Discover millions of ebooks, audiobooks, and so much more with a free trial

Only $11.99/month after trial. Cancel anytime.

ከእናንተም አንዱ ዲያብሎስ ነው
ከእናንተም አንዱ ዲያብሎስ ነው
ከእናንተም አንዱ ዲያብሎስ ነው
Ebook177 pages1 hour

ከእናንተም አንዱ ዲያብሎስ ነው

Rating: 0 out of 5 stars

()

Read preview

About this ebook

ከእናንተም አንዱ ዲያብሎስ ነው የሚለው ጥልቅ አባባል ኢየሱስ ለአስራ ሁለቱ ደቀመዛሙርቶች የተናገረው ነው። ብዙዎቻችን በዲያብሎስ ተጠቅተናል፤ ምክንያቱም ሽፍንፍኑን መግለጽ እና የእጆቹን ሰራ ማጋልጠ ስለማንችል ነው። በዚህ የተባረከ መጽሐፍ ውስጥ፤ የዲያብሎስ ሓጢአቱን ይገልጥልህና ፈጽሞ በዚያ መንገድ የማትሄድ ትሆናለህ። ከእናንተም አንዱ ዲያብሎስ ነው የሚለው አባባል ባንተ ላይ አይሁንብህ!

Languageአማርኛ
Release dateNov 8, 2018
ISBN9781641357555
ከእናንተም አንዱ ዲያብሎስ ነው
Author

Dag Heward-Mills

Bishop Dag Heward-Mills is a medical doctor by profession and the founder of the United Denominations Originating from the Lighthouse Group of Churches (UD-OLGC). The UD-OLGC comprises over three thousand churches pastored by seasoned ministers, groomed and trained in-house. Bishop Dag Heward-Mills oversees this charismatic group of denominations, which operates in over 90 different countries in Africa, Asia, Europe, the Caribbean, Australia, and North and South America. With a ministry spanning over thirty years, Dag Heward-Mills has authored several books with bestsellers including ‘The Art of Leadership’, ‘Loyalty and Disloyalty’, and ‘The Mega Church’. He is considered to be the largest publishing author in Africa, having had his books translated into over 52 languages with more than 40 million copies in print.

Related to ከእናንተም አንዱ ዲያብሎስ ነው

Related ebooks

Reviews for ከእናንተም አንዱ ዲያብሎስ ነው

Rating: 0 out of 5 stars
0 ratings

0 ratings0 reviews

What did you think?

Tap to rate

Review must be at least 10 words

    Book preview

    ከእናንተም አንዱ ዲያብሎስ ነው - Dag Heward-Mills

    ምዕራፍ 1 (Chapter 1)

    የዲያብሎስ ኃጢአቶች እንዴት የሰዎች ኃጢአቶች ሊሆኑ ይችላሉ

    ኢየሱስም፦ እኔ እናንተን አሥራ ሁለታችሁን የመረጥኋችሁ አይደለምን? ከእናንተም አንዱ ዲያብሎስ ነው ብሎ መለሰላቸው።

    ዮሐንስ 670

    ኢየሱስ ለራሱ ደቀመዝሙሮች ከእናንተ አንዱ ዲያብሎስ ነው አለቸው። ኢየሱስ ዲያብሎስን ከውድቀቱ ጊዜ ጀምሮ ያውቀዋል። ህገወጥነቱን፣ ክፋቱን፣ ፍጥረቱን፣ ኃጢአቱን እና ውድቀቱን ያውቀዋል። ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱን ከእናንተ አንዱ ዲያብሎስ ነው ብሎ መናገር፣ በእግጥም ትልቅ አባባል ነው።

    ያ ማለት ከደቀመዛሙርቱ አንዱ በኃጢአት እና በዲያብሎስ ኮቴ እየተመላለሰ ነበር ማለት ነው። ከደቀመዛሙርቱ አንዱ ጸባዩ (ድርጊቱ) ልክ እንደ ዲያብሎስ ነበር። ዲያብሎስን ለመለየት ለኢየሱስ ቀላል ነበር ምክንያቱም የሊሲፈርን የቀድሞውን ክብር፣ ኃጢአቱን እና ውድቀቱን ሁሉ ያውቀው ነበር! 

