Discover millions of ebooks, audiobooks, and so much more with a free trial

Only $11.99/month after trial. Cancel anytime.

የሚከሱህ ሰዎች
የሚከሱህ ሰዎች
የሚከሱህ ሰዎች
Ebook168 pages3 hours

የሚከሱህ ሰዎች

Rating: 0 out of 5 stars

()

Read preview

About this ebook

ምናልባት በሕይወትህ ከሚያጋጥሙህ ታላቅ ጠላቶች ውስጥ ‘በወንድሞች መካከል ያለ ከሳሽ’ ነው፡፡” ይህ የክስ መሣሪያ እንዴት እንደሚጠመድብህ እና እንዴትስ ልታሸንፈው እንደምትችል ይህን በዳግ ሂዋርድ ሚልስ የተጻፈ ምርጥ መጽሐፍ በማንበብ ታላቅ ማስተዋልን ተቀበል፡፡

Languageአማርኛ
Release dateJul 27, 2016
ISBN9781613954560
የሚከሱህ ሰዎች
Author

Dag Heward-Mills

Bishop Dag Heward-Mills is a medical doctor by profession and the founder of the United Denominations Originating from the Lighthouse Group of Churches (UD-OLGC). The UD-OLGC comprises over three thousand churches pastored by seasoned ministers, groomed and trained in-house. Bishop Dag Heward-Mills oversees this charismatic group of denominations, which operates in over 90 different countries in Africa, Asia, Europe, the Caribbean, Australia, and North and South America. With a ministry spanning over thirty years, Dag Heward-Mills has authored several books with bestsellers including ‘The Art of Leadership’, ‘Loyalty and Disloyalty’, and ‘The Mega Church’. He is considered to be the largest publishing author in Africa, having had his books translated into over 52 languages with more than 40 million copies in print.

Related to የሚከሱህ ሰዎች

Related ebooks

Reviews for የሚከሱህ ሰዎች

Rating: 0 out of 5 stars
0 ratings

0 ratings0 reviews

What did you think?

Tap to rate

Review must be at least 10 words

    Book preview

    የሚከሱህ ሰዎች - Dag Heward-Mills

    ከሳሾች

    ከዚህ በኋላ ታላቅ ድምፅ በሰማይ እንዲህ ሲል ሰማሁ! "አሁን የአምላካችን ማዳን፣ ኃይልና መንግሥት፣ የእርሱ ክርስቶስ ሥልጣንም መጥቶአል፡፡ ቀንና ሌሊት በአምላካችን ፊት ሲከሳቸው የነበረው፣ የወንድሞቻችን ከሳሽ ተጥሎአልና፡፡

    ራእይ 12፡10

    ዲያብሎስ ምንም እንኳ የወንድሞች ከሳሽ ተብሎ ቢታወቅም፣ እርሱ ግን በእርግጥ በወንድሞች መካከል ያለ ከሳሽ ነው፡፡

    በመሪነት ተሞክሮህ ብዙ ጊዜ የተለያዩ ዓይነት ሰዎች ይገጥሙሃል፡፡ ምናልባት ሊገጥሙህ ከሚችሉ አስፈሪ ከሆኑ ጠላቶች ሁሉ እጅግ የከፋው በወንድሞች መካከል ያለ ከሳሽ ነው፡፡

    ምናልባት ችግሮች በተለያዩ ደረጃዎች ሊመጡ ይችሉ ይሆናል። ነገር ግን ከችግሮች ሁሉ እጅግ የሚከፋው በወንድሞች መካከል ከሳሽ የመነሣቱ ጉዳይ ነው፡፡

    በአገልግሎትህ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ከከሳሹ ጋር ግብ ግብ ትገጥማለህ፡፡ ክስ ሊሸነፍ በማይችል ጠላት ላይ የሚነጣጠር የሰይጣን ከፍተኛ ስልት ነው፡፡

    ከፍተኛው የሰይጣን መሣሪያ

    ሰይጣን የሚሠራባቸው የተለያዩ ዘዴዎች አሉት፡፡ እንደ ፈታኝ፣ እንደ ውሸታም፣ እንደ ገዳይ ወይም እንደ አሳች ሊመጣ ይችላል። ይሁን እንጂ፣ ከሳሽ ሆኖ ከመጣብህ ውጊያው ሊደርስ ወደሚችልበት ቁንጮ ደርሷል ማለት ነው፡፡

