Discover millions of ebooks, audiobooks, and so much more with a free trial

Only $11.99/month after trial. Cancel anytime.

እረኛ መሆን ምን ማለት ነው
እረኛ መሆን ምን ማለት ነው
እረኛ መሆን ምን ማለት ነው
Ebook209 pages1 hour

እረኛ መሆን ምን ማለት ነው

Rating: 4.5 out of 5 stars

4.5/5

()

Read preview

About this ebook

እረኛ የሚለውን ቃል ስንሰማ በሃሳባችን የሚመጣው « በግ « ነው። በጎች በእረኞች የሚያስፈልጋቸው ጥገኛ የሆኑ ፍጡሮች ናቸው። እረኛ በጎችን የሚንከባከብና የሚወድ እነርሱንም የሚመራ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር እኛ የእርሱ የማሰማርያው በጎችን እንደሆንን ያሳየናል። ኢየሱስ ደቀመዝሙሩን ጴጥሮስን ለጌታ ፍቅር ማረጋገጫ እንዲሆን በጎቼን መግብልኝ ብሎታል። እረኛ መሆን ትልቅ ሥራ ነው። በእግዚአብሔር ግብረኃይል ውስጥ በመካተት በጎችን መጠበቅ ትልቅ መታደል ነው። በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ዳግ ሂዋርድ ሚልስ የእግዚአብሔርን ህዝብ የመጠበቅ ታላቅ ሥራ ውስጥ እንዴት አድርገን መግባት እንዳለብን ይጋብዘናል፣ይገፋፋናል፣ያሳየናል። ካማረው

Languageአማርኛ
Release dateJul 27, 2016
ISBN9781613954645
እረኛ መሆን ምን ማለት ነው
Author

Dag Heward-Mills

Bishop Dag Heward-Mills is a medical doctor by profession and the founder of the United Denominations Originating from the Lighthouse Group of Churches (UD-OLGC). The UD-OLGC comprises over three thousand churches pastored by seasoned ministers, groomed and trained in-house. Bishop Dag Heward-Mills oversees this charismatic group of denominations, which operates in over 90 different countries in Africa, Asia, Europe, the Caribbean, Australia, and North and South America. With a ministry spanning over thirty years, Dag Heward-Mills has authored several books with bestsellers including ‘The Art of Leadership’, ‘Loyalty and Disloyalty’, and ‘The Mega Church’. He is considered to be the largest publishing author in Africa, having had his books translated into over 52 languages with more than 40 million copies in print.

Related to እረኛ መሆን ምን ማለት ነው

Related ebooks

Reviews for እረኛ መሆን ምን ማለት ነው

Rating: 4.666666666666667 out of 5 stars
4.5/5

3 ratings0 reviews

What did you think?

Tap to rate

Review must be at least 10 words

    Book preview

    እረኛ መሆን ምን ማለት ነው - Dag Heward-Mills

    እረኛ መሆን ምን ማለት ነው

    ዳግ ሂዋርድ ሚልስ

    ካልተገለፀ በቀር፣ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ያሉ ጥቅሶች ሁሉ የተወሰዱት በ1954 ዓ.ም. ከታተመው የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ነው።

    Find out more about Dag Heward-Mills

    Healing Jesus Crusade

    Write to: evangelist@daghewardmills.org

    Website: www. daghewardmills.org

    Facebook: Dag Heward-Mills

    Twitter: @EvangelistDag

    ISBN: 978-1-61395-464-5

    ላይትሃውስ ቻፕል ኢንተርናሽናል

    መ.ሳ ቁጥር 15134

    አዲስ አበባ

    ኢትዮጵያ

    ይህ መጽሐፍ በ2003፣ የትርፍ ጊዜ አገልግሎት በሚል ርእስ ታትሞ ነበር። ትርጉም፡- ሬቨረንድ አማኑኤል ቶማስ ። በዚህ ሁለተኛ እትም ፣እረኛ መሆን ምን ማለት ነው በሚለው ርእስ በ2007 ዓ.ም ታተመ።

