Discover millions of ebooks, audiobooks, and so much more with a free trial

Only $11.99/month after trial. Cancel anytime.

አሥራት የማይከፍሉ ክርስቲያኖች ለምን ድሀ እንደሚሆኑ . . . እ...
አሥራት የማይከፍሉ ክርስቲያኖች ለምን ድሀ እንደሚሆኑ . . . እ...
አሥራት የማይከፍሉ ክርስቲያኖች ለምን ድሀ እንደሚሆኑ . . . እ...
Ebook283 pages1 hour

አሥራት የማይከፍሉ ክርስቲያኖች ለምን ድሀ እንደሚሆኑ . . . እ...

Rating: 0 out of 5 stars

()

Read preview

About this ebook

ይህ ጥንታዊ የመስጠት ግንዛቤ አይሁዳውያኖችን ወደ ታዋቂ ሐብት ያደረሳቸው ቢሆንም እንኳን ብዙ ሰዎች ከአሥራት መክፈል አስተሳሰብ ጋር ይታገላሉ፡፡ በዚህ መጽሓፍ ውስጥ ቢሾፕ ዳግ ሂዋርድ ሚልስ አሥራት መክፈል እንዴት አድርጎ ሐብትን ለማፍራትና የብልጽግናን ተአምራት እንደሚያጠንክር ያስተምረናል፡፡ ከዳግ ሂዋርድ ሚልስ ምርጥ ርዕሶች አንዱ በሆነው በዚህ መጽሐፍ ተባረክ፡፡

LanguageEnglish
Release dateJul 27, 2016
ISBN9781683981244
አሥራት የማይከፍሉ ክርስቲያኖች ለምን ድሀ እንደሚሆኑ . . . እ...
Author

Dag Heward-Mills

Bishop Dag Heward-Mills is a medical doctor by profession and the founder of the United Denominations Originating from the Lighthouse Group of Churches (UD-OLGC). The UD-OLGC comprises over three thousand churches pastored by seasoned ministers, groomed and trained in-house. Bishop Dag Heward-Mills oversees this charismatic group of denominations, which operates in over 90 different countries in Africa, Asia, Europe, the Caribbean, Australia, and North and South America. With a ministry spanning over thirty years, Dag Heward-Mills has authored several books with bestsellers including ‘The Art of Leadership’, ‘Loyalty and Disloyalty’, and ‘The Mega Church’. He is considered to be the largest publishing author in Africa, having had his books translated into over 52 languages with more than 40 million copies in print.

Read more from Dag Heward Mills

Related to አሥራት የማይከፍሉ ክርስቲያኖች ለምን ድሀ እንደሚሆኑ . . . እ...

Related ebooks

Christianity For You

View More

Related articles

Reviews for አሥራት የማይከፍሉ ክርስቲያኖች ለምን ድሀ እንደሚሆኑ . . . እ...

Rating: 0 out of 5 stars
0 ratings

0 ratings0 reviews

What did you think?

Tap to rate

Review must be at least 10 words

    Book preview

    አሥራት የማይከፍሉ ክርስቲያኖች ለምን ድሀ እንደሚሆኑ . . . እ... - Dag Heward-Mills

    አሥራት የማይከፍሉ ክርስቲያኖች ለምን ድሀ እንደሚሆኑ . . . እና  አሥራት የሚከፍሉ ክርስቲያኖች እንዴት ሀብታም መሆን እንደሚችሉ

    ዳግ ሂዋርድ ሚልስ

    ካልተገለፀ በቀር፣ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ያሉ ጥቅሶች ሁሉ የተወሰዱት በ1954 ዓ.ም. ከታተመው የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ነው።

