Discover millions of ebooks, audiobooks, and so much more with a free trial

Only $11.99/month after trial. Cancel anytime.

የማያውቁ ሰዎች
የማያውቁ ሰዎች
የማያውቁ ሰዎች
Ebook209 pages1 hour

የማያውቁ ሰዎች

Rating: 5 out of 5 stars

5/5

()

Read preview

About this ebook

በዚህ ዓይነተኛ መጽሐፍ ውስጥ፣ ቢሾፕ ዳግ ሂዋርድ-ሚልስ የታማኝነት መኖር የመሪውን ብቃት ምን ያህል እንደሚያዳብር ያስተምራሉ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን፣ የታሪክ እና የሥነ-ጽሑፍ ማጣቀሻዎችን መጠቀማቸው ደግሞ ርዕሰ ጉዳዩ ለማንኛውም ዓይነት መሪ ጠቃሚ እንዲሆን አድርጐታል፡፡

Languageአማርኛ
Release dateJul 27, 2016
ISBN9781613954584
የማያውቁ ሰዎች
Author

Dag Heward-Mills

Bishop Dag Heward-Mills is a medical doctor by profession and the founder of the United Denominations Originating from the Lighthouse Group of Churches (UD-OLGC). The UD-OLGC comprises over three thousand churches pastored by seasoned ministers, groomed and trained in-house. Bishop Dag Heward-Mills oversees this charismatic group of denominations, which operates in over 90 different countries in Africa, Asia, Europe, the Caribbean, Australia, and North and South America. With a ministry spanning over thirty years, Dag Heward-Mills has authored several books with bestsellers including ‘The Art of Leadership’, ‘Loyalty and Disloyalty’, and ‘The Mega Church’. He is considered to be the largest publishing author in Africa, having had his books translated into over 52 languages with more than 40 million copies in print.

Related to የማያውቁ ሰዎች

Related ebooks

Reviews for የማያውቁ ሰዎች

Rating: 5 out of 5 stars
5/5

1 rating0 reviews

What did you think?

Tap to rate

Review must be at least 10 words

    Book preview

    የማያውቁ ሰዎች - Dag Heward-Mills

    አለማወቅ እና ታማኝ አለመሆን

    ማንም የማያውቅ ቢኖር ግን አይወቅ።

    1ኛ ቆሮንቶስ 14፡38

    ስለታማኝነት እና ታማኝ አለመሆን ብዙ የምንማረው አለ ምንም እንኳን የምንማረው ነገር ቢኖርም አንዳንድ የማያውቁ ሰዎች የማያውቁ (ደንቆሮዎች) ሆነው መቅረትን ይመርጣሉ፡፡ ይህ መጽሐፍ የታማኝነትና ታማኝ የአለመሆን መሰረታዊ ሃሳቦችን የሚመሩ (የሚያስተዳድሩ) መርሆችን፣ህጎችን፣መመሪያዎችንና እውነታዎችን ይዟል፡፡ ታማኝ አለመሆን ብዙውን ጊዜ የአለማወቅ፣የአለመብሰልና የትምህርት መጉደል (ማነስ) ፍሬ ነው፡፡ ብዙውን ጊዜ ያልተማሩ ሰዎች ለማመጽና ታማኝ ላለመሆን የተጋለጡ ናቸው፣ ምክንያቱም የሚያደርጓቸው ነገሮች የሚያስከትሉባቸውን መዘዞች አያስተውሉትምና፡፡ ይህ መጽሐፍ በያዘው አስተምህሮ አማካኝነት በህይወትህና በአገልግሎትህ ውስጥ አለማወቅ ሊያመጣብህ የሚችለውን ጉዳቶች መቋቋም ትችላለህ፡፡

    ብዙ አብያተ ክርስቲያናት ድባቅ የተመቱት ከማናቸውም ምክንያቶች ይልቅ ታማኝ ባለመሆንና በመዘዞቹ ነው፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደዚህ ግንዛቤ የደረስሁት በአገልግሎቴ የመጀመሪያ ዓመት ላይ ነበር፡፡ በሤራ፣ በክስ፣ በውንጀላ፣ ስም በማጥፋትና በክፍፍል ምክንያት ጭል ጭል ትል የነበረው አገልግሎቴ ሰይጣናዊ ጥቃት ደረሰባት፡፡ በእነዚያ ቀናት ያየሁትን ያህል ውዥንብር ጨርሶ አይቼ አላውቅም፡፡

