙሉ ጊዜ አገልግሎት ያልሆነው

    በሙሉ ጊዜ አገልግሎት ውስጥ መሆን ማለት ኢየሱስ ‘‘ሰዎችን አጥማጅ'' አደረገህ ማለት ነው፡፡ ነገር ግን በአገልግሎት ውስጥ ገንዘብ ተከፋይ ሆንህ ማለት የሙሉ ጊዜ አገልጋይ ሆንህ ማለት አይደለም

    ደመወዝህን የሚከፍልህ ባንክ ሳይሆን ቤተክርስቲያን መሆኗ ለብቻው የሙሉ ጊዜ አገልጋይ አያደርግህም፡፡ የሙሉ ጊዜ አገልግሎት ሁሉንም የሚጠቀልል ደረጃ ሲሆን ጌታን ፈጽመህ የምትከተልበት መንገድ ነው፡፡ እርሱን መከተል ማለት ሰፊና ከዚህ በታች ያሉትን ነጥቦች የሚያካትት ነው፡፡ የሙሉ ጊዜ አገልግሎት ሌሎች ሥራዎችን እንደመቀየር ቀላል አይደለም፤ ይልቁኑ የሕይወት ዘመን መሰጠት ነው፡፡ ማንነትህ ሁሉ በእርሱ ተውጦ በእግዚአብሔር ኃይል የምትለወጥበት ነው፡፡

    የሙሉ ጊዜ አገልግሎት ከሚከተሉት አንዱንም አይደለም፡

    የሙሉ ጊዜ አገልግሎት ምቹ የሥራ አማራጭ አይደለም፡፡

    የሙሉ ጊዜ አገልግሎት ቀላል የሥራ አማራጭ አይደለም፡፡

    የሙሉ ጊዜ አገልግሎት የአረጋውያን መጦሪያ አይደለም፡፡

    የሙሉ ጊዜ አገልግሎት ሠራተኛን በድጋሚ ማሰማሪያ አይደለም፡፡

    የሙሉ ጊዜ አገልግሎት የእናቶችና ሕፃናት መጠለያ አይደለም፡፡

    የሙሉ ጊዜ አገልግሎት የጉብዝና እድሜያቸውን ሌሎች ነገሮች ላይ አጥፍተው መጨረሻቸው ሲቀርብ  የሚመጡ ሰዎች መሸሸጊያ አይደለም፡፡

    የሙሉ ጊዜ አገልግሎት የማስመሰያ የሥራ ዕቅድ አይደለም፡፡ አንዳንድ ሰዎች ሙሉ ጊዜ አገልግሎትን መደበኛ ደመወዝ ማግኛ በማድረግ በጎን ደግሞ የራሳቸውን ንግድ ያጧጡፋሉ፡፡ ንግድ ንግድ ነው፤ አገልግሎት ደግሞ አገልግሎት!

    የሙሉ ጊዜ አገልግሎት መደበኛ ሥራ ያላቸው ሰዎች የሚከውኑት የትርፍ ጊዜ እንቅስቃሴ አይደለም፡፡

    የሙሉ ጊዜ አገልግሎት ዓለማዊ ምኞታቸውን ማሳካት የሚፈልጉ ሰዎች የሚጠቀሙበት መሰላል አይደለም፡፡

    የሙሉ ጊዜ አገልግሎት የድህነት ቅነሳ መርሐ-ግብር  አይደለም፡፡ አንዳንድ ጊዜ አገልግሎት የተሻለ ገንዘብ ማግኛ መንገድ ተድርጎ ይቆጠራል፡፡

    የሙሉ ጊዜ አገልግሎት ከገሐዱን ዓለም ሞያ ወደ ቤተክርስቲያን ማሸጋገሪያ አይደለም፡፡ በገሐዱ ዓለም የሒሳብ ሹም ነበርህ ማለት ቤተክርስቲያንም ስትመጣ የሒሳብ ሹም ትሆናለህ ማለት አይደለም፡፡