    Find out more about Dag Heward-Mills

    Healing Jesus Crusade

    Write to: evangelist@daghewardmills.org

    Website: www. daghewardmills.org

    Facebook: Dag Heward-Mills

    Twitter: @EvangelistDag

    ISBN: 978-1-68398-124-4

    ላይትሃውስ ቻፕል ኢንተርናሽናል

    መ.ሳ ቁጥር 15134

    አዲስ አበባ

    ኢትዮጵያ

    መታሰቢያነቱ

    ለ ዶክተር ቻርልስ ኦሴይ

    የግል ጓደኛዬ ስለሆንህና በዓመታት መካከል ከጎኔ ስለቆምህ አመሰግንሃለሁ።

    ይህንን መጽሐፍ በሙሉም ሆነ በከፊል ያላሳታሚው ፈቃድ ማባዛት የተከለከለ ነው።

    ማውጫ

    አሥራትየማይከፍሉለምንድሀእንደሚሆኑስድስትምክንያቶች

    አሥራትየማይከፍሉትንየሚከተሉእርግማኖች

    እግዚአብሔርንመስረቅምንማለትእንደሆነ

    አሥራትየማይከፍሉሰዎችሃያመንፈሳዊችግሮች

    በገንዘብ  ወደ ጥቅም አልባነትየሚያወርዱሰባትእርምጃዎች

    አሥራት የማይከፍሉ ሰዎች ያሏቸው መጥፎ ሃሳቦች

    እግዚአብሔርንለሚረሱናአሥራትለማይከፍሉየተነገሩትንቢታዊማስጠንቀቂያዎች

    እያንዳንዱክርስቲያንስለአሥራትማወቅየሚገባውሰባትነገሮች

    እግዚአብሔርየአሥራትንሥርዓትለምንእንደመሠረተ

    ሰባትፈር ቀዳጅአሥራት ከፋዮች

    የአይሁድ ታሪካዊሀብት

    የአይሁድሀብትምስጢራት

    ዘመናዊውራባይስለብልጽግናሲያስተምር

    አሥራትከፋዮችየሀብትፈጠራሕጎችንእንዴትእንደሚያሟሉ

    አሥራትከፋዮችየመዝራትንናየማጨድንሕጎችእንዴትእንደሚቀሰቅሱ

    አሥራትከፋዮችእንዴትእግዚአብሔርቤትእንዲሠራላቸውእንደሚያደርጉ

    አሥራትከፋዮችእንዴትየእግዚአብሔርንቸርነትእንደሚቀሰቅሱ

    አሥራት ከፋዮችእንዴትምጽዋትመስጠትንእንደሚያነሣሡ

    አሥራትከፋዮችበሕይወታቸውእንዴትሰማያትንእንደሚከፍቱ

    አሥራትንበምትከፍልበት ማናቸውም ወቅትሁሉየሚሆኑአሥርነገሮች

    አሥራትን መክፈል ለምን የአገልግሎት የመጀመሪያ እርምጃ እንደሚሆን

    አሥራትለአንዳንድሰዎችየማይሠራላቸውአሥርምክንያቶች

    ክፍል 1

    አሥራት የማይከፍሉ ክርስቲያኖች ለምን ድሀ እንደሚሆኑ

    ምዕራፍ 1

    አሥራት የማይከፍሉ ለምን ድሀ እንደሚሆኑ ስድስት ምክንያቶች

    አሥራት የማይከፍሉ ድሀ የሚሆኑት ምንም የሚሰበስቡት መከር ስለሌላቸው ነው።

    ነፋስን ዘርተዋል፣ ዐውሎ ነፋስንም ያጭዳሉ፡ አገዳ የለውም፣ ከፍሬውም ዱቄት አይገኝም ቢገኝም እንግዶች ይበሉታል።

    ሆሴዕ 8፡7

    የብልጽግና መሠረታዊ ቅርጹ የአንድ ሰው ዘርን መዝራትና በኋላም በምላሹ መከርን መሰብሰቡ ነው። አሥራትን አለመክፈል አንድን ሰው ከዚህ መሠረታዊ የመዝራትና የማጨድ መርህ ውጭ ያደርገዋል። አሥራትህን ሳትከፍል ስትቀር የብልጽግናህን መሠረቶች ስለምትንድ የገንዘብህን አቋም ትጎዳለህ።