    መታሰቢያነቱ

    ለመጋቢ ሪቻርድ አዬ እና መጋቢ ጁኤል ኦቡኦቢሳ

    ለዓመታት ታማኝነታችሁ፣ መሰጠታችሁና ብርቱ ሥራችሁ አመሰግናለሁ።

    ይህንን መጽሐፍ በሙሉም ሆነ በከፊል ያላሳታሚው ፈቃድ ማባዛት የተከለከለ ነው።

    ማውጫ

    ምዕራፍ 1

    እረኛ ማለት ምን ማለት ነው

    ብዙ ሕዝብም ባየ ጊዜ፥ እረኛ እንደ ሌላቸው በጎች ተጨንቀው ተጥለውም ነበርና አዘነላቸው።

    ማቴዎስ 9፡36

    እረኛ ማን ነው በሚለው ማብራሪያ ላይ ልንታገል አይገባም። እረኛ በጉን በመንከባከብ እና በፍቅር የሚመራ ነው። እረኛ ማለት በጐችን እንዲንከባከብ እግዚአብሔር የጠራው ማለት ነው።

    በመፅሐፍ ቅዱስ ላይ የእግዚአብሔር ሕዝብ በጐች ሲባሉ እርሱም እነዚህን በጐችን ለመንከባከብ እረኞች የሚባሉ ሰዎችን ያስነሣል።

    እግዚአብሔር እንደ እባቦች፣ እንሽላሊቶች፣ ድመቶች እና ውሾች ስብስብ አይደለም የሚመለከተን። አይደለም! ፍቅር፣ እንክብካቤ እና ምሪት እንደሚፈልጉ እንደ በጐች ስብስብ ነው የሚያየን።

    ብዙ ሕዝብም ባየ ጊዜ፥ እረኛ እንደ ሌላቸው በጎች ተጨንቀው ተጥለውም ነበርና አዘነላቸው።

    መዝሙር 95፡6-7

    ይህን መፅሐፍ የምፅፈው ምክንያቱ የእግዝአብሔርን መንጋ ለመንከባከብ ብዙ ሕዝብ መቀላቀል እንደሚችል አበክሬ ስለማምን ነው። የእግዚአብሔርን ሕዝብ የመንከባከብ ታላቅ ሥራ ተነስተን የምንቀላቀልበት ሰዓት ነው። እረኛ መሆን የምንግዜም እጅግ ታላቅ የሆነ ነገር ነው። ምክንያቱም ጌታችን ሕዝቡን ይወዳል እናም እንክብካቤ እና ምሪት እንደሚያስፈልጋቸው በጐችን ነው የሚያያቸው። እረኛ መሆን ትልቅ የሆነ ሥራ ነው። ለዛም ነው ለቤተክርስቲያን ራስ ለሐዋሪያው ጴጥሮስ የተሰጠ ሥራ የነበረው። አስታውስ! ኢየሱስ ጴጥሮስን ፍቅሩን በጐቹን ለመመገብ እና መንከባከብ እንዲያስመሰክር ነግሮት የነበረው። ጴጥሮስ ትወደኛለህ የምትወደኝ ከሆነ በጐችን መግብ።

    ምሳ ከበሉ በኋላም ኢየሱስ ስምዖን ጴጥሮስን። የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ ከእነዚህ ይልቅ ትወደኛለህን? አለው። አዎን ጌታ ሆይ፥ እንድወድህ አንተ ታውቃለህ አለው። ግልገሎቼን አሰማራ አለው።

    ደግሞ ሁለተኛ። የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ ትወደኛለህን? አለው። አዎን ጌታ ሆይ፥ እንድወድህ አንተ ታውቃለህ አለው።