    የሙሉ ጊዜ አገልግሎት የደመወዝ ምንጭህን መለወጫ ማለት አይደለም፡፡

    የሙሉ ጊዜ አገልግሎት የዕረፍት ጊዜ ሥራ አይደለም፡፡ ተማሪዎች በዕረፍት ጊዜያቸው የሚሰማሩበትም መስክ አይደለም

    በሙሉ ጊዜ አገልግሎት ዙሪያ ያሉ መምታታቶች

    በአሁኑ ጊዜ ሰዎችን በተለያየ ሁኔታ የወረሩ የተለመዱ መምታታቶች አሉ፡፡ የሙሉ ጊዜ አገልጋዮችም ታዲያ ከእነዚህ ፈጽመው የጸዱ አይደሉም፡፡ የሙሉ ጊዜ አገልጋዮች ከሚምታቱባቸው ሐሳቦች ከብዙ በጥቂቱ የሚከተሉት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

    የሙሉ ጊዜ አገልጋይ በመሆኔ ለየት ያልሁ ነኝ፡፡

    በሙሉ ጊዜ አገልግሎት ስለተሰማራሁ ጥሩ ደመወዝ ይኖረኛል፡፡

    በሙሉ ጊዜ አገልግሎት ውስጥ ስለተሰማራሁ የመንፈሳዊውን ደረጃ ጣሪያ ነክቻለሁ፡፡ እናም ተጨማሪ መንፈሳዊ መሻሻሎች አያስፈልጉኝም፡፡

    በሙሉ ጊዜ አገልግሎት በመሰማራቴ ከትርፍ ጊዜ አገልጋዮች የተሻልሁ ነኝ፡፡

    በሙሉ ጊዜ አገልግሎት ስለተሰማራሁ ወደ ውጭ አገራት እጓዛለሁ፡፡

    በሙሉ ጊዜ አገልግሎት ስለተሰማራሁ ትልቅ ቤት ይኖረኛል፡፡

    በሙሉ ጊዜ አገልግሎት ስለተሰማራሁ መኪና ይኖረኛል፡፡

    በሙሉ ጊዜ አገልግሎት ስለተሰማራሁ ሀብታም እሆናለሁ

    በሙሉ ጊዜ አገልግሎት ስለተሰማራሁ መንፈሳዊ እሆናለሁ፡፡

    በሙሉ ጊዜ አገልግሎት ስለተሰማራሁ የተሻለ የትዳርና የቤተሰብ ሕይወት ይኖረኛል፡፡

    በሙሉ ጊዜ አገልግሎት ስለተሰማራሁ ለጸሎት፣ ለአምልኮና ቃሉን ለማጥናት በቂ ጊዜ ይኖረኛል፡፡

    በሙሉ ጊዜ አገልግሎት ስለተሰማራሁ እግዚአብሔር በእኔ በጣም ደስ ይለዋል፡፡

    በሙሉ ጊዜ አገልግሎት ስለተሰማራሁ በፍቅር እጓዛለሁ፡፡

    በሙሉ ጊዜ አገልግሎት ስለተሰማራሁ ፍርድ ይቀልልኛል፡፡

    በሙሉ ጊዜ አገልግሎት ስለተሰማራሁ የተቀባሁና የተጠበቅሁ ነኝ፡፡

    በሙሉ ጊዜ አገልግሎት ስለተሰማራሁ ልጆቼ በጥሩ ሁኔታ ያድጋሉ፡፡

    በሙሉ ጊዜ አገልግሎት ስለተሰማራሁ ምንም ዓይነት ሁኔታ ከመንግሥተ ሰማይ አያስቀረኝም፡፡

    በሙሉ ጊዜ አገልግሎት ስለተሰማራሁ ታማኝ ነኝ፡፡

    ከላይ የተጠቀሱት ነገሮች ሁሉ የግድ እውነት ሊሆኑ አይችልም፡፡ አብዛኛዎቹ ለአንተ እውን ላይሆኑ ይችላሉ፡፡ በቀላልና በፈጣን ሁኔታም የሚሳኩ አይደሉም፡፡ ስለሆነም በሙሉ ጊዜ አገልግሎት ውስጥ የእግዚአብሔር አጀንዳዎች ይፈጸሙ ዘንድ እግዚአብሔርን መፈለግ ይገባሃል፡፡

