Discover millions of ebooks, audiobooks, and so much more with a free trial

Only $11.99/month after trial. Cancel anytime.

የትህትና ቀመር
የትህትና ቀመር
የትህትና ቀመር
Ebook182 pages1 hour

የትህትና ቀመር

Rating: 5 out of 5 stars

5/5

()

Read preview

About this ebook

ትህትና /እራስን ማዋረድ/ በጣም አስፈላጊ የሆን መንፈሳዊ ጥራት ነው፡፡ ጥቂት ሰዎች ስለዚህ ዝነኛ ነገር ግን በጣም አስፈላጊ መንፈሳዊ ጥራት ስለሆነው ለመፃፍ ደፍረዋል፡፡ በዚህ የሚስብ መጽሐፋቸው፣ ዳግ ሂዋርድ ሚልስ በአብዛኛው ሊታይ የማይችለውን ትእቢት/ኩራት ግልፅ አድርገውታል፡፡ ይህ መጽሐፍ የተጻፍው እንደኛው በትግል ውስጥ ባለ ክርስቲያን ነው፤ ይባርካችኋል እንዲሁም የኢየሱስ ክርስቶስን እንደ ህፃን አይነት ትህትና /እራስን ማዋረድ/ እንድታዳብር ያበረታታሃል፡፡

Languageአማርኛ
Release dateJul 28, 2016
ISBN9781613954348
የትህትና ቀመር
Author

Dag Heward-Mills

Bishop Dag Heward-Mills is a medical doctor by profession and the founder of the United Denominations Originating from the Lighthouse Group of Churches (UD-OLGC). The UD-OLGC comprises over three thousand churches pastored by seasoned ministers, groomed and trained in-house. Bishop Dag Heward-Mills oversees this charismatic group of denominations, which operates in over 90 different countries in Africa, Asia, Europe, the Caribbean, Australia, and North and South America. With a ministry spanning over thirty years, Dag Heward-Mills has authored several books with bestsellers including ‘The Art of Leadership’, ‘Loyalty and Disloyalty’, and ‘The Mega Church’. He is considered to be the largest publishing author in Africa, having had his books translated into over 52 languages with more than 40 million copies in print.

Related to የትህትና ቀመር

Related ebooks

Reviews for የትህትና ቀመር

Rating: 5 out of 5 stars
5/5

1 rating0 reviews

What did you think?

Tap to rate

Review must be at least 10 words

    Book preview

    የትህትና ቀመር - Dag Heward-Mills

    ካልተገለፀ በቀር፣ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ያሉ ጥቅሶች ሁሉ የተወሰዱት በ 1954 ዓ.ም. ከታተመው የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡

    Find out more about Dag Heward-Mills at:

    Healing Jesus Campaign

    Write to: evangelist@daghewardmills.org

    Website: www. daghewardmills.org

    Facebook: Dag Heward-Mills

    Twitter: @EvangelistDag

    Write to:

    Dag Heward-Mills

    P.o.Box 114

    Korle-Bu

    Accra

    Ghana

    ላይትሃውስ ቻፕል ኢንተርናሽናል

    ስልክ + 251912063821

    መ.ሳ ቁጥር 15134

    አዲስ አበባ

    ኢትዮጵያ

    ይህን መጽሐፍ በሙሉም ሆነ በከፊል ያለ አሳታሚው ፈቃድ ማባዛት የተከለከተለ ነው፡፡

    Table of Contents

    ምእራፍ 1. ራስህን ዝቅ አድርግ

    ምእራፍ 2. እንደ ህፃን ትሁት ለመሆን እንዴት እንደሚቻል

    ምእራፍ 3. እንደ አገልጋይ ራስን ዝቅ ማድረግ እንዴት እንደሚቻል

    ምእራፍ 4. ከፍ ያለ ነገር አታስብ

    ምእራፍ 5. የትዕቢት ንግግርን እንዴት መመርመር ይቻላል

    ምእራፍ 6. ትዕቢተኛ ዓይን አለህ ማለት ምን ማለት ነው

    ምእራፍ 7. ራሳስህን አዋርድ ማለት አንተው ራስህ አድርገው ማለት ነው

    ምእራፍ 8. እንደ ኢየሱሰ ክርስቶስ ትሁት አገልጋይ መሆን ምን ማለት ነው

    ምእራፍ 9. መታበይ ማለት ምን ማለት ነው?

