Discover millions of ebooks, audiobooks, and so much more with a free trial

Only $11.99/month after trial. Cancel anytime.

አጋንንቶች እና እነርሱን እንዴት ማሸነፍ እንደሚቻል
አጋንንቶች እና እነርሱን እንዴት ማሸነፍ እንደሚቻል
አጋንንቶች እና እነርሱን እንዴት ማሸነፍ እንደሚቻል
Ebook150 pages2 hours

አጋንንቶች እና እነርሱን እንዴት ማሸነፍ እንደሚቻል

Rating: 5 out of 5 stars

5/5

()

Read preview

About this ebook

በዚህ ዓይነተኛ አዲስ የዳግ ሂዋርድ-ሚልስ መጽሐፍ ውስጥ የአጋንንቶች አሠራር ተጋልጧል፡፡ የጌርጌሴኖኑ በርኲስ መናፍስት ተይዞ የነበረ ሰው ምስክርነት በመጠቀም፣ በአጋንንቶች እና ርኲስ መናፍስት ላይ ድል የሚገኝበትን መንገድ ያሳያል፡፡

Languageአማርኛ
Release dateJul 28, 2016
ISBN9781613954331
አጋንንቶች እና እነርሱን እንዴት ማሸነፍ እንደሚቻል
Author

Dag Heward-Mills

Bishop Dag Heward-Mills is a medical doctor by profession and the founder of the United Denominations Originating from the Lighthouse Group of Churches (UD-OLGC). The UD-OLGC comprises over three thousand churches pastored by seasoned ministers, groomed and trained in-house. Bishop Dag Heward-Mills oversees this charismatic group of denominations, which operates in over 90 different countries in Africa, Asia, Europe, the Caribbean, Australia, and North and South America. With a ministry spanning over thirty years, Dag Heward-Mills has authored several books with bestsellers including ‘The Art of Leadership’, ‘Loyalty and Disloyalty’, and ‘The Mega Church’. He is considered to be the largest publishing author in Africa, having had his books translated into over 52 languages with more than 40 million copies in print.

Related to አጋንንቶች እና እነርሱን እንዴት ማሸነፍ እንደሚቻል

Related ebooks

Reviews for አጋንንቶች እና እነርሱን እንዴት ማሸነፍ እንደሚቻል

Rating: 5 out of 5 stars
5/5

5 ratings0 reviews

What did you think?

Tap to rate

Review must be at least 10 words

    Book preview

    አጋንንቶች እና እነርሱን እንዴት ማሸነፍ እንደሚቻል - Dag Heward-Mills

    አጋንንቶች እና እነርሱን እንዴት ማሸነፍ እንደሚቻል

    ዳግ ሂዋርድ ሚልስ

    ካልተገለፀ በቀር፣ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ያሉ ጥቅሶች ሁሉ የተወሰዱት በ1954 ዓ.ም. ከታተመው የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡

    ትርጉም፡- መስፍን ተስፋዬ

    አርታኢ፡- ሬቨረንድ አማኑኤል ቶማስ

    DEMONS AND HOW TO DEAL WITH THEM

    ስለ ዳግ ሂዋርድ ሚልስ የበለጠ መረጃ ከፈለጉ

    በዚህ ኢሜይል ይጻፉ፡- evangelist@daghewardmills.org

    ዌብሳይታቸውን ይጎብኙ፣ www.daghewardmills.org.