    ዛሬ ብዙ ክርስቲያኖች በኃጢአት እና በሉሲፈር ኮቴ እየተመላለሱ ነው። ሰይጣን የፈጸመውን እያንዳንዱን ኃጢአት እያደረጉ ነው። ብዙ መጋቢዎች ሉሲፈር በሄደባቸው በእነዚያው መንገዶች እየሄዱ ነው መጨራሻቸውም ዛሬ ሰይጣን ባለበት የጭለማ ትርምስምስ ውስጥ ነው። ጸባይህ (ድርጊትህ) እንደ ዲያብሎስ ነውን? ዲያብሎስ ነህን? ጸባዩ (ድርጊቱ) ልክ እንደ ዲያብሎስ የሆነ እና ሉሲፈር ያደረጋቸውን ኃጢአቶች እያደረገ ያለ አንድን ሰው ታውቃለህን?  

    ሰይጣን በብርሃን እና በዘላለማዊነት ግዛት ውስጥ ነፃ እና ደስተኛ መሆን ሲገባው ዛሬ ያለው በጭለማ ሰንሰለት ውስጥ ተገድቦ እና ታስሮ ነው። በመንግስተ ሰማይ መልአክ ሆኖ ሳለ ከሰራው ስህተት እና ኃጢአት የተነሳ ህይወቱ፣ አገልግሎቱ እና ተስፋው ተበላሽቶበታል። በሺህ የሚቆጠሩ መልአክቶችን አሳተ እንዲሁም ዛሬ በዓለማችን ያለውን ግራ መጋባት፣ ሽብር እና ክፋት ሁሉ እንዲሆኑ አደረገ።

    ብዙ አገልጋዮች ግራመጋባት ውስጥ ይኖራሉ እንዲሁም በውድቀት፣ በድህነት እና በጥልቅ ጨለማ ውስጥ ተወስነዋል። እየሆነባቸው ያለው እንኳን ምን እንደሆነ አያውቁትም። አገልግሎታቸው ለምን ውስን፣ የተገደበ እና ዝቅተኛ እንደሆነ አይገባቸውም።

    እያንዳንዱን የሰይጣንን ኃጢአቶች ልትደርስባቸው ነው፣ እንዲሁም ይህን መጽሐፍ ካነበብክ በሃላ በእነዚያ መንገዶች አትሄድም!

    የሰይጣንን የኃጢአት ህገ ወጥ መንገድ እንዴት ማስወገድ እንደምትችል እና ዲያብሎስን እንዳትሆን በዚህ መጽሐፍ ውስጥ አካፍልሃለሁ። እያንዳንዱ የወንጌል አገልጋይ አንድ ጊዜ የእግዚአብሔር ከፍተኛው አገልጋይ የነበረውን የሉሲፈርን ኮቴ ላለመከተል ከልቡ መጣር አለበት። ሉሲፈር በብርሃን ውስጥ ኖሮ ከነበረ፣ ከወደቀ እና ብዙ ግራ ማጋባትን መፍጠር ከቻለ፤ በዚህ ጨለማ እና እውር ዓለም ውስጥ የምንኖረው እኛማ ምን ያህል!  

    ምዕራፍ 2 (Chapter 2)

    የሰው ዲያቢሎስ አለን?

    ኢየሱስም፦ እኔ እናንተን አሥራ ሁለታችሁን የመረጥኋችሁ አይደለምን? ከእናንተም አንዱ ዲያብሎስ ነው ብሎ መለሰላቸው።

    ዮሐንስ 670

    አንድ ሰው በስራ ላይ ያለ እና ህያው የሚዳሰስ ዲያብሎስ ሆኖ ለተወሰነ ጊዜ በህይወትህ ውስጥ ሊኖር እንደሚችል አምነህ መቀበል መቻል አለብህ። ለእንደዚ ዓይነቱ ሰው መታዘዝ አያስፈልግም፣ መገዛት አያስፈልግም እንዲሁም ማዳመጥም አያስፈልግም።

    በምታየው መስራት የለብህም። አብሮህ ካለው ሰው ጋር መስራት ያለብህ በመለኮታዊ መገለጥ መሆን አለበት።

    የሆኑ ሰዎችን ልክ እንደ ዲያብሎስ ማስተናገድ አለብን ምክንያቱም በግላጭ ዲያቢሎሶች ናቸውና (ተለወሰነ ጊዜም ቢሆን)። አንዳንድ ሰዎች ሙሉ በሙሉ በዲያብሎስ የተያዙ እና የተወረሱ ናቸው። እነዚህን ሰዎች እንደ ዲያብሎስ ካላስተናገድን ከባድ ችግር ያስከትላል። እንደዚህ ያለ ነገር የምናገረው ለምንድ ነው? መጽሐፍ ቅዱስ የምንዋጋው ከስጋና ከደም ጋር አይደለም ይላል ነገር ግን ከአለቆች እና ከስልጣናት ጋር ነው። ከመጽሐፉ ቃል ጠላታችን ስጋና ደም እንዳልሆነ ግልጽ ነው ነገር ግን መንፈስ ነው! በእርግጥም መጋደላችን፣ ትግላችን እና ውጊያችን ከስጋና ከደም ጋር አይደለም። ከክፋት መናፍስቶች ጋር ነው።