    ምእራፍ 10. እንደ ሉሲፈር መታበይ ማለት ምንድን ነው?

    ምእራፍ 11. እንደ አስጢን መታበይ ማለት ምንድን ነው

    ምእራፍ 12. እንደ ናቡከደነፆር መታበይ ማለት ምን ማለት ነው

    ምእራፍ 13. እንደ ብልጣሶር መታበይ ማለት ምን ማለት ነው፡፡

    ምእራፍ 14. እንደ ሮብዓም መታበይ ማለት ምን ማለት ነው፡፡

    ምእራፍ 15. እንደ ፈርዖን መታበይ ማለት ምን ማለት ነው

    ምእራፍ 16. እንደ ቆሬ መታበይ ማለት ምን ማለት ነው

    ምእራፍ 17. በትዕቢት መውደቅ ምን ይመስላል?

    መታሰቢያነቱ

    ይህን መጽሐፍ ለጓደኛዬ ለሬቨረንድ ሰቲቭ ሜንሳ መታሰቢያነት አበርክቻለሁ፡፡ ለብዙ አመታት ጓደኝነትህና አብረን ስላሳለፍናቸው ጌዜያታቶች በሙሉ አመሰግንሃለሁ፡፡ ይህን ለማስተማር ስላነቃቃኝ  እራስን ዝቅ ማድረግ ለሚለው የሚያስደንቀው መልእክትህ አመሰግናለሁ፡፡

    ምእራፍ 1

    ራስህን ዝቅ አድርግ

    በጌታ ፊት ራሳችሁን አዋርዱ ከፍ ከፍም ያደርጋችኋል።

    ያዕቆብ 4፡10

    ሰዎች ትዕቢትን በተለያየ መንገድ ይገልፁታል፡፡ ዝምተኛ ሰው ከመሆንህ የተነሳ ሰዎች ትዕቢተኛ ነው ሊሉህ ይችላሉ፡፡ ረጅምና ልበሙሉ ከመሆንህ የተነሳም ሰዎች ትዕቢተኛ ነው ሊሉህ ይችላሉ፡፡ ሰዎች ጥሩ፣ አብረቅራቂና የሙቀት መጠን መቆጣጠሪያ የተገጠመለትን መኪና በመንዳትህ ትዕቢተኛ ነው ሊሉህ ይችላሉ፡፡

    ስለዚህ በእውነት ትዕቢት ምንድን ነው? ትሁት ወይም ትዕቢተኛ መሆንህ የሚያመጣው ለውጥ አለን? በእርግጥ የሚያመጣው ለውጥ አለ! ራሳችን በጌታ ፊት ማዋረድ አለብን፡፡ እግዚአብሔር ራሳችንን ዝቅ እድናደርግ በሚፈልግበት መንገድ መኖር አለብን፡፡

    ትዕዛዙ ግልፅ ነው! በሰው ፊት ሳይሆን ራሳችሁን በጌታ ፊት አዋርዱ፤ እግዚአብሔር ሊቀበለው የማይችል ዓይነት ትህትናን በመለማመድ ምንም ነገርን ማግኘት አንችልም፡፡ ትህትና በእግዚአብሔር በራሱ ብቻ የሚተረጎምና የሚገለፅ ጉዳይ ነው፡፡ የሰው ልጆች ትህትናን በተለያየ መንገድ ይተረጉሙታል ነገር ግን  በእግዚአብሔር ትርጓሜ ትህትና ለእኛ ካለው ፋይዳ አንጻር የሚታይ ነው፡፡

    ትህትና የእግዚአብሔርን ቃል ርዝመቱንና ጥልቀቱን መርምረን ምን እንደሆነ እስክንረዳ ድረስ በጣም አስፈላጊ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ስለ ትዕቢት የተገለፁት ማስጠንቀቂያዎችን መዘንጋት አደገኛ ነው፡፡