    ገና በአገልግሎቴ ጅማሬ፣ ታማኝ አለመሆንና ተዛማጅ ክፋቶቹ በዲያብሎስ ጦር ዕቃ ውስጥ የተካተቱ አውዳሚ መሣሪያዎች መሆናቸውን ደመደምሁ፡፡

    ብዙዎቹ ክርስቲያኖች የዲያብሎስ ከፍተኛ መሣሪያ በመተት፣ በጥንቆላና በውቃቢ አማካኝነት መሥራት እንደሆነ ያስባሉ፡፡ እነዚህ ነገሮች በዲያብስ ጦር ዕቃ ውስጥ ስፍራ ያላቸው መሣሪያዎች መሆናቸውን አምናለሁ፡፡

    ነገር ግን የሰይጣን ብርቱ ዘመቻ የሚካሂደው በማሳት ሥራ መሆኑን ሰዎች ሊረዱት ይገባል፡፡ ሰይጣን አንተን ማሳት ከቻለ፣ ሊያወድምህ ይችላል! ሰይጣን ብዙ ሰዎች የእግዚአብሔርን ሰው የሚቃወሙት በፍትሕና በእውነት ስም መሆኑን እንዲያምኑ ያደርጋል፡፡ ይሁንና፣ ብዙም ሳይቆይ በምስማርና በእሾክ ላይ እየሄዱ መሆናቸውን በብዙ ድካም ይረዱታል፡፡

    ጳውሎስ ከቤተ ክርስቲያን ጋር ሲጣላና ከመሪዎቿ አንዱ የሆነውን የእስጢፋኖስን መወገድ ተከታትሎ ባስፈጸመ ጊዜ ከደረሰባቸው ነገሮች ይህ አንዱ ነው፡፡ ሳውል መልካም ኅሊና የነበረው ሰው ነበር፡፡ በቅንነት ከሰላማዊቱ የኢየሩሳሌም ከተማ ችግር ፈጣሪ ሰዎችን እያስወገደ የነበረ መሰለው፡፡ ለጽድቅ ባለው መቆርቆር፣ ለኅብረተሰቡ ጠንቅ ናቸው ያላቸውን ሰዎች ከምድረ ገጽ ለማጥፋት ፈለገ፡፡ ሐሳዊ ሰባኪዎችንና አገልጋዮችን በማጋለጥ ቅዱስ ጦርነት እያካሄዱ ያሉ የሚመስላቸው ብዙ ሰዎች አሉ፡፡ እንደ ሳውል በመድረክ ላይ የሚደረገውን ግብዝነት ሁሉም ሰው እንዲያውቅ የማድረግ መለኮታዊ ውክልና የተሰጣቸው ይመስላቸዋል፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ በተግባር ይዋጋ የነበረው ከክርስቶስ ጋር መሆኑን የተረዳው በድንጋጤ ነበር፡፡

    ሲሄድም ወደ ደማስቆ በቀረበ ጊዜ ድንገት በእርሱ ዙሪያ ከሰማይ ብርሃን አንጸባረቀ፤ በምድርም ላይ ወድቆ ሳለ፣ ሳውል ሳውል፥ ስለ ምን ታሳድደኛለህ? የሚለውን ድምፅ ሰማ። ጌታ ሆይ፥ ማን ነህ? አለው። እርሱም፦ አንተ የምታሳድደኝ እኔ ኢየሱስ ነኝ፤ የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃል አለው። እየተንቀጠቀጠና እየተደነቀ፣ ጌታ ሆይ፥ ምን አደርግ ዘንድ ትወዳለህ? . . .

    የሐዋርያት ሥራ 9፡3-6

    ጳውሎስ ምን እየሠራ እንዳለ በትክክል ሲገባው ተደነቀ! ሰዎች የሚያደርጉትን ነገር የማያውቁ ከሆነ ብዙ ጊዜ ስሕተት ነገር ይሠራሉ፡፡ ጳውሎስ ወደኋላ ላይ እየሠራ የነበረውን ስላላወቀ ከእግዚአብሔር ምሕረትን እንደተቀበለ ተናግሯል፡፡

    አስቀድሞ ተሳዳቢና አሳዳጅ አንገላችም ምንም ብሆን፥ ይህን አደረገልኝ፤ ነገር ግን ሳላውቅ ባለማመን ስላደረግሁት ምህረትን አገኘሁ፥