    ጠቦቶቼን ጠብቅ አለው። ሦስተኛ ጊዜ። የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ ትወደኛለህን? አለው። ሦስተኛ። ትወደኛለህን? ስላለው ጴጥሮስ አዘነና። ጌታ ሆይ፥ አንተ ሁሉን ታውቃለህ፤ እንድወድህ አንተ ታውቃለህ አለው። ኢየሱስም፦ በጎቼን አሰማራ።

    ዮሐንስ 21፡15-17

    በሁሉም ቤተክርስቲያን ውስጥ ሁለት ዓይነት ሰዎች አሉ፤ በጐች እና እረኞች እረኛ ወይም በግ ነህ። እረኛ በመሠረቱ መጋቢ ነው። በእርግጥ በብዙ ቋንቋዎች ለእረኛ እና መጋቢ የተለየ ቃል የለም። እረኛ ለሚለው ቃል ሌላ ቃል ብንጠቀም መጋቢ አቻ ቃል ነው። እኔ እረኛ የሚለውን ቃል መጠቀም እመርጣለሁ ምክንያቱም መጋቢ ለሚለው ግልፅ የሆነ ትርጉም ስለሆነ ነው። እረኛ መሆን ማለት ሰዎችን እንደበግ ማየት አለብህ እናም እንደዛው ልትጐዳኛቸው ይገባል።

    ብዙ እንግዳ የሆኑ መጋቢ የሚለው ቃል ትርጉሞች አሉ እና ሁሉም መጋቢ ማን መሆን ወይም ምን ማድረግ እንዳለበት የራሱ የሆነ ሀሳብ አለው። ነገር ግን፣ እረኛ ነኝ ስትል ወዲያውኑ ሥራህ በጐችን መንከባከብ እንደሆነ ታውቃለህ። በግልፅም፣ እረኛ ከሆንክ የበግነት ባህሪይ የሌለውን መምራት የማይቻለውን፣ መማር የማይችለውን፣ እንክብካቤ ሊደረግለት የማይችለውን መንከባከብ አትችልም። በእንግሊዝኛው ቋንቋ መጋቢ የሚለው ቃል በብዛት የሚጠቀመው የእግዚአብሔር ሰው የእግዚአብሔር ወኪል በሚል ትርጉም ነው። ከዚህም የተነሣ ነቢያት፣ ሐዋሪያት፣ ዲያቆናት እና ሁሉም እግዚአብሔርን የሚወክል መጋቢ ይባላል። እረኛ የተለየ ሠራተኛ ሆኖ ለመንከባከብ ጊዜ ያለው፣ ለመውደድ ጊዜ ያለው፣ ለመመገብ ጊዜ ያለው እና በጐችን ለመሰብሰብ ጊዜ ያለው ነው።

    ከላይ የተጠቀሰውን ጥቅስ አስተውል እረኛ ካለመኖሩ የተነሣ በጐች ተበትነው ነበር። በጐች ያልተበተኑት ነብይ ካለመኖሩ የተነሣ አይደለም። በጐች ያልተበተኑት ወንጌል ሰባኪ ወይም ዲያቆን ስለሌለ አይደለም። በጐች የተበተኑት እረኛ ስለሌለ ነው። ብዙ ሰዎች እረኛ እንዲሆኑ እንደተጠሩ ጠንካራ እምነቴ ነው። ብዙ ሰዎች ፍቅራቸውን፣ ጊዜአቸውን ጉልበታቸውን ሌላውን ለመንከባከብ መስጠት ይችላሉ። ይህን ያወቁበት ምክንያት ብዙ ሰዎች እናት እና አባት ሲሆኑ ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተፈጥሮአዊ ክህሎት አላቸው። እረኛ መሆን ብዙ ማፍቀርን፣ መንከባከብን እና መምራትን ከማጠቃለሉ የተነሣ በጐች እረኛቸውን በመጨረሻ አባቴ ብለው ወደ መጥራት ይመጣሉ። አንድ ሰው በእረኛነት ቅባት ሲነሣ ሰዎች በዙሪያው ይሰበሰባሉ ምክንያቱም ሁሉም ሰው ፍቅርን፣ እንክብካቤን እና ምሪትን ስለሚፈልግ ነው።