    በፌስቡክ፣ Facebook: Dag Heward-Mills

    በትዊተር፣ Twitter: @EvangelistDag

    ISBN: 978-1-61395-433-1

    ላይትሃውስ ቻፕል ኢንተርናሽናል

    መ.ሳ ቁጥር 15134

    አዲስ አበባ

    ኢትዮጵያ

    ይህንን መጽሐፍ በሙሉም ሆነ በከፊል ያለ አሳታሚው ፈቃድ ማባዛት የተከለከለ ነው፡፡

    ማውጫ

    1. የአጋንንትን ሥራ ጉልህ ማሳያ

    2. ጨለማ፣ የአጋንንቶች መኖሪያ

    3. የክርስቶስ ኃይል ዛሬም የአጋንንትን ሥራ ይፋለማል

    4. የተለመደው የአጋንንት ሥራ ምልክት

    5. አጋንንት ሰዎች እንግዳ ነገር እንዲያደርጉ ያደርጋሉ

    6. እብደት

    7. ሰይጣን ሊገድልህ እየሞከረ ነው

    8. ሰይጣን ከሌሎች ሊለይህ ምኞቱ ነው

    9. አጋንንት ሰዎች ራሳቸውን እንዲጎዱ ያደርጋሉ፤

    10. የአጋንንት ሥራ ከቁጥጥር በላይ የሚሆኑ ሰዎች እንዲነሱ ያደርጋል

    11. ድብርትና ሀዘንተኝነት የአጋንንት ሥራ ውጤቶች ናቸው

    12. አጋንንት ሊያዋርዱህ ይተጋሉ!

    13. አጋንንት የሚሠሩት በቡድንና በአንድነት ነው

    14. አጋንንት በግዛት የተከፋፈሉ ናቸው

    15. የአጋንንት እንቅስቃሴ ጌታን ከሚያመልኩ ክርስቲያኖች ጋር ጎን ለጎን ይገኛል

    16. አጋንንት የሚሠሩት ከሚታይ ርቀት ሳይሆን ከመንፈሳዊ ርቀት ነው

    17. አጋንንት በአሳብ፣ በምናባዊ አመለካከት እና በክፉ ምክር

    18. አጋንንት በሰዎች ላይ አካላዊ ለውጥን ያስከትላሉ

    19. እግዚአብሔር በሚገኝበት አጋንንት ይናወጣሉ

    20. አጋንንትን ለይተህ እወቅ

    21. ከአጋንንት ጋር አለመስማማትህ ሥፍራቸውን እንዲለቁ ያደርጋል

    22. አጋንንት ችኮዎች ናቸው

    23. እባቦችና የቤተ ክርስቲያን መጋቢዎች

    24. አጋንንት እና ቤተክርስቲያን

    25. ነፃ መውጣት ተግባራዊ እርምጃን ይጠይቃል

    26. በጌታ የበረታህ ሁን

    27. የእግዚአብሔርን የጦር ዕቃ ሁሉ ልበስ

    28. ነፃነት በክርስቶስ

    ምዕራፍ 1

    የአጋንንትን ሥራ ጉልህ ማሳያ

    ወደ ባሕር ማዶም ወደ ጌርጌሴኖን አገር መጡ፡፡ ከታንኳይቱም በወጣ ጊዜ፣ ርኩስ መንፈስ የያዘው ሰው ከመቃብር ወጥቶ ወዲያው ተገናኘው እርሱም በመቃብር ይኖር ነበር፣ በሰንሰለትም ስንኳ ማንም ሊያስረው በዚያን ጊዜ አይችልም ነበር፣ ብዙ ጊዜ በእግር ብረትና በሰንሰለት ይታሰር ነበርና ዳሩ ግን ሰንሰለቱን ይበጣጥስ እግር ብረቱንም ይሰባብር ነበር፣ ሊያሸንፈውም የሚችል አልነበረም፤ ሁልጊዜም ለሌትና ቀን በመቃብርና በተራራ ሆኖ ይጮህ ነበር ሰውነቱንም በድንጋይ ይቧጭር ነበር፡፡ ኢየሱስንም ከሩቅ ባየ ጊዜ ሮጦ ሰገደለት በታላቅ ድምጽም እየጮኸ ፡- የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ሆይ፣ ከአንተ ጋር ምን አለኝ? እንዳትሣቅየኝ በእግዚአብሔር አምልሃለሁ አለ፤ አንተ ርኩስ መንፈስ ከዚህ ሰው ውጣ ብሎት ነበርና፡፡ ስምህ ማን ነው? ብሎ ጠየቀው፡፡ ብዙዎች ነንና ስሜ ሌጌዎን ነው አለው፣ ከአገርም ውጭ እንዳይሰዳቸው እጠብቆ ለመነው፡፡ በዚያም በተራራ ጥግ ብዙ የእሪያ መንጋ ይሰማራ ነበርና ፡- ወደ እሪያዎቹ እንድንገባ ስደደን ብለው ለመኑት፡፡ ኢየሱስም ፈቀደላቸው፡፡ ርኩሳን መናፍስቱም ወጥተው ወደ እሪያዎቹ ገቡ፣ ሁለት ሺህም የሚያህል መንጋ ከአፋፍ ወደ ባሕር ተጣድፎ በባሕር ሰጠሙ፡፡