    ያምሆኖ ግን እነዚህ ክፉ መናፍስት የሰው ዘር የሆነውን እና ዲያብሎስን መለየት በጣም አስቸጋሪ እስከሚሆን ድረስ አንዳንድ ሰዎችን አስጨንቀው እና ወርሰዋቸው ይኖሩባቸዋል። ይህ እንደዚህ ሲሆን ሰዎች በደንብ ዲያቢሎሶች ይሆናሉ ስለዚህም መስተናገድ ያለባቸው እንደ ዲያቢሎሶች መሆን አለበት።

    አንድ ሰው ሙሉ በሙሉ በዲያብሎስ ከተያዘ፣ ተጽኖ ውስጥ ካለ እና መጠቀሚያ ከሆነ፤ ይህን ሰው በዙሪያህ እንዳይሰራ ማድረግ እንዳለብህ አጽንቼ ማሳወቅ እፈልጋለሁ። መጋቢዎች ከሚገባው በላይ ትሁቶች ከመሆናቸው የተነሳ ፣ ከሚገባው በላይ ጥሩዎች ከመሆናቸው የተነሳ እና ዲያብሎስን ለመጋፈጥ ከሚገባው በላይ ከመቆጠባቸው የተነሳ አገልግሎቶች ሲፈራርሱ አይቼአለሁ። እንደዚሁም መጋቢዎች ከሚገባው በላይ ትሁቶች ከመሆናቸው የተነሳ ፣ ከሚገባው በላይ ጥሩዎች ከመሆናቸው የተነሳ እና እንደ እራሱ እንደ ዲያብሎስ ሲሰሩ የነበሩ ሰዎችን ለመጋፈጥ ከሚገባው በላይ ከመቆጠባቸው የተነሳ አገልግሎቶች ሲፈራርሱ አይቼአለሁ!   

    እንደ ዲያብሎስ ልታያቸው የሚገባህ አንዳንድ ሰዎች አሉ። እንደዚህ ዓይነቶቹን ሰዎች መናገር ያለብህ ልክ ዲያብሎስ እራሱን እንደምትናገረው መሆን አለበት! ይህንን አለማድረግ ማለት ዲያብሎስን በዙሪያህ በነፃነት እንዲኖር እና አንተን እየተቃወመ እንዲቀሳቀስ መፍቀድ ማለት ነው።

    ዲያቦሎስ

    ዲያቦሎስ የሚለው የግሪክ ቃል በአብዛኛው የተተረጎመው ዲያብሎስ ተብሎ ነው እንዲሁም ዲያብሎስን በደንብ ለመግለጽ ነው። ዲያቦሎስ የሚለው ቃል አዲስ ኪዳን ውስጥ ሰላሳ ስምንት ጊዜ ተጠቅሞበታል። ዲያቦለስ ሰላሳ አምስት ጊዜውን የተተረጎመው ዲያብሎስ ተብሎ ነው። ለምሳሌ ኢየሱስ ከዲያብሎስ ይፈተን ዘንድ መንፈስ ወደ ምድረ በዳ ወሰደው

    ያምሆኖ ግን፣ ሌሎቹ ሶስቱ ዲያቦሎስ በጣም ዋና ዋና ቦታ ላይ የተጠቀሱት ሰውን ለመግለጽ ነው። የሚያስገርም አይደል?  ዲያቦሎስ የሚለው ቃል የተጠቀመው የአስቆርቱን ይሁዳ፣ አንዳንድ የመጋቢዎችን ሚስቶችን እና አሮጊት ሴቶችን በመጠቆም ነው። (እባክህ ይህንን ራስህ አጣራው) የምናገረው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ካለ ማመን አለብህ።

