Discover millions of ebooks, audiobooks, and so much more with a free trial

Only $11.99/month after trial. Cancel anytime.

ዝንጉዎቹ
ዝንጉዎቹ
ዝንጉዎቹ
Ebook144 pages1 hour

ዝንጉዎቹ

Rating: 5 out of 5 stars

5/5

()

Read preview

About this ebook

አመጸኛ ሰዎች የተደረገላቸውን ነገር አያስታውሱም፣ ብዙ ጊዜም የተወሰኑ ነገሮችን ለመዘንጋት ይመርጣሉ፡፡ ጌታ ለይሁዳ ያደረገለትን ነገር አላስታወሰም፣ ከኢየሱስ ያያቸውንና የሰማቸውንም ነገሮች አላስታወሳቸውም፡፡ አሁን ‘ይሁዳ’ ብለን የምናውቀውን አጸያፊ ባህሪ ያወቅነው ለዚህ ነው፡፡ የማስታወስ ችሎታ አንድ አገልጋይ ሊኖሩት ከሚገቡት እጅግ አስፈላጊ ከሆኑ መንፈሳዊ ባሕርያት ውስጥ አንዱ ነው፡፡ የማያስታውሱ ሰዎች፣ ስኬታማ የመሆናቸው እድል እጅግ የጠበበ ነው፡፡ በቀላሉ ወደ ተወሰኑ ከፍታዎች መድረስ ያቅታቸዋል። ይሄ የተለየ እና እምብዛም የማይታወቀው የዚህ መጽሐፍ ርዕሥ፣ ከእግዚአብሔር ለአንተ የተሰጠ ስጦታ ነው

Languageአማርኛ
Release dateJul 27, 2016
ISBN9781613954591
ዝንጉዎቹ
Author

Dag Heward-Mills

Bishop Dag Heward-Mills is a medical doctor by profession and the founder of the United Denominations Originating from the Lighthouse Group of Churches (UD-OLGC). The UD-OLGC comprises over three thousand churches pastored by seasoned ministers, groomed and trained in-house. Bishop Dag Heward-Mills oversees this charismatic group of denominations, which operates in over 90 different countries in Africa, Asia, Europe, the Caribbean, Australia, and North and South America. With a ministry spanning over thirty years, Dag Heward-Mills has authored several books with bestsellers including ‘The Art of Leadership’, ‘Loyalty and Disloyalty’, and ‘The Mega Church’. He is considered to be the largest publishing author in Africa, having had his books translated into over 52 languages with more than 40 million copies in print.

Related to ዝንጉዎቹ

Related ebooks

Reviews for ዝንጉዎቹ

Rating: 5 out of 5 stars
5/5

1 rating1 review

What did you think?

Tap to rate

Review must be at least 10 words

  • Rating: 5 out of 5 stars
    5/5
    የተወሰኑ መጽሐፍትን አንብቤያለሁ በጣም አስተማሪ መጽሐፍት ናቸው እግዝአብሔር ይባርከው እላለሁ ።

Book preview

ዝንጉዎቹ - Dag Heward-Mills

የዝንጉ ሰው ነቀፌታዎች

እግዚአብሔር፥ . . . ይረሳ ዘንድ ዓመፀኛ አይደለምና።

ዕብራውያን 6፡10

1. ዝንጉዎች ነቀፌታ አለባቸው

እግዚአብሔር፥ ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ እስከ አሁንም ስለምታገለግሉአቸው፥ ያደረጋችሁትን ሥራ ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዓመፀኛ አይደለምና።

ዕብራውያን 6፡10

ብዙ ሰዎች ስለ ‘‘አራቱ ትላልቅ’’ ኃጢአቶች ጠንቅቀው ያውቃሉ፤ መዋሸት፣ መስረቅ፣ መዘሞትና መግደል ናቸው፡፡ ሰዎችን ስለ ኃጢአት ዝርዝር ብትጠይቃቸው የመርሳትን ኃጢአት የመጥቀስ እድላቸው የጠበበ ነው። ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል በዚህ ጉዳይ ላይ ግልጽ ነው፤ መርሳት ጽድቅ አይደለም! መርሳትና ነገሮችን ልብ ሳይሉ መቅረት በእግዚአብሔር ፊት ኃጢአቶች ናቸው፡፡