    በዚህ በመጀመሪያው ምእራፍ በጌታ ፊት ራሳችን የምናዋርድባቸውን ምክያቶች እንድናይ እፈልጋለሁ፡፡

    ሰባት ራስህ ዝቅ የምታደርግባቸው ምክንያቶች

    1. እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ስለሚቃወም ራስህን አዋርድ

    ነገር ግን ጸጋን አብልጦ ይሰጣል፤ ስለዚህ፦ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል።

    ያዕቆብ 4፡6

    ትዕቢት የእግዚአብሔር ተፃራሪ ስለሆነ እርሱ በትዕቢተኞች ላይ ጦርነትን አውጇል፡፡ ትዕቢተኛ ስትሆን እግዚአብሔር ጠላትህ ይሆናል የምትሰራውንም ሁሉ ይቃወማል፡፡

    ትዕቢተኛ የሆኑ ሰዎች እግዚአብሔር እየተቃወማቸው እንደሆነ እንኳን አያውቁም፡፡ አንዳንድ ጊዜ ክርስቲያኖች ሰይጣን እየተዋጋቸው እንደሆነ ስለሚያስቡ ዲያቢሎስን ሲቃወሙ ይታያል፡፡ ነገር ግን ትዕቢተኛ ክርስቲያኖችን በተመለከተ ዲያቢሎስ የእረፍት ጊዜውን ሊወስድ ይችላል፡፡ እግዚአብሔር ራሱ በመቆጣጠር ትዕቢተኞችን ይቃወማቸዋል፡፡

    እግዚአብሔር አንተንና ትዕቢትህን በመቃወሙ አንተም እሱን እየተቃወምክ ይሆናል፡፡ እኔ እግዚአብሔርን መቃወም አልፈልግም፣ አንተስ? እግዚአብሔር ጠላቴ እንዲሆን ፈፅሞ አልፈልግም፡፡ እግዚአብሔር ጣላትህ እንዲሆን ትፈልጋለህን? ባለህበት ሁኔታ የሚወድህ እግዚአብሔር እሱ ብቻ ነው፡፡ እሱ ጠላትህ ከሆነ እንግዲህ ምን ቀረህ?

    2. እግዚአብሔር ሰዎች ትሁት የሚሆኑበትን ጸጋ  ስለሚሰጥ ራስህን አዋርድ

    ነገር ግን ጸጋን አብልጦ ይሰጣል፤ ስለዚህ፦ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል።

    ያዕቆብ 4፡6

    በጣም አስደናቂ የሆነው ነገር እግዚአብሔር ለትሑታን የማይገባቸውን ዕርዳታ መስጠቱ ነው፡፡ ጸጋ  ሊገባን የማይችል ድጋፍና ሞገስ ነው ራስህን ዝቅ ባደረግህ ጊዜ እግዚአብሔር ጸጋ ን ላንተ በመላክ ምላሽን ይሰጥሃል፡፡ እራስን የማዋረድን ትሁት መንገድ በመከተልህ የማይገባንን ዕርዳታ መቀበል እንዴት ደስ የሚል ነገር ነው! ከዚህ የተለየ ራስህን ዝቅ የምታደርግበት ምክንያት ሊኖር አይችልም፡፡ ራስህን ዝቅ ስታደርግ ለሕይወትህና ለአገልግሎትህ ስለምታገኘው ያልተገባ ዕርዳታ አሰብ፡፡

    እግዚአብሔር ለቤተክርስቲያንህ ከማይገባንን ዕርዳታን እንዲሰጥ ትሻለህን? ለእረኝነት አገልግሎትህ እግዚአብሔር ፈፅሞ የማይገባንን ዕርዳታ እንዲያደርግልህ ትፈልጋለህን?  ይህንን ከፈለክ ራስህን ዝቅ አድርግ! ለወንጌል ሰርጭት አገልግሎትህ እግዚአብሔር ፈፅሞ የማይገባንን ዕርዳታ እንዲያደርግልህ ትፈልጋለህን?  ራስህ ዝቅ አድርግ!