    ለእግዚአብሔር ሕዝብ እንክብካቤ የሚያደርጉትን፣ የሚመግቡትን ስትገልፅ እረኛ የሚለውን ቃል መጠቀም ተማር ምክንያቱም ያን ናቸው እና። እራስህን እንደ እረኛ ስትገልጥ፣ የእረኛነት ሥራህ ላይ እንድታተኩር ያደርግሃል። ዛሬ አብዛኛው በጉን በመንከባከብ ማፍቀር እና ምሪት መስጠት የሚገባቸው ሰዎች አለማዊ መንግስት ከመሆናቸው የተነሣ ለዩኒቨርስቲ እንጂ ለቤተክርስቲያን የሚመቹ አልሆኑም።

    እረኛን ባንክ ውስጥ ከኮምፒውተር ጀርባ ተቀምጦ ብታየው፣ ወዲያው የምትጠይቀው የት ነው ፍየሎችህን እና በጐችህን የተውካቸው ነው? ምን እየሆኑ ነው? ማን እየተንከባከባቸው ነው? ዛሬ፣ አብዛኛው እረኛ በጐች እና ፍየሎቻቸውን ጥለው ከእረኝነት ፈፅሞ የተለየ ሥራ እየሠሩ የሚገኙት በገበያ ሥፍራ ነው። የእግዚአብሔርን ሕዝብ እንድንከባከብ እና እንድንመግብ የተሠጠንን ክብር አንቋሸነዋል። ይህንን መፅሐፍ አትወርውረው። እረኝነት በጣም አስፈላጊ የሆነ ሥራ ነው። የእግዚአብሔር ሥራ ነው። በቁም ነገር ያዘው። እረኛ ሆነህ ለእግዚአብሔር ሕዝብ እንክብካቤ ማድረግ ትችላለህ። ለእግዚአብሔር ደግሞ የሆነን ነገር ማድረግ ትችላለህ!

    የተቀበልንበት ጊዜ አለ አሁን ግን የምንሰጥበት ጊዜ ነው! የተማርንበት ጊዜ አለ አሁን ግን የምናስተምርበት ጊዜ ነው። ከሌሎች ምሪትን የተቀበልንበት ጊዜ አለ አሁን ግን ሌሎችን የምንመራበት ጊዜ ነው። እራስህን ለዚህ ለከበረው የእረኝነት፣ የአፍቃሪነት፣ ተንከባካቢነት እና ሰዎችን የማስተማር ሥራ ራስህን ስጥ። ክብር ነው። የትርፍ ጊዜ አገልጋይ እንኳ ብትሆን እረኛ መሆን ትችላለህ። ብዙ የትርፍ ጊዜ ሰዎች በአገልግሎት ውስጥ አሉ። አንተም ከተከበሩት የትርፍ ጊዜ ሰዎች እግዚአብሔርን እንደ እረኛ የሚያገለግሉት አንዱ መሆን ትችላለህ።

    በሙሉ ጊዜ አገልግሎት ውስጥ ካለህ እራስህን እንደ እግዚአብሔር ሰው ሳይሆን እንደ እረኛ አስብ። ይህ ጥሪህን በደንብ እንድትረዳው ይረዳሃል በማፍቀር፣ በመንከባከብ፣ በመምራት እና በማስተማር የእግዚአብሔር ስጦታ ተመላለስ፤ ለእግዚአብሔር ሕዝብ እረኛ ትሆናለህ። አስታውስ ኢየሱስ በጐችን በጣም ይወዳል። ስለ እኛ ሞቶልናል። በውድ ሁኔታ ቢያስብልን ነው። ማንኛውንም የእግዚአብሔርን መንጋ የሚንከባከብ በቀጥታ ወደ እግዚአብሔር ፍቅር ገብቷል ምክንያቱም ኢየሱስ መጋውን ያፈቅራል ሞቶለታል።