በውኑ ቆንጆ ጌጥዋን ወይስ ሙሽራ ዝርግፍ ጌጥዋን ትረሳለችን? ሕዝቤ ግን የማይቈጠር ወራት ረስቶኛል።

ኤርምያስ 2፡32

ዝንጉዎች የሚረሱዋቸው አንዳንድ ነገሮች ከአይምሮ በላይ ናቸው፡፡

ከእግዚአብሔር ሐሳብ ወደኋላ ስለማፈግፈግ የሚናገረው የተለመደው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ሙሽራይቱ የሰርጓን ልብስ እንደማትረሳ ያስታውሰናል፡፡ የሰርግ ልብስ ለሙሽራይቱ ከሁሉ የተከበረ ነገር ነው፡፡

ብዙዎቹ ሙሽሮች የሰርግ ልብሶቻቸውን የሚያዘጋጁት ከሁሉ አስቀድመው ነው፡፡ ሙሽራይቱ በፍጹም ልብሷን አትረሳም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔርን መርሳት እንዲሁ የማይጠበቅ ነገር መሆኑን ይነግረናል፡፡

ሰዎች ሲያድጉ በልጅነታቸው ማን እንደተንከባከባቸው፣ እንዳሳደጋቸውና እንደወደዳቸው ይረሳሉ፡፡ ወደ ክርስቶስ ያመጣቸውን፣ በጌታ ያሳደጋቸውንና በአገልግሎት ያስቀመጣቸውን ሰው ይዘነጋሉ፡፡ በጣም አስፈላጊ በሆነው የሕይወት መንገዳቸው ጊዜ የተረዱ ሰዎች የረዷቸውን ሰዎች ሊረሱ ይችላሉን; የረዷቸውንስ ሰዎች ዞረው ያጠቁ ይሆን; መልሱ ‘‘አዎ’’ ነው! ይሄ ሁልጊዜ ይሆናል፡፡

ሰዎች ሲበለጽጉ እግዚአብሔርን ይረሳሉ፡፡ አውሮፓ እጅግ ባለጠጋ አሕጉር በመሆንዋ ምክንያት እግዚአብሔርን ትታዋለች። ነገር ግን የያዙትን ነገር ሁሉ የሰጣቸው እግዚአብሔር ነው፡፡ ሰዎች እግዚአብሔር ከሰጣቸው በኋላ እምነት የለሽ ይሆናሉ፡፡ ሁሉን ነገር የሰጠህን መርሳት ምንኛ የሚያሳዝን

ኃጢአት ነው! በእርግጥ፣ እጅግ የከፋውን ቅጣት ሊቀበል የሚገባው ጽድቅ የሌለው ነው፡፡

2. ዝንጉዎች ጻድቅ ያልሆኑና የእግዚአብሔርም ባሕርይ የሌላቸው ናቸው፡፡

እግዚአብሔር፥ ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ እስከ አሁንም ስለምታገለግሉአቸው፥ ያደረጋችሁትን ሥራ ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዓመፀኛ አይደለምና።

ዕብራውያን 6፡10

ሰው ይረሳል፤ እግዚአብሔር ግን አይረሳም! የሚረሱ ሰዎች የእግዚአብሔር ባሕርይ የላቸውም! የማይረሱ ነገሮችን መርሳት የወደቀው የኃጢአተኛው ተፈጥሮና የተበላሸው ሰው ባሕርይ መገለጫ ነው፡፡

በእግዚአብሔር ቃልና መንፈስ ቁጥጥር ስር ያለ ሰው ነገሮችን አይረሳም፡፡

ተፈጥሯዊው ሰው የረዱትን ሰዎች ማስታወስ አይፈልግም፡፡ ያልዳነው ሰው ያለፈበትን ጎዳና ማስታወስ አይሻም፡፡ አሁን ለደረሰበት ደረጃ እንዴት እንደበቃ ማንም እንዲያውቅ ፍላጎት የለውም፡፡

ነገር ግን ይሄ የእግዚአብሔር ባሕርይ አይደለም፡፡ ኢየሱስ በምድር ላይ ሲመላለስ ከየት እንደመጣ በተደጋጋሚ ነግሮናል።

በራሱም ምንም እንደማያደርግ ተናግሯል፡፡

የሚናገረው አባቱ እንዲናገር የሰጠውን ብቻ እንደሆነ በተደጋጋሚ ገልጿል፡፡

ይሄ ከንቱ ትምክህት ከሞላበት የትዕቢተኛ ሰው ባሕርይ ፈጽሞ ተቃራኒ ነው፡፡ ትዕቢተኛና ክፉ ሰው ምንጩንና መነሻውን አይናገርም፤ በራሱ እንደተሠራ ያምናል፤ በራሱ ኃይል እንደተገኘም ያስባል፡፡

