Discover millions of ebooks, audiobooks, and so much more with a free trial

Only $11.99/month after trial. Cancel anytime.

የመስማት ጥበብ
የመስማት ጥበብ
የመስማት ጥበብ
Ebook242 pages1 hour

የመስማት ጥበብ

Rating: 3.5 out of 5 stars

3.5/5

()

Read preview

About this ebook

በእግዚአብሔር ፍጹም ፈቃድ ውስጥ ከመሆን ይበልጥ ጠቃሚ የሆነ ርዕስ የለም፡፡ የወንጌል አገልጋዮችን የሚለያቸው አንድ ነገር ቢኖር የእግዚአብሔርን ድምፅ በትክክል የመስማት ችሎታቸው ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስን ወደ እግዚአብሔር ፍጹም ፈቃድ መከተል እንዴት ጠቃሚ ነገር ነው፡፡ በእግዚአብሔር ፍጹም ፈቃድ ውስጥ ስትሆን ታብባለህ ደግሞም ለእግዚአብሔር ማድረግ የምትፈልገውን ሁሉ ከግብ ታደርሳለህ፡፡ ይህ የዳግ ሂዋርድ ሚልስ ድንቅ መፅሐፍ በሕይወትህና በአገልግሎት ላይ ትልቅ ተፅዕኖ ያደርጋል፡፡

Languageአማርኛ
Release dateJul 27, 2016
ISBN9781613954492
የመስማት ጥበብ
Author

Dag Heward-Mills

Bishop Dag Heward-Mills is a medical doctor by profession and the founder of the United Denominations Originating from the Lighthouse Group of Churches (UD-OLGC). The UD-OLGC comprises over three thousand churches pastored by seasoned ministers, groomed and trained in-house. Bishop Dag Heward-Mills oversees this charismatic group of denominations, which operates in over 90 different countries in Africa, Asia, Europe, the Caribbean, Australia, and North and South America. With a ministry spanning over thirty years, Dag Heward-Mills has authored several books with bestsellers including ‘The Art of Leadership’, ‘Loyalty and Disloyalty’, and ‘The Mega Church’. He is considered to be the largest publishing author in Africa, having had his books translated into over 52 languages with more than 40 million copies in print.

Related to የመስማት ጥበብ

Related ebooks

Reviews for የመስማት ጥበብ

Rating: 3.6666666666666665 out of 5 stars
3.5/5

3 ratings1 review

What did you think?

Tap to rate

Review must be at least 10 words

  • Rating: 5 out of 5 stars
    5/5
    መጽሐፉን በጣም ወድጄዋለሁ ደራሲውን እግዚአብሔር ይባርከው መጽሐፎቹን እነብኩ ነው ተባረኩ

Book preview

የመስማት ጥበብ - Dag Heward-Mills

ፍጹም የሆነውና ፍጹም ያልሆነው የእግዚአብሔር ፈቃድ

የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።

ሮሜ 12፥2

የእግዚአብሔር ፈቃድ ፍጹም የሆነ እና ፍጹም ያልሆነ በመባል ሊገለፅ ይችላል። ፍጹም ያልሆነ የእግዚአብሔር ፈቃድ ፍጹም ያልሆነ የተባለው እውነተኛ የሆነውን የእግዚአብሔር ፈቃድ የሚመስል ሲሆን እውነታው ግን እግዚአብሔር የማይፈልገው ስለሆነ ነው።

ፍጹም የሆነው የእግዚአብሔር ፈቃድ ምሉዕ፣ የበሰለና ጢም ብሎ የሞላው ፈቃዱ ነው። ፍጹም ያልሆነው ፈቃዱ ምንም እንኳ የመጀመሪያ ምርጫው ባይሆንም ሰዎች ያደርጉት ዘንድ የሚፈቅድላቸው ነገር ነው።

ፍጹም የሆነው የእግዚአብሔር ፈቃድ

1. ፍጹም የሆነው የእግዚአብሔር ፈቃድ እግዚአብሔር በዋናነት እንድትሆንበት የሚሻው ስፍራ ነው። ፍጹም በሆነው ፈቃዱ ውስጥ ስትሆን እግዚአብሔር ባንተ ይደሰታል፤ ስምህም ሲወሳ ይረካል።