    ይህ ሁኔታ በኢየሱስ ሕይወት ውስጥም ተፈጽሞ ነበር፡፡ በመጀመሪያ፣ ዲያብሎስ ወደ እርሱ የመጣው እንደ ፈታኝ ሆኖ ነበር፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ በምድረበዳ ለአርባ ቀናት ተፈተነ፡፡ ሰይጣን በምድረበዳ ኢየሱስን ከዋሸው በኋላ ወዲያው በጽኑ ሊያስተው ተጣጣረ፡፡

    በጌታን የአገልግሎት ዘመን ሁሉ፣ ዲያብሎስ እንደ ገዳይ ሆኖ ጥቃት ይሰነዝርበት ነበር፡፡ እርሱ በመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበር (ዮሐንስ 8፡44)፡፡ በርከት ባሉ የተለያዩ ጊዜያት ሰይጣን ሕዝብን በማስነሣት ኢየሱስን ሊገድል የተንቀሳቀሰ ቢሆንም ኢየሱስ ግን ከእጁ አምልጦአል፡፡

    በምኩራብም የነበሩ ሰዎች ሁሉ ይህን በሰሙ ጊዜ በቁጣ ገነፈሉ፡፡ ከተቀመጡበትም ተነሥተው ከከተማው አስወጡት፡፡ ቁልቁል ሊጥሉትም ከተማቸው ወደተሠራችበት ኮረብታ አፋፍ ወሰዱት፡፡ እርሱ ግን በመካከላቸው ሰንጥቆ ሄደ፡፡

    ሉቃስ 4፡29-30

    በሌላ ጊዜ ዲያብሎስ ኢየሱስን በገሊላ ባሕር ሊያሰጥመው ሞክሮ ነበር፡፡ ነገር ግን ኢየሱስ ማዕበሉን በመገሠጽ ባሕሩን ፀጥ ስላሰኘ አልተሳካለትም፡፡ ያን ማዕበል ያመጣው እግዚአብሔር አልነበረም፡፡ እንደዚህ ባይሆን ኖሮ ኢየሱስ ማዕበሉን መገሠጹ የእግዚአብሔርን ጥበብ መገሠጹ ይሆን ነበር፡፡

    እየተጓዙ ሳሉም ኢየሱስ እንቅልፍ ወስዶት ተኛ፤ በዚህ ጊዜ በባሕሩ ላይ ማዕበል ተነሣ፤ ውኃውም ጀልባዋን ዘልቆ ስለገባ፣ አደጋ አፋፍ ላይ ደረሱ፡፡

    ደቀመዛሙርቱም ቀርበው፣ ጌታ ሆይ ማለቃችን እኮ ነው፣ እያሉ ቀሰቀሱት፡፡ እርሱም ነቅቶ ነፋሱንና የውኃውን መናወጥ ገሠጸ፤ በዚህ ጊዜ ነፋሱም ነውጡም ተወ፤ ጸጥታም ሆነ፡፡

    ሉቃስ 8፡23-24

    በከሳሽነት ካባ መገለጥ

    ይሁንና የኢየሱስ አገልግሎት በመጨረሻ ሊደመደም የቻለው ሰይጣን የከሳሽነትን ካባ አድርጎ በተገለጠ ጊዜ ነበር፡፡ ኢየሱስ ወደ አገልግሎቱ ፍጻሜ ያደረሱትን ጽኑ ክሶች ለአንድ ሙሉ ሳምንት ተጋፈጠ፡፡ ይህ የብርቱ ክሶች ሳምንት ከደብረዘይት ቀን ጀምሮ እስከሚሰቀል ድረስ የቀጠለ ነበር፡፡ ማቴዎስ 21፡1-17 ላይ እንዴት ወደ ኢየሩሳሌም በድል አድራጊነት እንደገባና ቤተ መቅደሱን እንዳነጻ ትመለከታለህ፡፡ ኢየሱስ ኢየሩሳሌም ከገባበት ቀን በኋላ ጀምሮ ጥያቄዎቹና ክሶቹ እንዴት እንደጀመሩም ማየት ትችላለህ፡፡ (ማቴዎስ 21፡23)