    እረኞቹም ሸሽተው በከተማውና በአገሩ አወሩ፤ ነገሩም ምን እንደ ሆነ ለማየት መጡ፡፡ ወደ ኢየሱስም መጡ፣ አጋንንትም ያደሩበትን ሌጌዎንም የነበረበትን ሰው ተቀምጦ ለብሶም ልቡም ተመልሶ አዩና ፈሩ፡፡ ያዩት ሰዎችም አጋንንት ላደሩበት ሰው የሆነውንና ስለ እርያዎቹ ተረኩላቸው። ከአገራቸውም እንዲሄድላቸው ይለምኑት ጀመር፡፡ ወደ ታንኳይቱም በገባ ጊዜ አጋንንት አድረውበት የነበረው ሰው ከእርሱ ጋር እንዲኖር ለመነው ፡፡ ኢየሱስም አልፈቀደለትም፣ ነገር ግን ፡-ወደ ቤትህ በቤተ ሰዎችህ ዘንድ ሄደህ ጌታ እንዴት ያለ ታላቅ ነገር እንዳደረገልህ እንዴትስ እንደማረህ አውራላቸው አለው፡፡ ሄዶም ኢየሱስ እንዴት ያለ ታላቅ ነገር እንዳደረገለት አሥር ከተማ በሚባል አገር ይሰብክ ጀመር፣ ሁሉም ተደነቁ፡፡

    ማርቆስ 5፡1-20

    የጌርጌሴኖኑን እብድ ሰው ሁኔታ ማጥናት በአጋንንት እንቅስቃሴ ላይ የሚካሄድ የሬሳ ምርመራ ሳይንስ (ፓቶሎጂ) ነው፡፡ ይህን ታሪክ በማጥናት ብቻ ስለ ሰይጣንና ስለ አጋንንት በርካታ ነገሮችን ትማራለህ፡፡ ብዙ ሰዎች የሬሳ ምርመራ ሳይንስ ምንድነው ብለው ይገረማሉ፡፡ አንድ ሰው ለምን የሞተ ሰው ሬሳ በማጥናት ጊዜ ያጠፋል ብለን ብዙ ጊዜ እንገረማለን፡፡ እንደ ሕክምና ተማሪ አንድ ሐኪም ሬሳ በመቆራረጥ ጊዜ ማጥፋቱ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ አልተረዳሁትም ነበር፡፡ አንድ ጊዜ ከሞቱ በኋላ በቃ ሞተዋል፣ለምን አይተዋቸውም! በማለት አስብ ነበር፡፡

    ነገር ግን የሬሳ ምርመራ ሳይንስ የተለያዩ በሽታዎች በሰው አካል ላይ የሚያስከትሉትን ጉዳት የሚያጠና መሆኑን ለመረዳት ቻልሁ፡፡ የሬሳ ምርመራ ሳይንስ አንድ በሽታ ሊያስከትል የሚችለው ከፍተኛው ጉዳት ለማወቅ የሚደረግ ጥናት ነው፡፡ በሌላ አነጋገር አንድ በሽታ አስከመጨረሻ በሰው አካል ውስጥ እንዲቆይ ቢተው ምን ሊያስከትል እንደሚችል ለመረዳት የበሽታ ጥናት ሳይንስ ማካሄድ ይኖርብሃል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ በሽታዎች የሚያስከትሉትን ከፍተኛውን ጉዳት መረዳት የሚቻለው በሞተ ሰው አካል ላይ ጥናት በማድረግ ብቻ ነው፡፡

    ለምሳሌ ለረጅም ጊዜ በደም ብዛት ተሰቃይቶ የሞተ ሰውን ሬሳ በምትከፍትበት ጊዜ በልቡ፣ በደም ስሮቹና በኩላሊቶቹ ላይ ለውጥ ታስተውላለህ፡፡ እነኚህ ለውጦች የደም ብዛት በሽታ በሕይወት ባሉና በበሸታው በተያዙ ሰዎች ላይ ምን እያደረገ እንዳለ ለመረዳት ይረዳሀል፡፡ ሐኪሞች በአንድ የተወሰነ በሽታ ሙሉ በሙሉ ተጠቅቶ የሞተ ሰው አካልን በማጥናት ስለ በሽታው ከፊት ይልቅ የበለጠ ይረዳሉ፡፡ በተመሳሳይ ስለ ጌርጌሴኑ እብድ ሰው ሁኔታ በማጥናት የአጋንንት እንቅስቃሴ በሰው ልጅ ላይ የሚያስከትለውን ከፍተኛውን ጉዳት ትገነዘባለህ፡፡