    የክፍል ቁጥራቸውን ጠላሁ።

    የተረዳሁት ነገር እነዚህ ወጣት ሴቶች (የሴቶች ማደሪያ ዶርም ነበርና) አልጋቸው ላይ ይገላበጡ ነበር ግማሾቹ ከወንድ ጓደኞቻቸው ጋር ነበሩ። ከጥቂት ጊዜ በኋላ ረብሻችን እንደምናቆም ነበር የሚያውቁት። በዚህ ሁኔታ ውስጥ የእግዚአብሔር መንፈስ ቢያዘን እንዴት እንደምጠቀምበት ትዕዛዝ ሰጠኝ።

    በጥቅል አትስበክ፣ የዶርም ቁጥራቸውን ጥራ እና ለጠራኸው ዶርም መልዕክቱን ተናገር ብሎ ሹክ አለኝ። ታዘዝኩኝ የዶርም ቁጥራቸውን በመስማታቸው በጣም ደነገጡ እያንዳንዱን የማለዳ ወንጌል ሰባኪዎች አራት ወይም አምስት ዶርም የሚሰብኩት ሰጠኋቸው። በጣም የሚደንቅ ነገር ነበር! ሰዎቹ የመተኛ ክፍላቸው ቁጥር በመጠራቱ በጣም ተደነቁ። በእነዚህ በሚጠሩ የመተኛ ክፍሎች ውስጥ ላሉ ሰዎች ከጨለማ ውስጥ ድምፅ ይመጣላቸው ጀመር።

    እያንዳንዱ እግዚአብሔር በግል እየተናገራቸው እንደሆነ አውቀው ነበር። በእርግጥ አንዳንዶቹ እጅግ በጣም ተናዳው ነበር።

    አንዳንዶቹ የወንድ ጓደኞቻቸው ዶርም ውስጥ አብራዋቸው ተኝተው ነበር። በግል እየመጣላቸው ያለውን ቃል ከመስማት በስተቀር ምንም እድል አልነበራቸውም።

    አስታውሳለሁ ለዚህ ምላሽ አንድ ሴት ከክፍሏ ወደ ታች እየሮጠች መጥታ እጆችዋን ከፍ አድርጋ ዛሬ ህይወቴን ለክርስቶስ መስጠት እፈልጋለሁ። አለች! ደግሞ መወሰድ እፈልጋለሁ!

    አንዳንዶቹ በጣም ተቆጥተው ነበር ነገር ግን አንዳንዶቹ ድነው ነበር!

    መፅሐፍ ቅዱስ ሲናገር፣

    ለድሆችም ወንጌል ይሰበካል፤ በእኔም የማይሰናከለው ሁሉ ብፁዕ ነው።

    ማቴዎስ 11፡6

    ለራስህአትስበክ

    በእግዚአብሔርሥራታፍራለህ?

    ታፍራለህ?

    ምዕራፍ 2

    የትርፍ ጊዜ አገልግሎትን እንዴት አገኘሁት

    ሁለት የአገልግሎት ዓለማትን አይቼአለሁ። እነርሱም የትርፍ ጊዜ አገልግሎት እና የሙሉ ጊዜ አገልግሎት ናቸው። ብዙ ጊዜ አገልጋዮች ልብ የሚሉት የሙሉ ጊዜ አገልግሎት ብቻ ነው። በዚህ መጽሐፍ ውስጥ፣ በትርፍ ጊዜ አገልግሎት ውስጥ በመሰማራት የአገልግሎትን ሥራ መሥራት እንደሚቻል እንድትረዳ ለማድረግ እሞክራለሁ።