    በገንዘብህ ላይ እግዚአብሔር የማይገባህን እርዳታ እንዲሰጥህ ትፈለጋለህን? ራስህን ዝቅ አድርግ! በሞራላዊ ሕይወትህ እግዚአብሔር እንዲረዳህ ትፈልጋለህን? ራስህን ዝቅ አድርግ! በቅድስና ሕይወት ለመኖር እንደትችል እግዚአብሔር አብዝቶ አንዲረዳህ ትሻለህ፣ ያን ጊዜ ራስህን ዝቅ አድርግ! በአብዛኛው ሁሉም መንፈሳዊ እንቅስቃሴዎች በትህትና የታገዙ ናቸው፡፡

    ራስህን ዝቅ ባደረግህ ጊዜ መለኮታዊ ጸጋ  ይሰጥሃል፡፡  ሞክረህ እየው፡፡ ትሁት ሁን! እንደ ሕፃን ሁን እና አገልግል በሕይወትህ ለውጥ የማይጀምር እንደሆን ተመልከት፡፡

    ትዳርህ እንዴት ነው? አስቸጋሪ በሆነው ግንኙነትህ ላይ እግዚአብሔር እንዲረዳህ ትፈልጋለህ? ራስህን ዝቅ ማድረግ ላንተ አስፈላጊ የሆነውን የማይገባህን ዕርዳታ ለማግኘት ቁልፍ ነው፡፡

    3. ራስህን ዝቅ አድርግ ምክንያቱም በሕወትህ ወደሚቀጥለው ምእራፍ ከፍ የምትለው በርሱ ነውና

    በጌታ ፊት ራሳችሁን አዋርዱ እርሱም ከፍ ደርጋችኋል፡፡

    ያዕቆብ 4፡10

    ራስህን ዝቅ ማድረግ የሚያስፈልግበት ቀጣዩ ምከንያት ለእድገት ነው፤ ከፍ ማለትንና ማደግን የማይፈልግ ማነው? የጌታ ከፍ ማድረግ እና ማክበር እራስህን ዝቅ በማድረግህ የሚሰጡህ ስጦታዎች ናቸው፤ የእግዚአብሔርን ቃል በሚገባ አስተውል፡፡ ወደታች ዝቅ ባልህ ጊዜ እግዚአብሔር ከፍ ያደርግሃል፡፡

    መብዛትንና ከፍ ማለትን እየፈለከው አይደለምን? ስለዚህ ራህን ዝቅ አድርግና አገልጋይም ሁን! ራስህን ዝቅ አድርግና የሚሰለጥንና የሚማር ልጅ ሁን፡፡ ራስህን አሁን ካለህበት ደረጃ ወጥተህ ፈፅሞ አልመህ በማታውቀው ደረጃ ላይ ታገኘዋለህ፡፡

    እንግዲህ በጊዜው ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከኃይለኛው ከእግዚአብሔር እጅ በታች ራሳችሁን አዋርዱ፤

    1ኛ የጴጥሮስ 5፡6

    እስቲ ስለዚህ ነገር አስብ፡፡ ከፍ እንዲያደርጋችሁ ሲል ምን ማለቱ ነው? ከፍ ማለት ትርጉሙ ወደ ውብና አንፀባራቂ ልዕቀት በክብር ወደላይ መነሳት ነው፡፡ያ የምትፈለገው ነገር አይደለምን? ትህትና ወደዚህ ደረጃ የምትደርስበት ቁልፍ ነው

    4. ራስህ ዝቅ አድርግ ከላላና ጥበቃን ታገኛለህና

    እንዲሁም፥ ጐበዞች ሆይ፥ ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ታጠቁ፥ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል።

    1ኛ የጴጥሮስ 5፡5

    ትህትና መንፈሳዊ ከለላ ነው፡፡ ትህትና አመለካከት አይደለም፡፡ ትህትና የድህነት አና በቀላሉ የመኖር ዘዴ አይደለም፡ ትህትና ዓይንአፋርነትና የተሸነፈ የመመምሰል ጥበብ አይደለም፡፡ እውነታው