    አሥራት የማይከፍሉ ድሀ የሚሆኑት በረከቶችን ወደ ሕይወታቸው ስለማይስቡ ነው።

    በቤቴ ውስጥ መብል እንዲሆን አሥራቱን ሁሉ ወደ ጎተራ አግቡ የሰማይንም መስኮት ባልከፍትላችሁ፥ በረከትንም አትረፍርፌ ባላፈስስላችሁ በዚህ ፈትኑኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፦

    ሚልክያስ 3፡10

    አሥራት መክፈል የእግዚአብሔር ቃል እንደሚናገረው የተለያዩ ዓይነት በረከቶችን ይስባል። የተባረከ ሰው ሞገስና ረድኤት ያገኘ ሰው ነው። የምድር ሕይወታችን በጣም አስቸጋሪ ነው። ፈርዖን ዕድሜህ ምን ያህል ነው? ብሎ ያዕቆብን ስለ ሕይወቱ በጠየቀው ጊዜ እንዲህ አለ፣ ያዕቆብም ለፈርዖን አለው። የእንግድነቴ ዘመን መቶ ሠላሳ ዓመት ነው። የሕይወቴ ዘመኖች ጥቂትም ክፉም ሆኑብኝ፥ አባቶቼ በእንግድነት የተቀመጡበትንም ዘመን አያህሉም (ዘፍጥረት 47፡9)።

    ኢዮብም እንደዚሁ የሰው ልጅ ዕድሜ ጥቂትና በመከራ የተጨናነቀ መሆኑን ተናገሯል። በሕይወትህ ምንም ዓይነት መርገም ባይኖርብህም እንኳ ብዙ ችግሮችና መከራዎች ይገጥሙሃል። አሥራትህን ሳትከፍል ስትቀር በሕይወት ውስጥ የሚንሰራፉትን ችግሮች የሚቋቋምልህን በረከት ታጣለህ። መከራ ባንዣበበት ኑሮህ ላይ ምንም ዓይነት የበረከት ቃል ካልፈሰሰ እንዴት መሻሻል ትችላለህ? አሥራት የማትከፍል ሆነህ በሕይወትህ ላይ የድህነት ክምር ቢጫንብህ አይድነቅህ። አሥራት በሚከፍል ሰው ላይ ባለጸጋ የሚያደርግና ሐዘንን የሚያርቅ በረከት በብዛት ይመጣለታል።

    አሥራት የማያወጡ ድሀ የሚሆኑት የተረገሙ ስለሆኑ ነው።

    ሰው እግዚአብሔርን ይሰርቃልን? እናንተ ግን እኔን ሰርቃችኋል። እናንተም የሰረቅንህ በምንድር ነው? ብላችኋል። በአሥራትና በበኵራት ነው።

    እናንተ፥ ይህ ሕዝብ ሁሉ፥ እኔን ሰርቃችኋልና በእርግማን ርጉሞች ናችሁ።

    ሚልክያስ 3፡8-9

    አሥራት በማይከፍሉ ሰዎች ላይ የተለየ እርግማን አለ። ይህ እርግማን በዓለም ላይ ከሚታወቁ ታላላቅ ሃያ አምስት እርግማኖች አንዱ ነው። ይህ እርግማን አሥራት በማይከፍሉ ሰዎች ላይ ከሚፈሰሱት ከአዳም፣ ከኖኅና ከሌሎች ትውልዶች ተላልፎ ከመጡት እርግማኖች ላይ ተጨማሪ ነው። አሥራት በማይከፍሉ ሰዎች ላይ የሚመጣው እርግማን በወላጆችህና በቀደምት አባቶችህ ላይ በደረሰውና በተወላጆቻቸው ላይም በተላለፈው እርግማን ላይ በመደረብ ይሠራል። ሁላችንም በአንድም ሆነ በሌላ ምክንያት ከሠሩት ነገሮች የተነሣ የተረገሙ ሰዎች ተወላጆች ነን ማለት ያስደፍራል።