    በዚህ ጊዜ ሰይጣን እጅግ የከፋ መሣሪያውን በማንሣት በጌታ ላይ ሰነዘረ፡፡ የክስን መሣሪያ በመጨረሻ በሥራ ላይ አዋለ፡፡ ከፋሲካው በፊት ሙሉውን ሳምንት ኢየሱስ በፈሪሳውያን አማካኝነት ጥያቄ እየቀረበበትና እየተመረመረ (በክስ) ማለፍ ግድ ሆነበት፡፡

    ከዚህ በኋላ ፈሪሳውያን ወጥተው በመሄድ በአፍ እላፊ እንዴት እንደሚያጠምዱት ተማከሩ፡፡ ደቀ መዛሙርታቸውን ከሄሮድስ ወገኖች ጋር ወደ እርሱ ልከው መምህር ሆይ፤ አንተ እውነተኛና የእግዚአብሔርንም መንገድ በእውነት የምታስተምር እንደ ሆንህ፣ ለማንም ሳታዳላ ሁሉን በእኩልነት እንደምትመለከት እናውቃለን፤ ንገረን፤ ምን ይመስልሃል? ለመሆኑ ለቄሣር ግብር መክፈል ይገባል ወይስ አይገባም?

    ኢየሱስ ግን ተንኮላቸውን በመረዳት እንዲህ አላቸው፤ "እናንተ ግብዞች ለምን በነገር ልታጠምዱኝ ትሻላችሁ?

    ማቴዎስ 22፡15-18

    ጌታ ስለ እያንዳንዷ የሕይወቱ እና የአገልግሎቱ ሁኔታ ተመርምሮአል፡፡

    ለበርካታ ቀናት፣ በቤተ መቅደሱ ውስጥ ጥያቄ ያነሡበትን ሰዎች ክፋትና ግብዝነት መታገሥ ግድ ሆነበት፡፡ በሕይወቱ የመጨረሻዎቹ ሃያ አራት ሰዓታት ውስጥ ደግሞ በሊቀ ካህናቱ ግቢ፣ በጲላጦስ አደባባይና በሄሮድስ ቤተ መንግሥት ውስጥ ክስ ተሰንዝሮበታል፡፡

    ኢየሱስ የተሰነዘሩበትን ተከታታይ ከፍተኛ ደረጃ ክሶች በተለያዩ ዓይነት ምላሾች ተጋፍጦአቸዋል፡፡ በቤተ መቅደሱ ለተነሡበት ጥያቄዎች ተገቢዎቹን ምላሾች በመስጠት ከሳሾቹን አፍ ማስያዝ ችሎ ነበር፡፡

    ይህን ሲሰሙ ተደነቁ፤ ትተውትም ሄዱ፡፡

    ማቴዎስ 22፡22

    እንደዚህ ያለ ነገር ከዚህ ቀደም ፈጽሞ ሰምተው አያውቁም ነበር።

    ጠባቂዎቹም፣ እንደዚህ ሰው ከቶ ማንም ተናግሮ አያውቅም ሲሉ መለሱ፡፡

    ዮሐንስ 7፡46

    ይሁን እንጂ በጲላጦስ ወንበር ፊት በነበረ ጊዜና በሌሎች አረማውያን ገዢዎች ፊት በቀረበ ጊዜ በእርሱ ላይ ለሰነዘሩአቸው ለጥያቄዎች ምንም ምላሽ አልሰጠም ነበር፡፡

    እርሱ ግን አገረ ገዢው እስኪገረም ድረስ ለቀረበበት ክስ አንዲት ቃል እንኳ አልመለሰም፡፡

    ማቴዎስ 27፡14

    እንደምታየው ሰይጣን የሚያጠቃበት የተለያዩ ስልቶች አሉት፡፡ በዚህ የመጽሐፉ ክፍል ሰይጣን በማስፈራሪያነት የሚጠቀማቸውን ከሳሾች እንመለከታለን፡፡ ምናልባት አንተም በአገልግሎትህ የክስ ወረርሺኝ እየተሠቃየህ ይሆናል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ምን እየሆነብህ እንዳለም ላታውቅ ትችላለህ፡፡ ይህን መጽሐፍ አንብበህ በምትጨርስበት ጊዜ፣ እግዚአብሔር ጠላትህን የምትፋለምበትን ጥበብ ይሰጥሃል፡፡

    ክስ ምንድር ነው?