    1ኛ ጢሞቴዎስ 1፡13

    በአገልግሎት ያለኝ ትንሽ ልምድ፣ እምነት የሚጣልበት፣ ታማኝ፣ የተረጋጋ፣ የማይዋዥቅና አቋመ ጽኑ መሆን አለመቻል የአገልግሎቶች ከፍተኛ ገዳዮች መሆናቸውን አሳይቶኛል፡፡ እነዚህ የማናቸውም ዓይነት ሥራዎች ገዳዮች ናቸው፡፡ በሁሉም ሰዎች ውስጥ አጭር፣ ፈጣንና ቀላል መንገድ አለ የሚል ስሜት አለ፡፡ ሰይጣን ደግሞ ያን ዝንባሌ ያጋንነዋል፡፡

    ብዙ ክርስቲያኖች ዓመፀኞችንና ሸፋች ባለ ራእዮችን እስከመከተል ተታልለዋል፡፡ ብዙ ሰዎች ይህን የሚያደርጉት ካለማወቅ ነው፡፡ ዲያብሎስ በቤተ ክርስቲያን የዓመፅንና ታማኝ ያለመሆንን ባሕል ለመፍጠር አምባገነን የቤተክርስቲያን መሪዎችን ምሳሌ ይጠቀማል፡፡ ብዙዎቹ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ሳያውቁት ዓመፀኞችና ታማኝ ያልሆኑ ሆነዋል፡፡ በሚናገሯቸውና በሚያደርጓቸው ነገሮች ተከታዮቻቸውን ዓመፅ ያስተምራሉ፡፡ ሰው ለምን በእነርሱ ላይ እምነት እንደማይኖረው እና ታማኝ እንደማይሆንላቸው አይገባቸውም፡፡ አየህ ሽንገላ እንዲህ ብርቱ ነገር ነው፡፡ በምትታለልበት ወቅት ጥቁር ነጭ፣ ነጭ ደግሞ ጥቁር ነው ብለህ ታስባለህ፡፡

    ዘ ፋይናል ኩዌስት በተሰኘው መጽሐፉ እግዚአብሔር ለሪክ ጆይነር በሰጠው ራእይ በጣም ተደንቄ ነበር፡፡ ይህን መጽሐፍ ካገኘሁት ጊዜ ጀምሮ በሺዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች እንዲያነቡት መክሬአለሁ፡፡ የዚህ መጽሐፍ የመጀመሪያዎቹ ገጾች የተለየ ገላጭነት እንዳላቸው ተመለከትሁ፡፡ ጸሐፊው ግዙፍ አጋንንታዊ ሰራዊት በቤተ ክርስቲያን ላይ እየተመመ የመነሣቱን መገለጥ ያስረዳል፡፡ የዚህ አጋንንታዊ ሰራዊት ዋነኛ ዓላማ በማናቸውም ግንኙነቶች ደረጃ መለያየትን መፍጠር ነበር፡፡ ይኽውም ቤተ ክርስቲያኖች ከሌሎች ቤተ ክርስቲያኖች ጋር፣ ምዕመናን ከመጋቢዎቻቸው ጋር እንዲሁም ባሎች ከሚስቶቻቸው ጋር የማይስማሙበትን ሁኔታ መፍጠር ነበር፡፡

    ሌላኛው የመገለጡ ክፍል እነዚህ አጋንንታዊ ሰራዊት የሚጠቀሟቸው የውጊያ መሣሪያዎች ነበሩ፡፡ በተለይ የያዟቸው ጦሮች ክህደት የተሰኙ መሆናቸውን ተገነዘብሁ፡፡ ክህደት ከፍተኛው ታማኝ ያለመሆን ደረጃ ወይም መልክ መሆኑን ታውቃለህ? የተጠቀሰው አንድ ጦር ብቻ ሲሆን ስሙም ክህደት መባሉ ያስደንቀኛል፡፡ ወድ ወዳጄ፣ እኔ በቤተ ክርስቲያን ላይ ሰይጣን የሚያነሣው ዋነኛ መሣሪያ ታማኝ አለመሆን እና ክህደት እንደሆነ አምናለሁ፡፡