2. ፍጹም በሆነው የእግዚአብሔር ፈቃድ ውስጥ የላቀውን ስፍራ ታገኛለህ፣ ከቀደመው የእግዚአብሔር እቅድ ጋር ትጋጠማለህ፡፡

3. ፍጹም በሆነው የእግዚአብሔር ፈቃድ ውስጥ ስትሆን እግዚአብሔር አንተን የሠራበትንና ያስፈለግህበትን ነገሮች በፍጹምነት ታሟላለህ።

ፍጹም ያልሆነው የእግዚአብሔር ፈቃድ

1. እግዚአብሔር ልጆቹ ፍጹም ወዳልሆነው የእግዚአብሔር ፈቃድ እንዲገቡ የሚተዋቸው በአመፀኝነታቸው ምክንያት እንዲሁም ለእነርሱ ያለውን ፍጹምና የቀደመውን እቅዱን ሲገፉ ነው።

2. ፍጹም ባልሆነው የእግዚአብሔር ፈቃድ ውስጥ በምትሆንበት ጊዜ እግዚአብሔር በእርግጥ አልተደሰተብህም፤ እየቻለህ፣ እየታገሰህና ንስሐ እንድትገባ ጊዜ እየሰጠህ ነው፡፡

3. ፍጹም ባልሆነው የእግዚአብሔር ፈቃድ ውስጥ ሆነህ የእግዚአብሔር ሞገስ ያለህ ብትመስልም ለጌታ ያለህ አገልግሎት ምሉዕ አይደለም፤ እግዚአብሔር በሕይወትህ ያለውን ዋና እና የቀደመ አላማውንም እየፈፀምክ አይደለም።

4. ፍጹም ያልሆነው የእግዚአብሔር ፈቃድ ተገቢ ያልሆነው ስፍራህ ነው፡፡ ለሥራውም የማትበቃ ነህ።

ፍጹም ከሆነው የእግዚአብሔር ፈቃድ ፍጹም ወዳልሆነው መንሸራተት

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እግዚአብሔር ምንም እንኳ የእርሱ ፈቃድ ባይሆንም ሰዎች የወደዱትን እንዲያደርጉ ሲተዋቸው እናያለን። ብዙውን ጊዜ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ፍጹም ለሆነው ለእግዚአብሔር ፈቃድ በዓመፅና በጥላቻ የተሞሉ ነበሩ። ይህን ጊዜ አፋጣኝ ፍርድ በእነርሱ ላይ ከማድረግ ይልቅ ፍጹም ባልሆነው (ባልተመረጠው፣ ባልተገባው፣ ተቀባይነት በሌለው እና ተስማሚ ባልሆነው) ፈቃዱ ውስጥ እንዲባዝኑና ለዓመፃቸው ተመጣጣኝ ቅጣት እንዲቀበሉ ያደርጋቸዋል!

በዚህ መጽሐፍ ውስጥ እግዚአብሔር እንዴት ለሕዝቡ ንጉሥ እንዲኖራቸው እንደፈቀደና ንጉሦቻቸውን ግን እንዴት ሕዝቡን ለመቅጣት እንደተጠቀመባቸው ታያለህ። እንዲበሉና እንዲበለፅጉ ፈቅዶላቸው ነገር ግን ክሳትንና ግራ መጋባትን ላከባቸው። ጣዖታትን እንዲሠሩ ፈቀደላቸው ኋላ ግን አጠፋቸው። ነቢዩን ተልዕኮውን እንዲፈፅም ከተወው በኋላ ይገስጸው ዘንድ አህያ ላከበት።

እግዚአብሔር ሰዎች ፍጹም ባልሆነው ፈቃዱ ውስጥ ገብተው ይባዝኑ ዘንድ መፍቀዱ ከራሱ ማንነት ጋር የሚጣረስ አይደለም። ለአመፃቸው፣ ለግትርነታቸውና ፍጹም የሆነውን ፈቃዱን ለመግፋታቸው ምላሽ ነው። በመጨረሻም ሰዎች ሁሉ ተገቢ የሆነውን፣ የሚመጥነውን እና ለየት ያለ የእግዚአብሔርን ፍርድ ይቀበላሉ!