    አንድ ቀን፣ ቀደምት አባቶቼ የባሪያ ፈንጋዮች እንደነበሩ ስደርስበት በጣም ተጨነቅሁ። ለባሪያ ንግድ የተመሠረተ ጥንታዊ ወደብ በአባቴ ከተማ መኖሩንም ደረስሁበት። ከዚህም የተነሣ እኔ ለምርኮ ካልተሸጡ ሰዎች የአንዱ ተወላጅ መሆኔ ግልጽ ነው። ስለዚህም እኔ ወንድሙን ለባርነት አሳልፎ የሸጠ የአንድ ሰው ተወላጅ መሆኔ የሚያስኬድ ነገር ነው። ወንድምህን አሳልፎ መሸጥ በእርግጥ በቤተሰብህ ውስጥ እርግማንን ያመጣል። ወንድሞቻቸውን ለመስተዋትና ለርካሽ ጌጣጌጥ አሳልፈው የሸጡ ሰዎች የሚኖሩባቸው ቦታዎች ዛሬ በዓለም ላይ ለምን በድህነት አረንቋ የሚማቅቁ እንደሆነ ጠይቀህ አታውቅም?

    በመሆኑም አሥራትን አለመክፈል በሕይወትህ ላይ ከእነዚህ እርግማኖች ላይ ተጨማሪ እርግማንን ያስከትላል። ቀድሞውንም በአዳም እርግማን ምክንያት እየተሠቃየህ እንዳለህ አትዘንጋ። በተጨማሪም የካም ተወላጅ ከሆንህ ደግሞ በካም እርግማን ምክንያትም እየተጎሳቆልህ ትሆናለህ።

    ወድ ወዳጄ ሆይ፣ ከዚህ በላይ ምን ያህል መሸከም ትችላለህ? በረከትን የሚያመጣ አንድን ነገር ለማድረግ አሁን ጊዜው አይመስልህም? እነዚህን ሁሉ ጠንቀኛ እርግማኖች እንድትቋቋም የአሥራት መክፈልን በረከት ማግኘት ያስፈልግሃል! ታዲያ አሥራትህን ለመክፈል እምቢ ባልህ መጠን የባሰ እየደኸየህ መሆንህ የሚያስገርም ነውን?

    አሥራት የማይከፍሉ ድሀ የሚሆኑበት ምክንያት ነቀዞች ያለማቋረጥ ሀብታቸውን ስለሚበዘብዟቸው ነው።

    ስለ እናንተ ነቀዙን እገሥጻለሁ፥ የምድራችሁንም ፍሬ አያጠፋም

    በእርሻችሁም ያለው ወይን ፍሬውን አያረግፍም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፦

    ሚልክያስ 3፡11

    አሥራት መክፈል የሚያስገኘው ከፍተኛ በረከት እግዚአብሔር ለአንተ ነቀዙን መገሠጹ ነው። የድሀ አገሮች መሪዎች ሲናገሩ ከሰማሃቸው ትንሽ ተጨማሪ ገንዘብ ቢያገኙ ችግራቸው ሁሉ እንደሚወገደላቸው ከአባባላቸው ትረዳለህ። ነገር ግን እውነቱ ይህ አለመሆኑ ያሳዝናል። እስካሁን ድረስ እንኳ በዓይነተኛ ድህነት የሚማቅቁት ብዙ የገንዘብ ድጋፍ የሚቀበሉ አካባቢዎች ናቸው። ይህ እንቆቅልሻዊ ገጽታ የሚታየው የገንዘቡ ተቀባዮች የተሰጣቸውን ገንዘብ ለመያዝ ባለመቻላቸው ነው።

