Discover millions of ebooks, audiobooks, and so much more with a free trial

Only $11.99/month after trial. Cancel anytime.

የኢየሱስ ደም፣ የደሙ ኃይል
የኢየሱስ ደም፣ የደሙ ኃይል
የኢየሱስ ደም፣ የደሙ ኃይል
Ebook86 pages34 minutes

የኢየሱስ ደም፣ የደሙ ኃይል

Rating: 3.5 out of 5 stars

3.5/5

()

Read preview

About this ebook

መጽሐፍ ቅዱስ ስለተለያዩ የደም ዓይነቶች ይናገራል፤ የፍየሎች ደም፣የበጎች ደም፣የእርግቦች ደም! እንዲሁም መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር ካለ ደም ሥርየት የለም ይላል። በመሆኑም እነዚህ የተለያዩ የደም ዓይነቶች ኃጢያታችንን ያስወግዱልናልን? መልሱ ግልጽ የሆነ አይደለም ነው። ታዲያ ኃጢያታችን ሊያስወግድልን የሚችል ምንድ ነው? ከኢየሱስ ክርስቶስ ደም ሌላ ምንም የለም! ኃጢያታችን ሊያስወግድ እና ድነትን ሊሰጠን የሚችለው የኢየሱስ ደም ብቻ ነው። በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ስለኢየሱስ ክርስቶስ ደም ብዙ የተቀደሱ እውነታዎችን ታገኛለህ። የኢየሱስ ደም እንዴት ህይወት እንደሚሰጥና እንዴት ትልቅ ዋጋ ያለው እንደሆነም ትደርስበታለህ። እንዲሁም በመን

Languageአማርኛ
Release dateJul 27, 2016
ISBN9781613954287
የኢየሱስ ደም፣ የደሙ ኃይል
Author

Dag Heward-Mills

Bishop Dag Heward-Mills is a medical doctor by profession and the founder of the United Denominations Originating from the Lighthouse Group of Churches (UD-OLGC). The UD-OLGC comprises over three thousand churches pastored by seasoned ministers, groomed and trained in-house. Bishop Dag Heward-Mills oversees this charismatic group of denominations, which operates in over 90 different countries in Africa, Asia, Europe, the Caribbean, Australia, and North and South America. With a ministry spanning over thirty years, Dag Heward-Mills has authored several books with bestsellers including ‘The Art of Leadership’, ‘Loyalty and Disloyalty’, and ‘The Mega Church’. He is considered to be the largest publishing author in Africa, having had his books translated into over 52 languages with more than 40 million copies in print.

Related to የኢየሱስ ደም፣ የደሙ ኃይል

Related ebooks

Reviews for የኢየሱስ ደም፣ የደሙ ኃይል

Rating: 3.625 out of 5 stars
3.5/5

8 ratings0 reviews

What did you think?

Tap to rate

Review must be at least 10 words

    Book preview

    የኢየሱስ ደም፣ የደሙ ኃይል - Dag Heward-Mills

    ቃሎቹ እና የኢየሱስ ክርስቶስ ደም

    ከኢየሱስ ክርስቶስ የምንማራቸው ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ ስለኢየሱስ ክርስቶስ ልናጠና የምንችላቸው ብዙ ጉዳዮች አሉ! የእርሱን ሕይወት፣ ቤተሰቡን እና ስኬቶቹን ልናጠና እንችላለን፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስን በተመለከተ ሁለቱ አበይት ጉዳዮች ግን ቃሎቹ እና ደሙ ናቸው፡፡

    እጅግ ውድ ቃላት

    የኢየሱስ ቃላት የእግዚአብሔርን እውነቶች እና ጥበብ የያዙ መሆናቸው ከፍተኛ ዋጋ የሚሰጣቸው ናቸው፡፡

    የኢየሱስን ቃላት ከሁሉ ቃላት በላይ ማስቀመጥ አግባብነት አለው፡፡ በአሁኑ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የኢየሱስ ቃላት በተለይ በቀይ ተጽፈዋል፡፡

    ከዚህ ቀደም ውብ የሆኑት የኢየሱስ ቃላት በመጽሐፍ ቅዱስ ከሌሎቹ ቃላት ጋር ተደባልቀው ተጽፈው ነበር፡፡ ዘመናዊ መጽሐፍ ቅዱሶች ግን ለኢየሱስ ቃላት የሚገባውን ክብር ሰጥተዋል፡፡ በመሆኑም የኢየሱስን ቃላት ላቅ ያለ ስፍራ ተሰጥቶታል፡፡

    ቤተክርስቲያን በተሐድሶ ውስጥ በነበረችበት ወቅት ሰዎች ትኩረታቸውን ክርስቶስ በቀራኒዮ በሰራው ስራ ላይ አድርገው ነበር፡፡ ከዚህ ቀደም ባሉት ጊዜያት ትኩረቱ በክርስቶስ ማንነት ላይ ነበር፡፡ ከዛ በኋላ ባለው ዘመን ደግሞ ኢየሱስ በምድር ላይ ማለትም ከበረት እስከ መስቀል የነበረው ሕይወት ትኩረት ተሰጥቶታል፡፡ አሁን ደግሞ በኢየሱስ ክርስቶስ ደም ላይ ማተኮር ይኖርብናል፡፡