አንዳንድ ሰዎች ይህንን ፍጹም ያልሆነ ፈቃዱን ይሁንታ የተሰጠበት የእግዚአብሔር ፈቃድ ይሉታል። ብዙ የወንጌል አገልጋዮች በዚህ ፍጹም ባልሆነው የእግዚአብሔር ፈቃድ ውስጥ ይንቀሳቀሳሉ። ሌሎቹ ደግሞ በሕይወት ዘመናቸው በሙሉ ፍጹም ባልሆነው እግዚአብሔር ፈቃድ ውስጥ ይኖራሉ።

ፍጹም ባልሆነው የእግዚአብሔር ፈቃድ ውስጥ የሚመላለሱ ሰዎች ሁሉም ነገር መልካም እንደሆነ ይሰማቸዋል። አገልግሎታቸው ያብባል በሚሠሩትም ነገር ሁሉ ላይ የእግዚአብሔር ሞገስ ያለ ይመስላል። ሆኖም ግን መትረፍረፍና የሚታይ ስኬት እግዚአብሔር ባንተ ለመደሰቱ ማስረጃ አይሆንም።

ብዙዎቻችን በሚታይ ነገር ማለትም ሰዎች በረከቶች ብለው በሚጠሯቸው ነገሮች እንታለላለን። ገንዘብና መትረፍረፍ ግን መቼም እግዚአብሔር በአንተ ለመደሰቱ ምልክት ሆኖ አያውቅም። ዲያብሎስም ለሚያገለግሉት ገንዘብን ይሰጣል። ሰይጣን ኢየሱስን ወድቆ ቢሰግድለት ዓለሙን ሁሉ ሊሰጠው እንደሚችል ነግሮታል።

ልትፈልገው የተገባው የእግዚአብሔር መገኘት እና የመንፈስ ቅዱስን ድምፅ እንጂ የገንዘብ በረከት ወይም ማናቸውም ውጫዊ ነገር አይደለም።

ከአንድ አገልጋይ ጋር ስትገናኝም መፈለግ ያለብህ የእግዚአብሔር መገኘት ከእርሱ ጋር መሆኑን ነው። የእግዚአብሔር ድምፅና ቃል የሚገኝበት አገልጋይ መሆኑን ልብ ማለት ያስፈልግሃል።

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ፍጹም ከሆነው የእግዚአብሔር ፈቃድ ሰዎች ፍጹም ወዳልሆነው ሲንሸራተቱ እናያለን። እግዚአብሔርም ፍጹም ባልሆነው ፈቃዱ ውስጥ ያለውን ሕዝብ እየባረከ ይመስላል በእውነት ግን አልተደሰተባቸውም።

እስቲ ፍጹም ወዳልሆነው የእግዚአብሔር ፈቃድ ውስጥ የገቡ ሰዎችን በምሳሌነት እንመልከት፦

1. እስራኤል ንጉሥ እንዲኖረው በመጎትጎት ፍጹም ወዳልሆነው የእግዚአብሔር ፈቃድ ውስጥ ገብቷል።

እስራኤል ንጉሥ ይኖራቸው ዘንድ ፍጹም የሆነ እና የጊዜው የእግዚአብሔር ፈቃድ አልነበረም። ነገር ግን እግዚአብሔር ፈቀደላቸው፣ ለሳሙኤል ደግሞ በግሉ ሕዝቡ እንደናቀው ነግሮታል።

ንጉሥ ይኖራቸው ዘንድ ፍጹም ፈቃዱ ባይሆንም እንኳ ፈቅዶላቸዋል። በቀጣይም የሆነውን ስትመለከት ነገሩ ለመልካም አልሆነም፤ የእስራኤልም ልጆች በንጉሦቻቸው አማካኝነት ከፍተኛ ስቃይ ደርሶባቸዋል።

እግዚአብሔር አንዳንድ ነገሮችን ፈቅዶ ስናይ በምናየው መታለል አያስፈልግም፡፡ እውነተኛ የሆነው የእግዚአብሔር ልብ የሚገለጠው በታማኝነት ወደ እርሱ ለቀረበው ሕዝቡ ነው።

በሕዝብ ፊት ሁሉም የሚስማማበትን ነገር እየተናገርን የልባችንን ግን ሌላ ቦታ መግለጥ ሁሌም የምናደርገው ነገር ነው። ስለዚህ እግዚአብሔር በአንድ ነገር ላይ ያለውን ትክክለኛ የልብ ሐሳብ መፈለግን መማር አለብህ፡፡