    ቀዳዳ ያለበትን ባልዲ ለመሙላት የሚያስፈልግህ ምን እንደሆነ አስበህ ታውቃለህ? ሀብት ውኃ የተሞላ ባልዲ ሆኖ ፍቺ የሚሰጠው ቢሆን፣ እንዲህ ያለውን ባልዲ ለመሙላት የሚያስፈልግህ ውኃ ብዙ በሆነ ነበር። ነገር ግን ቀዳዳዎቹ ከተደፈኑ ባልዲውን ለመሙላት የሚያስፈልግህ ትንሽ ውኃ ብቻ ነው።

    ይህ ነቀዙ ከተገሠጸ በኋላ የሚገኝ ምስጢራዊ በረከት ነው። ነቀዙ ከተገሠጸ በኋላ አንተን ሀብታም ለማድረግ የሚያስፈልግ ነገር ቢኖር ጥቂት ነገር ብቻ ይሆናል። ይሁንና እንዲህ ዓይነቱ በረከት ከሌለህ የተሻሉ ሥራዎችን ብትፈልግም፣ ከዚያም የተሻለ ገንዘብ ብታገኝም፣ ነገር ግን ሁልጊዜም ሀብታም መሆን አይሳካልህም። ነቀዙ ከተገሠጸ ያን ያህል አታገኝ ይሆናል ነገር ግን ባልዲዎችህ በፍጥነት ይሞላሉ። ከዚያም ወዲያው ሞልተው መፍሰስ ይጀምራሉ።

    ውድ ወዳጄ አሥራትህን በምትከፍልበት ጊዜ እግዚአብሔር ሊያደርግልህ የገባው ተስፋ ይህ ነው። ዛሬውኑ ከድህነትህ ውጣና ነቀዙ ከተገሠጸ በኋላ የሚመጣውን በረከት ተቀበል። ሰዎች በመካከለኛው ዕድሜያቸው ለምን ትልቅና ወፍራም እንደሚሆኑ ጠይቀህ ታውቃለህ? ሰዎች ብዙ ጊዜ በዚህ ዕድሜ አብዝተው አይበሉም። እንደ እውነቱ ከሆነማ በመካከለኛ ዕድሜ ያሉ ብዙ ሰዎች ክብደታቸውን ለመቀነስ ምግብ ይቀንሳሉ። እንዲህም አድርገው ክብደታቸው ይጨምራል። ይህ የክብደት መጨመር ምክንያቱ ምንድን ነው? ሰዎች ዕድሜአቸው እየጨመረ ሲሄድ የበሉትን ምግብ ለሰውነት አገልግሎት የመለወጥ ዓቅማቸው ያሽቆለቁላል። በሌላ አነጋገር ስብን የሚያቃጥለው እሳት ያንሳል ማለት ነው። በሰውነት ውስጥ ስብን የሚያቃጥለው እሳት በየቀኑ አስር ልኬቶችን ያቃጥል ከነበረ ወደ አምስት ያዘቀዝቃል እንደ ማለት ነው።

    ከዚያም በድንገት በየቀኑ ያልተቃጠለ አምስት ልኬት ስብ በሰውነትህ ውስጥ መከማቸት ይጀምራል። ያለ ምንም ጥረት ክብደት ትጨምራለህ፣ እየሰፋህ እየሰፋህም ትሄዳለህ። የአንድን ሰው ዕድሜ በሰውነቱ መጠን የምታውቀው ለዚህ ነው። እያረጀህ ስትሄድ ንጥረ ምግብን ለሰውነት አገልግሎት የመለወጡ ሂደት እየቀነሰ ይሄዳል (ነቀዙ ተገሥጾአል)፣ የክብደት ጭመራውም (ብልጽግናው) መከሰት ይጀምራል።