    በዚህ ነገር እየተገረምሁ እያለሁ፣ ታላቅ መሰናክል የገጠማቸው ብዙዎቹ አብያተ ክርስቲያናት ለዚህ የተዳረጉት ክህደት የተነሣ እንደሆነ ተገነዘብሁ፡፡ አክብሮቴን የሰጠኋቸውን ብዙ ታላላቅ የእግዚአብሔር ሰዎች ሳስብ አገልግሎቶቻቸው እንዴት እንደተቀጩ ልብ አልሁ፡፡ ለተፈጠሩት የሚያስቆጩ ውድቀቶች ታማኝ አለመሆን ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል፡፡

    በዚህ መገለጥ ውስጥ የተጠቀሱ አራት ቀስቶች ነበሩ፤ እነርሱም ክስ፣ ሐሜት፣ ስም ማጥፋት እና ስህተት መፈለግ ናቸው፡፡ ከውጫዊ ሁኔታቸው እንዲሁ ለሚያይ ሰው እነዚህ አራት መሣሪያዎች ውጤታማ የሚሆኑ አይመስሉም፡፡ እንዲያውም ሰይጣን የሚጠቀምባቸው መሣሪያዎች መስለውም አይታዩም፡፡ ይሁንና፣ ለተወሰኑ ዓመታት በአገልግሎት ውስጥ ከቆየሁ በኋላ ዲያብሎስ የሚጠቀምባቸው ብቃት ያላቸው መሣሪዎች እነዚህ እንደሆኑ ድምዳሜ ላይ ደረስሁ፡፡ እንዲሁ ከላይ የሚመለከታቸው በልምድ ያልበሰለ ሰው እነዚህን ተራ ችግሮች አድርጎ ሊቆጥራቸው ይችላል፡፡

    ብዙ ሰዎች እነዚህ የተጠቀሱትን መሣሪያዎች ማናቸውም አገልጋይ በቀላሉ ሊያስተናግድ የሚችለው ተራ ነገሮች አድርገው እንደሚቆጥሩ እርግጠኛ ነኝ፡፡ ዲያብሎስ ክስ የተከሰሰውን ሰው ምን ያህል እንደሚያዳክም፣ ግራ እንደሚያጋባ እና ሽባ እንደሚያደርግ ያውቃል፡፡ የተከሰሰው ሰው የቱንም ያህል ንጹሕ ይሁን አንድ ጊዜ ከተከሰሰ ወዲያ ውዥንብር ውስጥ ይገባል፡፡ ሰው እንዲህ ያለ ነገር ስለምን ያስባል? ብሎ ራሱን ይጠይቃል። ንጹሕ ሰዎች እንኳ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ክሶቹ ትክክል ናቸው ብለው እስከሚስማሙ ድረስ ክሶች ብርቱዎች ናቸው፡፡ ክሶች የተከሰሰውን ሰው ሽምድምድ ያደርጉታል፡፡ ሰዎች ከተሸመደመዱ ወዲያ የመንቀሳቀስ ኃይላቸው ይታሰራል፡፡ ክሶቹ በሚዛመቱበት ወቅት የተከሰሰው ሰው መርዙ በተሰራጨባቸው አካባቢዎች ለመንቀሳቀስ ልበ ሙሉነት ይከዳዋል፡፡ ስም ማጥፋት፣ ሐሜትና ስህተት መፈለግ ሁላቸውም የክስ ዓይነቶች ናቸው፡፡ እነዚህ ነገሮች ቤተ ክርስቲያንን ያዳክማሉ፣ ሽባ ያደርጋሉ፣ ያደናግራሉ፡፡ ይህ መደነጋገር በቤተ ክርስቲያን ውስጥና ውጭም ነው፡፡ የተከሰሰው ሰውም ሆነ ሰሚዎቹ ይደናገራሉ፡፡ ብዙ ሰዎች ይህን ውዥንብር ፈጽሞ አያሸንፉትም። አንዳንዶች አገልግሎትን መቀበል ሌሎች ደግሞ በአገልግሎት መቀጠል ፈጽሞ አይችሉም፡፡ ክስ እንዲህ ጽኑ የሆነ የጠላት መሣሪያ ነው! መጽሐፍ ቅዱስ ለቤተ ክርስቲያን ጥንካሬ የሚመጣው ከሳሹ ሲወገድ እንደሆነ መናገሩ የሚያስደንቅ አይደለም፡፡ የከሳሹን ድምፅ እስከሰማህ ድረስ በሆነ መንገድ ትዳከማለህ፡፡