3. የሚረሱ ሰዎች ጽድቅ የሌላቸውና እንዳይለመልሙ የተረገሙ ናቸው፡፡

በውኑ ደንገል ረግረግ በሌለበት መሬት ይበቅላልን? ወይስ ቄጠማ ውኃ በሌለበት ቦታ ይለመልማልን? ገና ሲለመልም ሳይቈረጥም፥ ከአትክልት ሁሉ በፊት ይደርቃል። እግዚአብሔርን የሚረሱ ሁሉ ፍጻሜአቸው እንዲሁ ነው የዝንጉም ሰው ተስፋ ይጠፋል።

ኢዮብ 8፡11-13

ዝንጉዎች እንዳይለመልሙ ሆነው የተረገሙ ናቸው፡፡ የመርሳት ኃጢአት አደገኛ ከመሆኑ የተነሣ በሚዘነጉ ላይ እርግማኖች ይዘንባሉ፡፡ ወሳኝ ነገሮችን ስትረሳ የግድ የእርግማንን ድምፅ መስማት አያስፈልግህም፡፡ የሚረሱትን እግዚአብሔር እንደሚያደርቃቸው በመጽሐፍ ቅዱስ አስቀድሞ ተጽፏል፡፡ እግዚአብሔር ያሳለፈህን ጎዳናና ለአንተ ያደረገልህን ነገሮች ሁሉ ተጠንቅቀህ አስታውስ፡፡

4. ጽድቅ የሌላቸው ሰዎች የመርሳትን አደጋዎች አያስቧቸውም

በባቢሎን ወንዞች አጠገብ በዚያ ተቀመጥን ጽዮንንም ባሰብናት ጊዜ አለቀስን።

በአኻያ ዛፎችዋ ላይ መሰንቆቻችንን ሰቀልን።

የማረኩን በዚያ የዝማሬን ቃል ፈለጉብን፥ የወሰዱንም። የጽዮንን ዝማሬ ዘምሩልን አሉን።

የእግዚአብሔርን ዝማሬ በባዕድ ምድር እንዴት እንዘምራለን?

ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ብረሳሽ፥ ቀኜ ትርሳኝ።

ባላስብሽ፥ ምላሴ በጕሮሮዬ ይጣበቅ ከደስታዬ ሁሉ በላይ ኢየሩሳሌምን ባልወድድ።

መዝሙር 137፡1-6

ማስታወስን ትልቅ ትኩረት ልትሰጠው ይገባል፡፡ ዘማሪው ኢየሩሳሌምን መርሳት አደገኛ እንደሆነ አውቋል፡፡ የመጣሁበትን ባላስታውስ ብሎ በራሱ ላይ መርገም አስቀመጠ፡፡ ይሄ የሚያሳየው የማስታወስ ርዕሰ ጉዳይ ምን ያህል ትኩረት የሚሻ እንደሆነ ነው፡፡ አንተም አንዳንድ ነገሮችን የማታስታውስ ከሆነ መኖርህን ልታቆም ትችላለህ፡፡ እግዚአብሔር ከየት እንዳነሣህ የማታስታውስ ከሆነ ምላስህ ከጉሮሮህ ሊጣበቅ ይችል ይሆናል። እግዚአብሔር ያደረገልህን ነገር በረሳህ ጊዜ ቀኝ እጆችህ ላይታዘዙልህ ይችላሉ፡፡

5. ጽድቅ የሌላቸው ሰዎች ሲጠግቡ፣ ቤት ሲኖራቸውና ባለጠጋ ሲሆኑ እግዚአብሔርን ይረሱታል፡፡

ከበላህና ከጠገብህ በኋላ፥ መልካምም ቤት ሠርተህ ከተቀመጥህበት በኋላ፥ የላምና የበግ መንጋ ከበዛልህ በኋላ፥ ብርህና ወርቅህም ያለህም ሁሉ ከበዛልህ በኋላ፥ ልብህ እንዳይጓደድ ከግብፅም ምድር ከባርነት ቤት ያወጣህን፥

ዘዳግም 8፡12-14

የመርሳት ኃጢአተኝነት በተለምዶ የሚያጠቃው ጥጋበኞችን ነው! በራሳቸው ቤት ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች እግዚአብሔርን ወደ መርሳት ያደላሉ፡፡ ባላቸው ሀብት ላይ የጨመሩትም በፍጥነት እግዚአብሔርን ረስተውታል፡፡

ሀብታምና ባለጠጋ ሆነህም ከየት እንደመጣህ የምታስብ ዓይነት ሰው መሆን አለብህ፡፡ ብዙ ሀብታሞች ብዙ እየተናገሩ ጥቂት የሚሰጡ መሆናቸው ያሳዝናል፡፡ ሰዎች እግዚአብሔር ስለሰጣቸው በረከቶች ይናገራሉ፤ ነገር ግን ስላደረገላቸው ነገር እግዚአብሔርን አያከብሩትም፡፡