እግዚአብሔር ሳሙኤልን ንጉሥ እንዲሾምላቸው ሲፈቅድ አዝኖ ነበር። ሕዝቡ እንደገፋው አውቋል። ሕዝቡ የሳሙኤልን ልጆች እንደምክንያት እንደተጠቀሙበትም ያውቃል። እግዚአብሔር በጥያቄአቸው ተስማማ ሆኖም ግን ለእስራኤል ቀና አልሆነለትም። እግዚአብሔር የማይወደውን ነገር በሕይወትህ እንዲሆን ሲፈቅድ ጠንቀቅ በል።

የእስራኤልም ሽማግሌዎች ሁሉ ተሰብስበው ወደ ሳሙኤል ወደ አርማቴም መጡና፦ እነሆ፥ አንተ ሸምግለሃል፥ ልጆችህም በመንገድህ አይሄዱም አሁንም እንደ አሕዛብ ሁሉ የሚፈርድልን ንጉሥ አድርግልን አሉት።የሚፈርድልንም ንጉሥ ስጠን ባሉት ጊዜ ነገሩ ሳሙኤልን አስከፋው ሳሙኤልም ወደ እግዚአብሔር ጸለየእግዚአብሔርም ሳሙኤልን አለው፦ በእነርሱ ላይ እንዳልነግሥ እኔን እንጂ አንተን አልናቁምና በሚሉህ ነገር ሁሉ የሕዝቡን ቃል ስማ።

1ኛ ሳሙኤል 8፡4-7

2. የሞአብ ንጉሥ በተደጋጋሚ ለበለዓም ይተነብይለት ዘንድ በጠየቀው ጊዜ በለዓም ፍጹም ከሆነው ከእግዚአብሔር ፈቃድ ውስጥ ወጣ::

እግዚአብሔር በለዓም ከሞአቡ ንጉሥ ከባላቅ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት እንዲፈጥር እንደማይፈልግ ግልጥ አድርጐለታል። ሆኖም ግን በለዓም ባላቅ ያቀረበለትን ገንዘብ ፈለገ። እግዚአብሔርንም ንጉሡን ይናገር ዘንድ እንዲፈቅድለት ለመነ። በመጨረሻም ጌታ እንዲሄድ ፈቀደለት። እንዴትም ሊያናግራቸው እንደሚገባ ምክርን ሰጠው። ዘመናዊ ክርስቲያኖች ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ እንደሆነ ይናገራሉ። ይህ ክፍል የተጻፈው እኛ በአመፃ ስንሞላ እግዚአብሔር እንዴት የራሳችንን መሻት እንድናደርግ ሊፈቅድልን እንዲሚችል ለማስጠንቅቅ ነው።

እግዚአብሔርም ወደ በለዓም መጥቶ፦ እነዚህ በአንተ ዘንድ ያሉ ሰዎች እነማን ናቸው? አለው። በለዓምም እግዚአብሔርን፦ የሞዓብ ንጉሥ የሴፎር ልጅ ባላቅ። እነሆ፥ ከግብፅ የወጣ ሕዝብ የምድርን ፊት ሸፈነ፥ አሁንም ና እርሱንም ርገምልኝ ምናልባት እወጋው አሳድደውም ዘንድ እችል እንደ ሆነ ብሎ ወደ እኔ ልኮአል አለው። እግዚአብሔርም በለዓምን፦ ከእነርሱ ጋር አትሂድ የተባረከ ነውና ሕዝቡን አትረግምም አለው። በለዓምም ሲነጋ ተነሥቶ የባላቅን አለቆች፦ ከእናንተ ጋር እሄድ ዘንድ እግዚአብሔር አልፈቀደምና ወደ ምድራችሁ ሂዱ አላቸው። የሞዓብ አለቆች ተነሡ፥ ወደ ባላቅም መጥተው፦ በለዓም ከእኛ ጋር ይመጣ ዘንድ አልፈቀደም አሉት። ባላቅም ደግሞ ከፊተኞች የበዙና የከበሩ ሌሎችን አለቆች ሰደደ።ወደ በለዓምም መጥው፦ የሴፎር ልጅ ባላቅ፦ ክብርህን እጅግ ታላቅ አደርገዋለሁና፥ የተናገርኸውንም ሁሉ አደርግልሃለሁና እባክህ፥ ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ ምንም አይከልክልህ እባክህ፥ ና፥ ይህን ሕዝብ ርገምልኝ አለ ብለው ነገሩት። እግዚአብሔርም ወደ በለዓም በሌሊት መጥቶ። ሰዎቹ ይጠሩህ ዘንድ መጥተው እንደ ሆነ፥ ተነሣ ከእነርሱም ጋር ሂድ ነገር ግን የምነግርህን ቃል ብቻ ታደርጋለህ አለው።በለዓምም ሲነጋ ተነሣ፥ አህያይቱንም ጭኖ ከሞዓብ አለቆች ጋር ሄደ።እርሱም ስለ ሄደ እግዚአብሔር ተቈጣ የእግዚአብሔርም መልአክ ሊቋቋመው በመንገድ ላይ ቆመ። እርሱም በአህያይቱ ላይ፥ ሁለቱም ሎሌዎቹ ከእርሱ ጋር ነበሩ።