    ታላቅም ድምፅ በሰማይ ሰማሁ እንዲህ ሲል፦ አሁን የአምላካችን ማዳንና ኃይል . . . ፣ ቀንና ሌሊትም በአምላካችን ፊት የሚከሳቸው የወንድሞቻችን ከሳሽ ተጥሎአልና።

    ራእይ 12፡10

    በእግዚአብሔር ሰዎች ላይ የማያቋርጡ ክሶች ለምን እንደሚወረወሩ ጠይቀህ ታውቃለህ? በአንድ ትልቅ ከተማ ውስጥ ታላቅ ፈር ቀዳጅ ሥራ የሠራ መጋቢ ትዝ ይለኛል፡፡ በዚህ ሰው ብዙ ሰዎች ድነትን፣ ብዙ አገልጋዮችም ሥልጠናን አግኝተዋል፡፡ ይህ ሰው በመጨረሻ ከተማዪቱን ለቅቆ እስከሚሄድ ድረስ ስሙ ጠፋ፡፡ ጥፋቶቹ እጅግ ከመጋነናቸው የተነሣ ስለ እርሱ ምንም መልካም ነገር እስከማይነገርበት ደረጃ ላይ ደረሰ፡፡ በመጨረሻም፣ ከተማዪቱን ለቅቆ እስከመሄድና አገልግሎቱንም እስከመተው ደረሰ፡፡ የሰይጣን አሠራር ስልት ቀላል ነው፡- በራሳቸው እምነት አስከማይኖራቸው ድረስ ክሰሳቸው! በማኅበረሰቡ ውስጥ ካለው ሰው ሁሉ ማንም ስለ እነርሱ መልካም እስከማያስብ ድረስ ክሰሳቸው፡፡ የሚሠሩቱን በራሳቸው እንዲያቆሙ አድርግ የሚል በጣም ቀላል የሆነ ስልት ነው፡፡

    ይሁን እንጂ ያን አካባቢ ትቶ ከወጣ ከብዙ ዓመታት በኋላ በእነዚያ በባረካቸው ሰዎች እንደገና የክብር ግብዣ ተደረርጎለት ተጠራ፡፡ የአገልግሎቱን ፍሬ ባየ ጊዜ እንደተደነቀ አምናለሁ፡፡ ለከሳሹና ለግብራበሮቹ የማያቋርጥ ውጊያ እጅ መስጠት እንዳልነበረበት ምናልባት አሁን ሳይገነዘብ አልቀረም፡፡ ከዚህ ሁኔታ በኋላ ወደ አገልግሎቱ መመለሱን የምነግርህ በደስታ ነው፡፡

    በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ሌላው አስደናቂ መገለጥ አጋንንት የሚጋልቡት ፈረሶችን ሳይሆን ክርስቲያኖችን መሆኑ ነው፡፡ በሌላ አነጋገር ክርስቲያኖች ሳያውቁት የዲያብሎስ አገልጋይ ይሆናሉ!

    የክርስቶስን አካል በመከፋፈል ስልቱ በጣም የተሳካለት አንድ መጋቢ አውቃለሁ፡፡ ላለፉት አስራ አምስት ዓመታት ውስጥ አገልግሎቱን የተከታተልሁ ሲሆን፣ ቤተ ክርስቲያንን በመከፋፈልና ተቃዋሚ ጎራዎችን በመፍጠር በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ልዩ ስጦታ እንዳለው ይሰማኛል፡፡ ይህ ሰው ድርጊቶቹና እርምጃዎቹ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ቡድኖችን መፍጠራቸውን የሚያውቅ እንኳ አይመስለኝም፡፡ ይህን ሥራውን የሚሠራው ብዙ ሳይጨነቅና በሚያስደንቅ ዲፕሎማሲ ነበር! ስታየው በፊትህ እጅግ የተከበረ ስለሚመስል ቤተ ክርስቲያንን በቡድኖች እየከፋፈለ መሆኑ ፈጽሞ አይታሰብህም፡፡ እንዴት ከፋፋይ እንደሆነ የምትረዳው ቁጭ ብለህ ድርጊቶቹን ስታሰላስል ነው።