    በእርግጥ አሥራት የማይከፍሉ እየደኸዩ የሚሄዱበት ምክንያት በቁጥጥር ሥር ያልዋለ ነቀዝ በሕይወታቸው ስስላለ ነው።

    አሥራት የማይከፍሉ የሚደኸዩት የማሳቸው ፍሬዎች ያለማቋረጥ ስለሚጠፉ ነው።

    ስለ እናንተ ነቀዙን እገሥጻለሁ፥ የምድራችሁንም ፍሬ አያጠፋም በእርሻችሁም ያለው ወይን ፍሬውን አያረግፍም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፦

    ሚልክያስ 3፡11

    በብክነት፣ ሥርዓት በጎደለው አያያዝ፣ በግዴለሽነት፣ በእሳት፣ በአደጋዎች፣ በዓመፆች፣ በስርቆትና በጦርነትም ያፈራኸውን ያለ አግባብ ማጣት ጎጂ ቢሆንም ይህ በእርግጥ የአጥፊው ሥራ ነው። አሥራት የመክፈል በረከቶች ከሆኑት አንዱ ነቀዙ መገሠጹ ነው። አጥፊው የነቀዙ ወንድም ነው። በነቀዙና በአጥፊው መካከል ያለው ልዩነት አጥፊው ሀብትህን በሚጎዳ ሁኔታና በጭካኔ ማስወገዱ ነው። የሀብትህ አጥፊ በአንተ ላይ ሲሠራብህ ማየት እጅግ ያማል። ምክንያቱም በእንዲህ ዓይነት የሚገጥምህን ጥፋት ለመቀበል ትርጉም አልባ ሆኖ ስለሚሰማህ ነው። አሥራትህን መክፈል ጀምር፣ እግዚአብሔር የሀብትህን አጥፊ እንደሚገሥጽ ተስፋ ገብቷል።

    አሥራት የማይከፍሉ ክርስቲያኖች ድሆች የሚሆኑት መከራቸውን ለመሰብሰብ ዕድል ከማግኘታቸው በፊት ፍሬዎቻቸውን ስለሚነጠቁ ነው።

    ስለ እናንተ ነቀዙን እገሥጻለሁ፥ የምድራችሁንም ፍሬ አያጠፋም በእርሻችሁም ያለው ወይን ፍሬውን አያረግፍም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፦

    ሚልክያስ 3፡11

    አሥራት የማይከፍሉ ክርስቲያኖች የሚደኸዩበት ሌላኛው ምክንያት የመከራቸውን ፍሬ ለመሰብሰብ ዕድል ከማግኘታቸው በፊት ስለሚጠፋባቸው ነው። አሥራት የማይከፍሉ የጠፋ መከር እርግማን አለባቸው። የጠፋ መከር የሚያሳየው ላፈሰስኸው ቅሪት ተመጣጣኝና ተገቢ መከርን መሰብሰብ አለመቻልን ነው።

    የሆነ ሰው ጠንክረህ ብትሠራ ሀብታም ትሆናለህ እያለ በልበሙሉነት ያስተምር ነበር። በመቀጠልም፣ ሀብታም ያልሆኑ ሰዎች ጠንክረው የማይሠሩ ናቸው። በማደግ ላይ ያሉ አገሮች ወገባቸውን ታጥቀው መሥራት ይገባቸዋል፣ ያን ጊዜ ብልጽግና ዕድል ፈንታቸው ይሆናል በማለት ተናገረ።

    ነገር ግን ዞር ብለህ ብታይ፣ ላባቸውን እያንጠፈጠፉ የሚሠሩ ሰዎችን ትመለከታለህ። ሆኖም ግን እነዚህ ሰዎች ሀብታሞች አይደሉም! ራሳቸው እስከሚዞር በየቀኑ ለአሥራ ሁለት ሰዓት የሚሠሩ ሰዎችን ታገኛለህ። የሚያገኙት ገቢ ግን ባዶ ለማለት እስከሚያስደፍር መናኛ ነው። ከእነዚሁ ሰዎች ጥቂት ራመድ ብለህ ብትመለከት ደግሞ ለአንድ ሰዓት ብቻ እየሠሩ ሚሊዮኖችን የሚያፍሱትን ትመለከታለህ።