    ትሀትና  ራስህን የሚሸፍንህ መንፈሳዊ ካባ ነው፡፡ ክርስቲያኖችን በርካታ ከሆኑ ከማይታዩና ከመንፈሳዊ ጥፋቶች የሚጠብቅ ነው፡፡ ትህትናን ተላበስ በዚህ ሕይወት ካሉ ብዙ ጥፋቶች ትሸፈናለህ፣ ነፃ ትወጣለህ አንዲሁም ትጠበቃለህ፡፡

    5. ራስህን ዝቅ አድርግ ምክንያቱም ትዕቢትህ እየቀረበ ለመጣው ለጥፋትህ፣ ለውድቀትህና ለውርደትህ ምልክት ነው፡፡

    ሰውን ትዕቢቱ ያዋርደዋል መንፈሱን የሚያዋርድ ግን ክብርን ይቀበላል።

    ምሳሌ 29፡23

    ትዕቢት ጥፋትን፥ ኵሩ መንፈስም ውድቀትን ይቀድማል።

    ምሳሌ 16፡18

    ትዕቢት ከመጣች ውርደት ትመጣለች በትሑታን ዘንድ ግን ጥበብ ትገኛለች።

    ምሳሌ 11፡2

    ትዕቢት ምልክት ነው! እየመጣ ያለውን ውድቀት፣ እየመጣ ያለውን ችግርና እየመጣ ያለውን ክፉ ነገር አመላካች ነው፡፡ ራህ ዝቅ ማድረግህ በሕይወትህና በአገልግሎትህ ሊከሰት ያለውን አደጋ ያስወግዳል፡፡ ሰይጣን በአንተ በራስህ ከፍ ማለትና ከቅጥ ባለፈ ድፍረት በሆነ ንግግርህ ይሳባል፡፡ እነዚህ ለእሱ የተከፈቱ በሮች ናቸው፡፡

    ትዕቢት የውርደት አጋንንቶች፣ ጥፋትና ሽንፈት የሚሰባሰቡበት መንፈሳዊ ምልክት ነው፡፡ ትዕቢትህ ለክፉ መናፍስት ግልጽ ጥሪን እንደምታቀርብበት ጥሩንባን ይመስላል፡፡ ትዕቢተኛ ከሆንክ  መላዕክት አንተን ለመርዳት አይላኩልህም፡፡ ትዕቢተኛ በሆንክ ጊዜ አጋንንት አንተን ለማጥፋት ይሰባሰባሉ፡፡ ለአጋንንት በቀላሉ የተጋለጥህ ትሆናለህ ምክያቱም መንፈሳዊው ካባህና ልብስ ከላይህ ተገፍፏልና፡፡

    6. በጌታ ፊት ራስህን ዝቅ አድርግ ምክንያቱም ትዕቢት ከመነሻው ሰይጣናዊና አጋንንታዊ ነውና፡፡

    በውኑ አዞውን በመቃጥን ታወጣለህን? ምላሱን በገመድ ታስረዋለህን? ወይስ ስናጋ በአፍንጫው ታደርጋለህን? ከፍ ያለውን ሁሉ ይመለከታል በትዕቢተኞችም ሁሉ ላይ ንጉስ ነው፡፡

    ኢዮብ 40፡25-26

    ሁሉም ትዕቢተኛ ሰዎች ንጉስ አላቸው ያም ንጉስ ሰይጣን ነው፡፡ ሰይጣን የሁሉም ትዕቢተኞች ንጉስ ነው፡፡ ራስህን ትሁት ለማድረግ መወሰን ይኖርብሃል፡፡ እንደዚያ ካደረግህ ሰይጣን ንጉስህ ገዢህ አይሆንም፡፡ አንድ ጊዜ በትዕቢት መመላለስ ከጀመርክ  በራሱ በሰይጣን ገዢነት ስር ትኖራለህ እንዲሁም ትመላለሳለህ፡፡

    ትዕቢት ከመሰረቱ አጋንንታዊና ሰይጣናዊ ነው፡፡ ሰይጣን ከሰማይ የተጣለው በክፉ

    Enjoying the preview?
    Page 1 of 1