    ክስ በሌላ ሰው ላይ የሚሰነዘር ውንጀላ ወይም ነቀፋ ነው፡፡ ክስ በሰዎች ላይ ጣትን በመቀሰር ውንጀላን ይጭንባቸዋል፡፡ ክስ ማለት አንድ ሰው ስሕተትን፣ በተለይም ወንጀልን እንደፈጸመ በመግለጽ ጥፋተኝነትን የሚያስተጋባ ንግግር ነው፡፡

    በአንድ ሰው ላይ የሚሰነዘሩ እነዚህ ንግግሮች ያለማቋረጥ ሕይወትን የማጠውለግና የማዳከም ችሎታ አላቸው፡፡ በማያቋርጡ ክሶች መካከል ለረጅም ጊዜ ጸንቶ መቀጠል የሚችል በጣም ጠንካራ ልብ ያለው ሰው ብቻ ነው፡፡

    ክሶች ምንም እንኳ ከሰዎች አፍ ውስጥ ቢወጡም፣ በወንድሞች ከሳሽ የተቀቡ ንግግሮች ናቸው፡፡ ሰይጣን በወንድሞች መካከል ያለ ከሳሽ ነው፡፡

    ብዙ ጊዜ ከሳሾች ሆነው የሚያገለግሉ ሰዎች እነማን ናቸው?

    በአገሬ አንዳንድ ሰዎች የጥበቃ ሠራተኛ ሆነው ይቀጠራሉ፡፡ እንደዚሁም በልኳንዳ ቤት እና በመንገድ ዳር ጥብስ ሥጋ(ኪባብ) ሻጮች ሆነው የሚቀጠሩ ሰዎችም አሉ፡፡ እንደዚሁም ሰይጣን ከሳሾች አድርጎ የሚቀጥራቸው ሰዎችም አሉ፡፡ እኔ እነዚህን ሰዎች የተከሳሽ የቅርብ ወዳጆች ብዬ እጠራቸዋለሁ፡፡

    እንጀራዬን ተካፍሎኝ የበላ፣ የምተማመንበትም የቅርብ ወዳጄ በእኔ ላይ ተረከዙን አነሣ፡፡

    መዝሙር 41፡9

    የቅርብ ወዳጆች በሕይወትህ የቅርብህ የሆኑ፡ ጓደኞች፣ ባል፣ ሚስት፣ ወንድ ልጆች፣ ሴት ልጆች፣ እጮኛ ምስጢረኞች፣ ረዳት መጋቢዎች፣ የቤተክርስቲያን አባላት፣ ጋዜጠኞች፣ የክፍል ጓደኞች፣ ወዘተ ናቸው፡፡ ክሶች ውጤት እንዲኖራቸው ካስፈለገ መተላለፍ ያለባቸው የቅርብ በሆነ ሰው ነው፡፡

    ለምን ክሶችን ዝም ብሎ ወደ ጎን ተወት ማድረግ አይቻልም?

    ክሶች እውነት ወይም ውሸት የሆኑ ንግግሮች አይደሉምን? እውነት ካልሆኑ ለምን ዝም ብለህ ችላ አትላቸውም? ይሁን እንጂ ክሶች እንዲህ እንደሚታሰበው ቀላል አይደሉም፡፡

    ክሶች የገሃነም ቅባት የተቀቡ ናቸው፡፡ ክሶች መንፈሳዊ ነገሮች ናቸው፡፡ ክሶች ሰይጣናዊ መርዝ የተቀባባቸው ትንንሽ ቀስቶች ናቸው፡፡ መርዛቸው የደም ጅረትህ ውስጥ እንደገባ፣ ወዲያው ልብህን በማጥቃት በመላው ሰውነትህ ይሰራጫል፡፡ በፍጥነት እንደሚሰራጭ ተፈጥሯዊ መርዝ፣ ትንሽ በምትመስል ቀስት በእጅጉ ትጠቃለህ፡፡