    ደስ የሚያሰኘው፣ በአሁኑ ወቅት የኢየሱስ ደም ያለው ልዩ ዋጋ እውቅና እያገኘ ነው፡፡ የኢየሱስ ደም የሚገባውን የተለየ ስፍራ እያገኘ ነው፡፡ የኢየሱስ ደም የሚገባውን የተለየ ስፍራ እያገኘ ነው፡፡

    እጅግ ውድ ደም

    ኃጢአታችን በኢየሱስ ቃላት ሊታጠብ አይችልም፡፡ ስማችን በሕይወት መዝገብ ላይ እንዲጻፍ ይህ የማይረባ ኃጢአተኛ ማንነታችን በኢየሱስ ደም መታጠብ አለበት፡፡ ኢየሱስ ቢሰብክም ቢያስተምርም እንኳ እኛን በደሙ ኃይል ከኃጢአት ነፃ ማውጣት ነበረበት፡፡ ያለ ደም መፍሰስ የኃጢአት ስርየት የለም። ኃጢአቶችን መሸፈን እንዲችል ደም መፍሰስ ነበረበት፡፡

    ስለኃጢአታችን ማን ይከፍልልናል።

    የእግዚአብሔር እውነተኛ ጥበብ በኢየሱስ ትምሕርቶች እንደሚገኙ ጥርጥር የለውም፡፡ ነገር ግን ስለኃጢአታችን ማን ይከፍልልናል። እኛ ከገሐነም እንድናመልጥ የሚያስፈልገውን ዋጋ ማን ይከፍልልናል። እኛ በኢየሱስ ክርስቶስ ደም ተዋጅተናል (ዳግመኛ ተገዝተናል)፡፡ እኛ የተዋጀነው በኢየሱስ ቃላት ሳይሆን በኢየሱስ ደም ነው፡፡ የተዋጀነው በበሬ እና በፍየል ደም ሳይሆን በኢየሱስ ደም ነው፡፡

    ስብከቱን አቁምና ደሙ እንዲፈስ ፍቀድ

    ኢየሱስ በሰላሳ አመቱ ስብከቱን አቁሞ ወደ መስቀሉ የሄደው ለምንድነው። የእግዚአብሔርን ቃል የመስበክንና የማስተማርን ተልዕኮውን ለምን በሌላ አገሮች አልቀጥለውም። ወደ ሶሪያ፣ ሊባኖስ፣ እንግሊዝ፣ ጀርመን፣ ኢራቅ፣ ኢራን፣ ሕንድ እና አፍሪካ ሊጓዝ አይችልም ነበርን። በርግጥ ይቻል ነበር! ሕይወቱን በመስቀል ላይ በሰጠ ጊዜ እድሜው ገና ሰላሳ ነበር፡፡ ተጨማሪ አርባ አመቱ ድረስ ቢኖር ዓለምን በሙሉ ሊዞር ይችል ነበር፡፡

    በሕንድ አገር ቼናይን በጐበኙሁበት ወቅት በተጠራጣሪው በቶማስ ስም የተሰራ ቤተክርስቲያን አገኘሁ ቶማስ ከአስራ ሁለቱ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዛሙርት አንዱ ነው፡፡ ታሪኩ እንደሚለው በሆነው ሐዋርያው ቶማስ ሕንድ ተጉዞ አገልግሏል። በዚያ ስፍራ ተሰውቶ ለነበረ በስሙ ቤተክርስቲያን ተገነባለት፡፡ ከኢየሱስ ጋር አብሮ የነበረው ቶማስ ሕንድ ሔዶ ማገልገል ከቻለ፣ ኢየሱስ ክርስቶስም ወደ ሕንድ ተጉዞ ሊያገለግል በቻለ ነበር፡፡ ኢየሱስ ዓለምን ዞሮ የመንግስቱን ወንጌል ሊሰብክ ይችል ነበር፡፡

    ኢየሱስ በድንገት ስብከቱን አቁሞ እንደሚያዝ፣ እንደሚገረፍ እና እንደሚገደል እያወቀ ወደ ኢየሩሳሌም አቀና፡፡ ኢየሱስ እንዲህ ብሏል፡፡ ሕይወቴን በራሴ ፈቃድ አሳልፌ እሰጣለሁ እንጂ ከእኔ ማንም አይወስዳትም።

    መስቀሉ ለምን አስፈለገ።

    ኢየሱስ ክፉ ሰዎች እንደሚሰቅሉት እያወቀ ሆን ብሎ ወደዚያ ስፍራ ለምን ሔደ። ለሰው ልጆች ደሙን ለማፍሰስ የመረጠው ይህንን መንገድ ስለሆነ ነው፡፡ ኢየሱስ ስለኛ ደሙን ባያፈስልን ኖሮ የኢየሱስ ቃላት በተረሳና አገልግሎቱም እዚያው ባበቃ ነበር። ነገር ግን ዛሬም የኢየሱስ ደም ኃይል በስራ ላይ ነው፡፡ በዓለማችን በሚገኘው ጥልቅ ሸለቆም ሆነ ትልቅ ተራራ ይደርሳል፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሞተ ሁለት ሺ አመታት ቢያልፍ ከኢየሱስ ደም የተነሳ የእግዚአብሔር የማዳን ኃይሉ ዛሬም ይሰራል፡፡ የኢየሱስ ደም አስፈለጊ የሆነው ለዚህ ነው፡፡

    የኢየሱስ ቃላት

    ኢየሱስ ታዋቂ የሆኑትን እነዚህን

    Enjoying the preview?
    Page 1 of 1