    የጌርጌሴኑ እብድ ሰው ታሪክ ከፍተኛውን ዓይነት የአጋንንት ሰርጎ አገባብ ለማጥናት የሚረዳ ነው፡፡ ሰይጣን እድል ቢያገኝ በአንተ ላይ ሊያደርግ የሚፈልገው ነገር የሚያስረዳ መገለጥ ነው። እያንዳንዱ የእብዱ ሰው የአኗኗር ገጽታ አጋንንታዊ ባህሪን ይገልጣል፡፡ ሰይጣን መንገድ ቢያገኝ ኖሮ የእኔና የአንተ መጨረሻ (ከእብዱ ሰውጋር) ተመሳሳይ ይሆን ነበር፡፡ ምንም እንኳ አብዛኛዎቹ ሰዎች ሙሉ በሙሉ የጌርጌሴን እብዶች ባይሆኑም አብዛኛዎቻችን ከሞላ ጎደል በዚህ እብድ ሰው የተገለጠውን ዓይነት ተመሳሳይ አጋንንታዊ ልምምዶች ውስጥ እናልፋለን፡፡

    የጌርጌሴኖኑ እብድ ሰው ምስክርነት ሦስት ነገሮችን ያሳየናል፡-

    እድልቢያገኙአጋንንትበአንተላይሊያደርጉየሚፈልጉትንነገር

    ምንምእንኳቀስበቀስቢሆንምአጋንንቶችበሰዎችላይእያደረጉያለውንነገር

    አጋንንቶችሙሉበሙሉየሚገለጡበትሰውየመጨረሻሁኔታ

    ይህን መጽሐፍ እያነበብክ ሳለ እግዚአብሔር ስለ አጋንንቶች ተግባርና እንዴት በአንተ ላይ ተጽዕኖ ሊያደርጉ እንደሚችሉ ይገልጥልሃል፡፡ መጽሐፉን አንብበህ በምትጨርስበት ጊዜ ከአጋንንት ተጽዕኖ ነጻ ትወጣለህ፡፡

    ብዙዎች የጌርጌሴኖኑ እብድ ሰው ታሪክ ወደ የአእምሮ ሕመምተኞች ሕክምና ተቋም መግባት ያለበት የአእምሮ በሽተኛ ታሪክ ነው ብለው ያስባሉ፡፡ ለራሳቸው እኔ እብድ ስላይደለሁ፣ ይህ ታሪክ እኔን አይመለከተኝም ብለው ያስባሉ፡፡ ሆኖም ግን ይህ ምስክርነት ሁላችንንም ይመለከተናል፡፡

    የጠላትህን እንቅስቃሴና እቅድ ማወቅ የትኛውንም ጦርነት ለማሸነፍ ወሳኝ ነው፡፡ ከክፉ ርኩሳን መናፍስት ጋር ያለውን ጦርነት ለማሸነፍ ከፈለግህ ጠላትህ የትና እንዴት እንሚሠራ ማወቅ አለብህ፡፡ ጠላት አንተን ለማጥቃት ምን እንዳቀደ ማወቅ ይገባሃል፡፡

    በሰይጣን እንዳንታለል፣ የእርሱን አሳብ አንስተውምና፡፡

    2ኛ ቆሮንቶስ 2፡11

    ምዕራፍ 2

    ጨለማ፣ የአጋንንቶች መኖሪያ

    መጋደላችን . . . ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር . . .ነው፡፡

    ኤፌሶን 6፡12

    የዚህ ዓለም ጨለማ የርኩሳን መናፍስት መኖሪያ ነው፡፡ ጨለማ ስንል ክፉ የተንሰራፋበትን ሁኔታ ለማለት ነው። ሰይጣን በዚህ ዓለም ጨለማ ይገዛል፡፡ ሽንገላ የመንፈሳዊ ጨለማ ምሳሌ ነው፡፡ ለዚህም ምክንያቱ ሽንገላ ያለበት

    Enjoying the preview?
    Page 1 of 1