    ከዚህ የሰይጣን ሰራዊትና የስልቶቹ መገለጥ ራእይ ይህን አጭር ክፍለ ምንባብ እንዳካትት ሪክ ጆይነር ስለፈቀደልኝ ደስተኛ ነኝ፡፡ የሰይጣንን ስልቶች በግልጽ እንድትረዳ ጸሎቴ ነው፡፡

    "የአጋንንቱ ሰራዊት እጅግ ግዙፍ ስለነበር ዓይኖቼ ማየት እስከሚደክማቸው ድረስ መጨረሻቸው አይታይም ነበር፡፡ እያንዳንዳቸው ዓርማ ይዘው በቡድን በቡድን ሰፍረው ነበር፡፡ ግንባር ቀደሙ ቡድን ትዕቢት፣ ራስን ማመጽደቅ፣ ክብር ፈላጊነት፣ ራስ ወዳድ ምኞት፣ በጽድቅ አለመፍረድ፣ እና ምቀኝነት በተሰኙ ዓርማዎች ሥር ተኮኩለው ነበር፡፡ የእነዚህ የክፋት ቡድኖች ብዛት ማየት ከምችለው በላይ ከዚህም እጅግ ያለፈ ነበር፡፡ ነገር ግን የእነዚህ ከገሃነም የተላኩ የክፋት ሰራዊት ግንባር ቀደሞቹ በጣም ኃይለኞች ይመስሉ ነበር፡፡ የእነዚህ ሰራዊት መሪ የወንድሞች ከሳሽ ራሱ ነበር፡፡

    ይህ ሰራዊት የተሸከማቸው የጦር መሣሪያዎችም፣ ስም ነበራቸው፡፡ ሰይፎቹ ማስፈራራት፤ ጦሮቹ ደግሞ ክህደት፣ ፍላጻዎቹ ደግሞ ክስ፣ ሐሜት፣ ስም ማጥፋትና ስህተት መፈለግ የሚሉ ስሞች ተሰጥቷቸው ነበር፡፡ ተቀባይነት ማሳጣት፣ ምሬት፣ ትዕግሥት የለሽነት፣ ይቅር አለማለትና ፍትወታዊ ምኞት የተሰኙ ስሞች የያዙ ጭፍሮችና ትናንሽ የአጋንንት ቡድኖች ደግሞ ለዋናውን ውጊያ ሁኔታዎችን እንዲያመቻቹ ከዚህ ሰራዊት ቀድመው ተላኩ፡፡

    እነዚህ ትናንሽ ቡድኖችና ጭፍራዎች በቁጥር በጣም ያነሱ ነበሩ፣ ነገር ግን ብርታታቸው ከሚከተሉት አንዳንድ ግዙፍ ክፍለ ጦሮች የሚተናነስ አልነበረም፡፡ ቁጥራቸው ያነሰው ለስልታዊ ዓላማዎች ሲባል ብቻ ነበር። መጥምቁ ዮሐንስ አንድ ግለሰብ እንደነበረ፣ ነገር ግን ሕዝቡን ለጌታ ለማዘጋጀት እንዲያጠምቃቸው ልዩ የሆነ ቅባት እንደተሰጠው ሁሉ፣ እነዚህ ትናንሽ የአጋንንት ጭፍሮች ሕዝቡን እንዲያጠምቁ ልዩ የሆነ የክፋት ኃይል ተሰጥቷቸው ነበር፡፡ አንድ የጥላቻ ጋኔን ቁጥር ስፍር በሌላቸው ሰዎች፣ እንዲያውም በየሰዉ ዘር ወይም ባሕሎች ውስጥ መርዙን ሊዘራ ይችላል፡፡ አንድ የፍትወት ጋኔን ከአንድ የፊልም ተዋናይ፣ ወይም ከአንድ ፊልም፣ ወይም ከአንድ ማስታወቂያ ጋር ራሱን በማዳበል በብዙኃን ሕዝብ ላይ የኤሌክትሪክ ብራቅ የሚመስል ፍላጻ በመወርወር ያደነዝዛቸዋል፡፡ ይህ ሁሉ የሚደረገው ተከትሎ ለሚመጣው ታላቅ የክፋት ሰራዊት ዝግጅት ይሆን ዘንድ ነበር፡፡

    ይህ ሰራዊት በተለይ እየተመመ የነበረው በቤተ ክርስቲያን ላይ ሲሆን የቻለውን ሁሉ ከማጥቃትም የሚመለስ አልነበረም፡፡

    Enjoying the preview?
    Page 1 of 1