ዘኁልቁ 22፥9-22

3. የእስራኤል ልጆች በፍቅረ ነዋይ ሲያዙ ፍጹም ከሆነው የእግዚአብሔር ፈቃድ ወጡ።

ፈጥነውም ሥራውን ረሱ፥ በምክሩም አልታገሡም። በምድረ በዳም ምኞትን ተመኙ፥ በበረሃም እግዚአብሔርን ተፈታተኑት። የለመኑትንም ሰጣቸው ለነፍሳቸው ግን ክሳትን ላከ።

መዝሙር 106፥13-15

የእስራኤል ልጆች እንደ ዘመነኛዋ ቤተክርስቲያን በአፍቅሮተ ነዋይ ተያዙ። በዚያን ጊዜ እንደሆነውም ምድራዊ መሻታቸውን ለመፈፀም ሲሉ ቃሉን የሚያጣምሙትን የአፍቅሮተ ነዋይ ሰባኪዎችን ሰጣቸው።

በአፍቅሮተ ነዋይ ላይ ያለማቋረጥ የሚሰጠው ስብከት ከአጓጊነቱ ጋር ተያይዞ ስብከቱን የእግዚአብሔር ፍጹም ፈቃድ አስመስሎታል። በጉባኤ ውስጥ በጣም በርካታ ታዳሚዎች መገኘታቸውና በዚህ በአፍቅሮተ ነዋይ ዙሪያ የሚያጠነጥኑ አገልግሎቶች ላይ የሚታየው ጊዜያዊ ስኬት እግዚአብሔር በነገሩ የተደሰተ ያስመስለዋል።

ጥንትም የእስራኤላውያንን የአፍቅሮተ ነዋይ ጥያቄአቸውን የመለሰላቸው ቢመስልም ፍጹም ባልሆነው ፈቃዱ ውስጥ ነበሩ፤ ምክንያቱም በአፍቅሮተ ነዋይ ስለተያዙ ቀጥቷቸዋልና። የቀጣቸውም በነፍሳቸው ክሳት ነበር። እግዚአብሔር በፍጹም ፈቃዱ መሠረት ሄደው ቢሆን ኖሮ ባልቀጣቸው ነበር።

እግዚአብሔር ልጆቹ እንዲበለፅጉ ይፈልጋል፤ ነገር ግን ባልተገባ መንገድና ላልተገባ አላማ እንዲሆን አይደለም። ጠቡ ከብልፅግና ጋር ስላልሆነም ብልፅግናን ለልጆቹ ሰጥቷል። ዛሬ እግዚአብሔር ለቤተክርስቲያን ብልፅግናን እየሰጣት ነው፣ ነገር ግን የነፍስ ክሳት፣ በመንፈሳዊነት ስር አለመስደድ፣ በሽታ፣ የትዳር ፍቺ፣ ምግባረ ብልሹነት እንዲሁም ግብረ ሰዶማዊነት አብሮ ተያይዞ የመጣ ይመስላል። ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲያደርግልን ግድ የምንለውን ነገር ልንጠነቀቅ ይገባል፤ ምክንያቱም አጥብቀን ከምንሻው የራሳችን መንገድ ጋር ተያይዞ የሚመጣው ቅጣት ምናልባት ደስ የማያሰኘን ሊሆን ይችላልና።

4. የእስራኤል ልጆች አሮን የጥጃ ጣዖት እንዲሰራላቸው ባስገደዱት ጊዜ ፍጹም ወዳልሆነው የእግዚአብሔር ፈቃድ ውስጥ ገብተዋል::

የእስራኤል ልጆች አሮንን ከፊታቸው ሆኖ የሚመሯቸውን ጣዖት እንዲሰራላቸው ግድ ማለታቸው የራሳቸውን መንገድ መከተል የፈለጉ እንደሆነ ያሳያል።