    የትርፍ ጊዜ አገልጋይ ማለት መደበኛ ሥራውን የሠራ በኢየሱስ አገልግሎት ውስጥ በንቃት የሚሳተፍ ነው። የሙሉ ጊዜ አገልጋይ ደግሞ ሥራውን ሙሉ በሙሉ ትቶ ሙሉ ትኩረቱን በአገልግሎት ላይ ያደረገ ሰው ነው። በሙሉ ጊዜ አገልግሎት ውስጥ ያሉ ብዙ አገልጋዮች፣ የትርፍ ጊዜ አገልጋዮች በአገልግሎት ውስጥ የመካፈላቸው ሀሳብ ምቾት አይሰጣቸውም። የዚህም ምክንያት አገልግሎት ለጥቂት የተጠሩ የእግዚአብሔር ሰዎች እንደሆነ አድርገው ለማቆየት ስለሚፈልጉ ነው። አንዳንድ የሙሉ ጊዜ አገልጋዮች የትርፍ ጊዜ አገልጋዮች ለአገልግሎት ጠንካራ የሆነ (በገንዘብ ያልሆነ) አስተዋፅዎ ማድረግ ይችላሉ የሚለውን ሀሳብ መቀበል አይፈልጉም። ብዙ የሙሉ ጊዜ አገልጋዮች አባላቶቻቸው የገንዘብ ድጋፍ ሰጪዎች ብቻ ሆነው ቢቀሩ ደስ ይላቸዋል። እኔ የምሠራውን ሥራ መሥራት ከቻልክ፣ እኔን ምን ልዩ ያደርገኛል; ብለው ያስባሉ። መጋቢዎች እነርሱ ብቻ የአገልግሎት ሥራ በመሥራት የተለዩ ሰዎች እንደሆኑ እንዲሰማቸው ይፈልጋሉ። ለምን ተራው ሰው እኔ የምሠራውን ሥራ ይሠራል፣ ይላሉ እኔ (መጋቢው) የምሠራውን ከሠራ እኔን ምን ልዩ ያደርገኛል ብለው ይጠይቃሉ።

    ሌሎች አገልጋዮች ደግሞ ተራው ሰው የአገልግሎትን ሥራ መሥራት ይችላል ብለው አያምኑም። ጊዜው ኖሯቸው የመንጋቸውን ችግር መድረስ ይችላሉ?፣ ለድንገተኛ ጊዜ መድረስ ይችላሉ?፡ እንደኛ በሀይለኛ ሁኔታ ማገልገል ይችላሉ? ብለው የጠየቁኝ መጋቢዎች አሉ።

    ለእነኚህ ጥያቄዎች መልሱ በጣም ቀላል ነው - አዎ! ለብዙ ዓመታት በትርፍ ጊዜ አገልግሎት ውስጥ ነበርኩ እናም እንደሚቻል በተግባር አይቼዋለሁ።

    ይህን መጽሐፍ እየጻፍኩ ያለሁት በመቅደስ ውስጥ እግዚአብሔርን ብቻ ከሚጠብቁ የሙሉ ጊዜ ካህናት ልማዳዊ አስተሳሰብ ሌላ አማራጭ ላስተዋውቅህ ነው። የትርፍ ጊዜ አገልግሎት ለቤተክርስቲያን ዕድገት ወሳኝ ነገር ነው። በዚህ ዓለም ያልተለመደ ዕድገት ያመጡ አብያተ ክርስቲያናት የትርፍ ጊዜ አገልጋዮችን የመጠቀምን መርህ ተጠቅመዋል። ይህ ታላቁን ተልእኮ ለመፈጸም ዋነኛ ነገር እንደሆነ አምናል ሁ። ይህ አለም በጥቂት ካህናት እና መጋቢዎች በምንም ዓይነት አናሸንፍም፣ ሁሉም ሰው መሳተፍ አለበት። ብዙ ሰዎች በከፍተኛ የአገልግሎት ደረጃ ላይ መሳተፍ አለባቸው። በቤተክርስቲያን ውስጥ የትርፍ ጊዜ አገልግሎት መነቃቃት አለበት።

    የትርፍ ጊዜ መጋቢ የሚባል ነገር አለ፣ ያም፣ መደበኛ ሥራውን ከአገልግሎት ጋር አጣምሮ የሚሠራ ማለት

    Enjoying the preview?
    Page 1 of 1