    ታላላቅ የእግዚአብሔር ሰዎች በተመልካች ዘንድ እንደ ቁምነገር ባልተቆጠሩ መሠረተ-ቢስ በሆኑ ክሶች ፈጽሞ ሲሽመደመዱ አይቻለሁ፡፡ እንግዲህ የክስ ኃይል ያን ያክል ነው፡፡ ክስ ረቂቅ የሆነ መሣሪያ ሲሆን ውጤቶቹም ምስጢራዊ ናቸው፡፡ እውነቱን ለመናገር ክሶች መንፈሳዊ መሣሪያዎች ናቸው፡፡

    ጣትን መቀሰር

    ይህ ከሆነ ብርሃንህ እንደ ንጋት ጮራ ይፈነጥቃል፤ ፈውስህ ፈጥኖ ይደርሳል፤ ጽድቅህ ቀድሞህ ይሄዳል፤ የእግዚአብሔር ክብር ደጀን ይሆንልሃል፡፡

    የዚያን ጊዜ ትጣራለህ፤ እግዚአብሔርም ይመልስልሃል፤ ለርዳታ ትጮኻለህ፤ እርሱም አለሁልህ ይልሃል፡፡ የጭቆናን ቀንበር፣ የክፋትን ንግግርና ጣት መቀሰርን ከአንተ ብታርቅ፣ ለተራበው ብትራራለት፣ የተገፉት እንዲጠግቡ ብታደርግ፣ ብርሃንህ በጨለማ ያበራል፣ ሌሊትህም እንደ ቀትር ፀሐይ ይሆናል፡፡

    ኢሳይያስ 58፡8-9

    ክሶች በሌላ አባባል ጣትን መቀሰር የሚል ስያሜም አላቸው፡፡ ጣትን በመቀሰር የሚወረወረው ክፋት በሕይወትህና በአገልግሎትህ ውስጥ ያለው ብርሃን እንዲደበዝዝ እስከማድረግ የበረታ ነው፡፡ ጣት መቀሰርን ብትተው ብርሃንህ እንደ ንጋት ያበራል ፈውስም ይሆንልሃል!

    ጣት ቀሳሪ ሰው በአካባቢው እንዲፈነጭ ከተፈቀደለት አገልግሎቶች ሊለመልሙ አይችሉም፡፡ በክርስቶስ አካል መካከል ካሉ ጨለማዎች የሚበዛው ወንድም በወንድም፣ እህት በእህት፣ ባል በሚስት፣ ወዘተ ከሚሰነዝሯቸው የማያቋርጡ ክሶች የመነጨ ነው፡፡

    በዙሪያህ ያሉ ከሳሾችን ማወቅ አለብህ፡፡ እያንዳንዱ ጥሩ መሪ የክስን መርሆች በሚገባ አጥርቶ ማወቅ ይገባዋል፡፡ በተለያዩ ክሶች ምክንያት በአገልግሎትህ ልትጠወልግና ልትዳከም ትችላለህ! አገልግሎትህ በክሶች መዘዝ አቅጣጫውን ሊስት ይችላል፡፡ እኔ ራሴ ይህ ሁኔታ በሕይወቴ ገጥሞኝ ያውቃል፡፡ ይህ ቁምነገር ምናልባት የዚህ መጽሐፍ ዋነኛው ክፍል ስለሆነ አጽንኦት ሰጥተህ እንድታጠናው ጸሎቴ ነው፡፡

    እግዚአብሔር የወንድሞችን ከሳሽ እንዴት በማያዳግም ሁኔታ እንደተፋለመው የራእይ መጽሐፍ ያሳያል፡፡ ክሶችን ፀጥ ማሰኘት የሚያስገኛቸውን አራት አስደናቂ ጥቅሞች ይዘረዝራል፡፡ በእነዚህ አራት

    Enjoying the preview?
    Page 1 of 1