አሮን የጥጃውን ጣዖት ሲሰራላቸው፣ እግዚአብሔር የጣዖት አምልኮን የሚጨምር አዲስ ሃይማኖት ጀምሯል ብለው አስበው መሆን አለበት። አሮን በሥራቸው በመሳተፉ እስራኤላውያን አዲሱ እምነታቸውን እግዚአብሔር እንዳፀደቀላቸው በመቁጠር ጨፍረዋል።

ምንም እንኳ የሚመራቸው አሮን የእግዚአብሔር ሰው ቢሆንም ነገር ግን በእግዚአብሔር ፍጹም ፈቃድ ውስጥ አልነበሩም። በእግዚአብሔር ፍጹም ፈቃድ ውስጥ ባለ መገኘታቸውም የቅጣት ምላሻቸውን ለመቀበልም ብዙ ጊዜ አልቆዩም።

ሕዝቡም ሙሴ ከተራራው ሳይወርድ እንደ ዘገየ ባዩ ጊዜ፥ ወደ አሮን ተሰብስበው፦ ይህ ከግብፅ ምድር ያወጣን ሰው ሙሴ ምን እንደ ሆነ አናውቅምና ተነሥተህ በፊታችን የሚሄዱ አማልክት ሥራልን አሉት። አሮንም፦ በሚስቶቻችሁ በወንዶችና በሴቶች ልጆቻችሁም ጆሮ ያሉትን የወርቅ ቀለበቶች ሰብራችሁ አምጡልኝ አላቸው። ሕዝቡም ሁሉ በጆሮቻቸው ያሉትን የወርቅ ቀለበቶች ሰብረው ወደ አሮን አመጡለት።

ከእጃቸውም ተቀብሎ በመቅረጫ ቀረጸው፥ ቀልጦ የተሠራ ጥጃም አደረገው እርሱም፦ እስራኤል ሆይ፥ እነዚህ ከግብፅ ምድር ያወጡህ አማልክትህ ናቸው አላቸው።

ዘፀአት 32፥1-4

በኮሬብም ጥጃን ሠሩ፥ ቀልጦ ለተሠራ ምስልም ሰገዱ።ሣርም በሚበላ በበሬ ምሳሌ ክብራቸውን ለወጡ።ታላቅ ነገርንም በግብጽ፥ ድንቅንም በካራን ምድር፥ ግሩም ነገርንም በኤርትራ ባሕር ያደረገውን ያዳናቸውንም እግዚአብሔርን ረሱ።እንዳያጠፋቸው ቍጣውን ይመልስ ዘንድ የተመረጠው ሙሴ በመቅሠፍት ጊዜ በፊቱ ባይቆም ኖሮ፥ ያጠፋቸው ዘንድ ተናገረ።

መዝሙር 106፥19-23

የአሮንም ልጆች ናዳብና አብዩድ በየራሳቸው ጥናውን ወስደው እሳት አደረጉበት፥ በላዩም ዕጣን አኖሩበት፥ በእግዚአብሔርም ፊት እርሱ ያላዘዛቸውን ሌላ እሳት አቀረቡ።እሳትም ከእግዚአብሔር ፊት ወጥቶ በላቸው፥ በእግዚአብሔርም ፊት ሞቱ።

ዘሌዋውያን 10፥1-2

6. አብርሃም ከአጋር ወራሽ የሚሆነውን ልጅ ለማግኘት ወደ አጋር ሲገባ ፍጹም ወዳልሆነው የእግዚአብሔር ፈቃድ ውስጥ ገብቷል::

አብርሃም ከአጋር ልጅን ሲወልድ በርካታ ችግሮችን ወደ ህይወቱ ጠርቷል። እግዚአብሔር ከአጋር ልጅ እንዲኖረው አልነገረውም ነበር፤ ነገር ግን ከአጋር በመውለድ አብርሃም ሚስቱን ማስደሰት ፈለገ።

እግዚአብሔር አብርሃም አጋርን ሲያገባት ዝም ብሎታል። ብሎም የአጋርንም ልጅ ባርኮታል። ይሁን እንጂ ያ የእግዚአብሔር ፍጹም ፈቃድ አልነበረም። እግዚአብሔር አብርሃምን ከሳራ

Enjoying the preview?
Page 1 of 1