6. ጽድቅ የሌላቸው ሰዎች ብዙ ጊዜ ትዕቢተኞች ናቸው

ከበላህና ከጠገብህ በኋላ፥ መልካምም ቤት ሠርተህ ከተቀመጥህበት በኋላ፥ የላምና የበግ መንጋ ከበዛልህ በኋላ፥ ብርህና ወርቅህም ያለህም ሁሉ ከበዛልህ በኋላ፥ ልብህ እንዳይጓደድ ከግብፅም ምድር ከባርነት ቤት ያወጣህን፥ በልብህም። ጉልበቴ የእጄም ብርታት ይህን ሀብት አመጣልኝ እንዳትል።

ዘዳግም 8፡12-14፣17

ትዕቢት ዋነኛው የመርሳት መነሻ ምክንያት ነው፡፡ ሰዎች እግዚአብሔር እንደረዳቸው መቀበል አይፈልጉም፡፡

በጭራሽ ሰው እንደረዳቸው መመስከር አይፈልጉም፡፡

በእርግጥ በልባቸው ራሳቸውን በራሳቸው እንደሠሩና አንተም እንደዚያው እንድታስብ ይፈልጋሉ፡፡

እነዚህ ሰዎች ለእግዚአብሔር እውቅና አይሰጡም፡፡ ልባቸውም በትዕቢት የተሞላ ነው፡፡

አስራታቸውን የማይከፍሉ ሰዎች በብልጥግናቸው ለእግዚአብሔር ሚና እውቅና አይሰጡትም፡፡ ሰዎች ልባቸው በሚታበይበት ጊዜ እንደዚህ ይላሉ፣ ‘‘አሁን ያለኝን ሀብት ለማግኘት እጅግ ጠንክሬ ሠርቻለሁ፡፡’’

የአውሮፓ ዘመናዊ አረማውያን

በአንድ አጋጣሚ እንዲት ሀብታም አውሮፓዊት ሴት በእግዚአብሔር ታምን እንደሆነ ጠየቅኋት፡፡ በመደነቅ ካየችኝ በኋላ፣ እንደዚህ ዓይነት ‘‘ተራ’’ ጥያቄ ስለጠየቅኋት ተገረመች።

‘‘በእርግጥ አላምንም፣’’ ብላ መለሰች፡፡

ወደ ደረቷ እያመለከተች እንዲህ አለች፣ ‘‘በራሴ አምናለሁ፡፡ በእግዚአብሔር ማመን ለምን አስፈለገኝ;’’

አፍሪካውያን በእግዚአብሔር የሚያምኑበት ምክንያት ለችግሮቻቸው መፍትሔዎች ስለሌሏቸው ነው ብለው ለቁጥር የሚታክቱ አውሮፓውያን ሲናገሩ ሰምቻለሁ፡፡ በአንድ ወቅት ክርስትናን በዓለም ዙሪያ ያስፋፋችው ዘመናዊቷ አውሮፓ በእምነተቢስነትና በአረማዊነት ተውጣለች፡፡ በአውሮፓ ለዚህ ሁሉ አጋንንታዊ ወረርሽኝ መነሻ የሆነው ከእግዚአብሔር ውጪ በራስ መተማመንና ጠንክሮ በመሥራት መመካት ነው፡፡ አውሮፓ ስሕተትና ክፋት ውስጥ ወድቃለች፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሔርን ረስታዋለች፡፡

7. ጽድቅ የሌላቸው ሰዎች ባለጠጋ በሚሆኑበት ጊዜ ማንንም አያስታውሱም

ሰዎች ባለጠጋ በሚሆኑበት ጊዜ ሀብታቸውን እንዴት እንዳገኙ እጅግ በቀላሉ ይረሳሉ፡፡ ሀብታቸውን በራሳቸው ጥረት እንጂ በእግዚአብሔር ጸጋ ያላገኙት ለማስመሰል ይሞክራሉ፡፡

ብዙ ሀብታሞች በቤተክርስቲያን በቋሚነት እንደማይሳተፉ አስተውለሃል; ጥቂት ባለጠጋዎች አስራት ይከፍላሉ፡፡ ብዙዎቹ አስራት ከፋዮች ግን ብዙም የተጋነነ ገንዘብ የማያገኙ ደሞዝተኞች ናቸው፡፡

Enjoying the preview?
Page 1 of 1