    ምዕራፍ 2

    የገሀዳዊው አለም ሥራና በአገልግሎት ሥራ ውስጥ ያለው ልዩነት

    ልዩነት አለ

    ነገር ግን ለእኔ መገዛትንና ለምድር ነገሥታት መገዛትን ያውቁ ዘንድ ይገዙለታል ሲል ወደ ሸማያ መጣ።

    2ኛ ዜና 12፡8

    ሮብዓም በእግዚአብሔር ላይ ባመፀ ጊዜ ነቢዩ አስደንጋጭ መልእክትን አመጣ፡፡ ይህም እግዚአብሔርን በማገልገልና የዓለምን ነገሥታት በማገልገል መካከል ያለውን ልዩነት ማሳየት ነበር፡፡

    እግዚአብሔርን በማገልገልና ዓለምን በማገልገል መካከል ልዩነት አለ፡፡ በዚህ ጠፊ ዓለም ውስጥ ሀብትን ማጋበስ ከፍ ካለው ከእግዚአብሔር ጥሪ ጋር አይተካከልም፡፡  ለአንድ ሟች ሰው ታላቅ ክብር የሚባለው እውነተኛ መሠረቶች ያላትን ከተማ መገንባት  ነው፡፡ ብዙዎች ጊዜያዊና አላፊ የሆነውን በመገንባት ሕይወታቸውን ያሳልፋሉ፡፡ ይህ ማለት ደግሞ ብዙ ሰዎች ጊዜያቸውን የሚያሳልፉት የአሸዋ ቤተ መንግሥት በመገንባት ነው ማለት ነው፡፡

    ፈርዖን ማን ነው?

    ፈርዖን የሰይጣን ‘‘አምሳያ'' ነው፡፡ ግብፅ የዓለም፣ እስራኤል ደግሞ የእግዚአብሔር ሕዝብ ‘‘ተምሳሌቶች'' ናቸው፡፡ ፈርዖን የእግዚአብሔርን ሕዝብ በከባድ ሥራ በማስጨነቅ ታላላቅ ከተሞችን እንዲገነቡ አደረጋቸው፡፡ ይህም ዛሬ በገሃዱ ዓለም ያለውን የሥራ ሁኔታ በግልጽ ያሳያል፡፡

    በዓለም ውስጥ ጊዜ እየጠፋ ያለው ከተሞችን በመገንባት ነው፡፡ ታዲያ በመጨረሻ በሞት ስናልፍ ለዚህች ዓለም ልንተወው የምንችለው ነገር ውብ ሕንፃዎችንና የሕንፃ ቅርጾችን ብቻ ይሆናል፡፡

    የዚህ ዓለም ሥራ አድካሚ፣ አስጨናቂ እንዲሁም ብዙ ላባችንን የምናፈስበት ነው፡፡ የምንገነባው የዚህችን ዓለም ታላላቅ ከተሞች እንደሆነ ሳናስተውል ስንለፋና ስንኳትን እንኖራለን፡፡ የኒው ዮርክ፣ ፓሪስ፣ ለንደን፣ አክራ፣ ሌጎስ እና ናይሮቢ ከተሞች የተገነቡት ቀን ከሌት ጠንክረው በሠሩ ሰዎች ላብ ነው፡፡

    እነዚህ ሰዎች አልፈዋል፡፡ ሆኖም ታላላቆቹ ከተማዎች ግን አሁንም ድረስ አሉ፡፡ የሕይወት ዘመናቸው ሲጠቀለል የሰዎቹ ሚና ለታላላቆቹ ከተሞች እድገት አስተዋጽዖ ማድረግ ብቻ ነው፡፡ ሰይጣን የዚህን ዓለም የመንግሥታት ክብር አሳይቶ ለኢየሱስ የተናገረውን አትርሳ፡