    አዎን ተግቶ መሥራት ወደ ብልጽግና መምራት እንደሚገባው እውነት ነው። ይሁን እንጂ በአመዛኙ ይህን ሲያስከትል አይታይም። በስዊድን አገር የሚገኝ የአውቶብስ አሽከርካሪ በጋና ያለ ተመጣጣኝ ባለሙያ የሚያገኘውን አስራ ዘጠኝ እጥፍ ያገኛል። ይህ ለምን ይሆናል? ላጠፉት አንድ ዓይነት ሰዓትና ላከናወኑት አንድ ዓይነት ሥራ ለምን እኩል አያገኙም? ለምንድን ነው አንዱ አንድ መቶ ዘርቶ አንድ መቶ ሲያገኝ ሌላኛው ደግሞ አንድ መቶ ዘርቶ ሃያ ሦስት የሚያገኘው?

    በእርግጥ የጠፉ መከሮች የቱ ጋር እንዳሉ የምታየው እዚህ ላይ ነው። የባከነ መከር ማለት አንድ ሰው ላፈሰሰው ቅሪት ተመጣጣኙን መከር ማግኘት ሳይችል ሲቀር ነው። ብዙ ሰዎች እንዲህ ዓይነቱ የቡቃያ መርገፍ ሰለባዎች ይሆናሉ።

    ብዙ ጊዜ የቡቃያ መርገፍ መንስኤዎች መከሩ ከጠፋበት ሰው ቁጥጥር ውጭ ናቸው። አንድ ሜክስካዊ ሰው ከድንበሩ አምስት ማይሎች አለፍ ብሎ ከሚኖረው አሜሪካዊ አቻው ለልፋቱ በጣም ያነሰ የሚያገኘው ለምንድን ነው? በአሜሪካ ምድር ያለ አሜሪካዊ አቻው የሜክሲካዊውን ያህል ጊዜና ጥረት አድርጎ ከሜክሲካዊው አስራ ዘጠኝ ጊዜ የበለጠ ውጤት የሚያገኘው ለምንድን ነው? ለዚህ እቆቅልሽ መንስኤዎቹም ይሁኑ መፍትሄዎቹ ግለሰቡ ለማስተካከል ከሚችለው በላይ ናቸው። ነገር ግን ሁሉን ቻይ አምላክ መከሩ ያለአግባብ ወደ መሬት እንደማይወድቅበት ለአሥራት ከፋዩ ሰው ተስፋ ገብቶለታል። ፍሬዎችህ ከመከሩ ጊዜ በፊት እንዲረግፉ አይፈቅድም። አሥራት መክፈል ለብልጽግና ዋነኛው ቁልፉ መሆኑ ታዲያ ለምን ይደንቃል? አሥራት የማይከፍሉ ከገቢያቸው አሥር ከመቶውን ለእግዚአብሔር ከመስጠት በመከልከላቸው ድሀ ሊሆኑ መቻላቸው ያስደንቅሃልን?

    ያለ እግዚአብሔር እርዳታ ምን ማድረግ ትችላለህ? እግዚአብሔር ካልረዳህ በቀር ምንስ ያህል ርቀህ መሄድ ትችላለህ? ልትጠቀምባቸው ሳትችል በመቅረትህ ፍሬዎችህ ወደ መሬት ከመርገፋቸው በፊት አሁን አሥራት መክፈል መጀመር ግድ ነው።

    ምዕራፍ 2

    አሥራት የማይከፍሉትን የሚከተሉ እርግማኖች

    አሥራቶችን አለመክፈል በርካታ የተለያዩ እርግማኖችን ይቀሰቅሳል። ብዙ ሰዎች አሥራትን አለመክፈል የሚቀሰቅሰው "የሚልክያስ

    Enjoying the preview?
    Page 1 of 1