    ዲያብሎስም፣ ይህ ሥልጣን ሁሉ ክብራቸውም ለእኔ ተሰጥቶአል ለምወደውም ለማንም እሰጠዋለሁና ለአንተ እሰጥሃለሁ፤

    ሉቃስ. 6፡4

    ይህ የሚያሳየን በዚህ ዓለም ከተሞች ላይ ሰይጣን ሥልጣን እንዳለው ነው፡፡ ዲያብሎስ የዚህ ዓለም አምላክ ተብሏል (2ኛ ቆሮ. 4፡4)፡፡ ለሰው ልጆች ከባድ ሥራን የሚሰጥ እንዲሁም የዚህን ዓለም ከተሞች ይገነቡ ዘንድ የሚመራ ሰይጣን ነው፡፡

    ክርስቲያኖችም ከግንበኛው ሰራዊት ጋር ተቀላቅለው እነዚህን ታላላቅ ከተሞች በመገንባቱ ሂደት ውስጥ የበኩላቸውን እየተወጡ ነው፡፡

    በግብፅም ዮሴፍን ያላወቀ አዲስ ንጉሥ ተነሣ።እርሱም ሕዝቡን። እነሆ፥ የእስራኤል ልጆች ሕዝብ ከእኛ ይልቅ በዝተዋል በርትተውማል፤ እንዳይበዙ፥ ሰልፍም በተነሳብን ጊዜ ጠላቶቻችንን አግዘው እንዳይወጉን ከምድሪቱም እንዳይወጡ፥ ኑ እንጠበብባቸው አለ።በብርቱ ሥራም ያስጨንቁአቸው ዘንድ ግብር አስገባሪዎችን ሾመባቸው ለፈርዖንም ፊቶምንና ራምሴን ጽኑ ከተሞች አድርገው ሠሩ።ነገር ግን እንዳስጨነቁአቸው መጠን እንዲሁ በዙ፥ እጅግም ጸኑ ከእስራኤልም ልጆች የተነሣ ተጸይፈዋቸው ነበር።ግብፃውያንም የእስራኤልን ልጆች በመከራ ገዙአቸው።

    ዘጸአት. 1፡8-13

    ፈርዖን ግብፅን እንደተቆጣጠራት ሁሉ፣ ሰይጣንም ዓለምንና ከተሞቿን ተቆጣጥሯል፡፡ የዚህች ዓለም መምታታትና ግራ መጋባት ቀስ በቀስ እየጨመረ መጥቶ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሰው ለዚህ ነው፤ በገንዘብ ተቋማት፣ በባንኮችና በሌሎች የገሐዱ ዓለም ድርጅቶች ውስጥ ተቀጥረህ የምትሠራ ከሆነ ለፈርዖን ሲሠሩ ከነበሩትሥና የአሸዋ ቤተ መንግስት ለመገንባት ብዙ ጫና፣ ውጥረትና ላብ ካፈሰሱት እስራኤላውያን ጋር ልትመሳሰል ትችላለህ፡፡ ሙሴ የእስራኤል ሕዝብ ነፃ ይወጣ ዘንድ ለእግዚአብሔር ጥያቄ አቅርቧል፤ ወደ ሙሉ ጊዜ አገልግሎት መግባት የሚፈልግ ማንም ሰው ከዓለም ሥርዓት የመለየት ሐሳብ ሲጠናወተው ራሱን ያገኘዋል፡፡ የሙሉ ጊዜ አገልግሎት ለእግዚአብሔር የሚቀርብ አገልግሎት ነው! የግብፅን አገር ለቅቆ ወደ ምድረ በዳ መግባትና ለጌታ መሥዋዕትን እንደማቅረብ፣ ብሎም የመገናኛውን ድንኳን እንደ መትከል ነው፡፡

    እግዚአብሔር ሕዝቡ  የመገናኛ ድንኳን በመትከልና እርሱን በማምለክ ጊዜያቸውን እንዲያሳልፉ ይፈልጋል፡፡ በእርግጥ ከዓለም ሥርዓት መላቀቅ

    Enjoying the preview?
    Page 1 of 1