    የኢየሱስን ምሳሌ ተከተል እና አንዳንድ ሰዎችን እንደ ዲያብሎስ አስተናግዳቸው

    1. ኢየሱስ ጴጥሮስን ያስተናገደው እርሱ ልክ ዲያብሎስ እንደነበር አድርጎ ነው።

    ጴጥሮስም ወደ እርሱ ወስዶ፦ አይሁንብህ ጌታ ሆይ፤ ይህ ከቶ አይደርስብህም ብሎ ሊገሥጸው ጀመረ።

    እርሱ ግን ዘወር ብሎ ጴጥሮስን፦ ወደ ኋላዬ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን፤ የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን አታስብምና ዕንቅፋት ሆነህብኛል አለው።

    ማቴዎስ 1622-23

    ልክ እንደ ኢየሱስ አንዳንድ ሰዎች በህይወትህ ውስጥ እንዳለ በግላጭ የሚዳሰስ ዲያብሎስ ሆነው ለተወሰነ ጊዜ በዲያብሎስ ተይዘው ዲያብሎስም ሊጠቀምባቸው እንደሚችል መቀበል አለብህ። ለጊዜው እንደ ዲያብሎስ ሲሰራ የነበረው፣ ኢየሱስ እንደ ቤተክርስቲያን መሪ አድርጎ የሾመውን ጴጥሮስን ኢየሱስ ያስተናገደው ጠንካራ እና ወሳኝ ሆኖ ነው። ኢየሱስ በእርሱ ዙሪያ መልሶ እንዲናገር አልፈቀደለትም። ኢየሱስ በህይወቱ ውስጥ እንዲሰራ አልፈቀደለትም።

    ኢየሱስ ክርስቶስ ጴጥሮስ በሰይጣን ተጽንዖ ውስጥ ነው አላለም!

    ጴጥሮስ ኢየሱስን ተላምዶተ ነበር። ምናልባትም የቤተክርስቲያን መሪ ሆኖ መሾሙ እራሱ ላይ ወጥቶበት ከነበረው ቦታው አነቃንቆት ሊሆን ይችላል። ኢየሱስን በአገልግሎቱ ውስጥ አቅጣጫ ሊያሳየው ሞከረ። የእግዚአብሔርን ልጅ መገሰጽ ጀምሮ ነበር። ስለ መስቀሉ ሞኝነት ለኢየሱስ እየነገረው ነበር! የመስቀሉ ስብከት ለብዙዎች ሞኝነት እንደሆነ አስታውስ! በእርግጥም በዚያን ቀን ለጴጥሮስ ሞኝነት ነበር። መቀጠል እና መስቀል ተሸክሞ መሄድ የሚያስፈልግ እንደሆነ ለኢየሱስ እየነገረው ነበር። ኢየሱስ ከጴጥሮስ መላመድ እና አለመብሰል ባሻገር አልፎ አየ። ነገር ግን ከጴጥሮስ ተላምዶ ወይም ከአለመብሰል ነው አላለም። ሰይጣን የጴጥሮስን ድምጽ እየተጠቀመ እንደነበር ለይቶት ነበር። በቅጽበት ጴጥሮስን ገሰጸው እና ሰይጣንን በቀጥታ አስቆመው።

    በ1993ዓ.ም. አዶልፍ ሂትለር ሲናገር ሰዎች የሰይጣንን ድምጽ ለይተውት ቢሆን ኖሮ ከጅማሬው ባስቆሙት ነበር። ነገር ግን መጋቢዎች ሳይቀር ይህንን የጅምላ ነፍሰ ገዳይ እንደ ጀግና አወድሰውት ነበር። አዶልፍ ሂትለር ለሃምሳ ሚሊዮን ሰዎች ሞት ምክንያት ነበር። ብዙ ሰዎችን እያወቀ ወደሞት መርቷል። የመጨረሻው ትዕዛዙ የራሱን ወገኖች ጀርመኖችን እንዲያጠፉአቸው ነበር። በጦርነቱ ተሸንፈዋልና በህይወት መኖር አይገባቸውም ብሏል። ጀርመናውያኖች ከሰሯቸው ትልቁ ስህተት ይህንን ሰው እንዲናገር፣ እንዲሰራ፣ እንዲያብብ እና መሪ እንዲሆን መፍቀድ ነበር። ሰይጣንን ከጅማሬው መለየት እና ማስቆም ያስፈልጋል!

    ዲያብሎስን በህይወትህ ውስጥ ለአንድ ደቂቃ እንኳን አትፍቀድለት። እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ብልህ እና ፈጣን ሁን። በመኖሪያህ ክፍል ውስጥ ኃይለኛ ተናዳፊ ገዳይ እባብን ብታገኝ ለጥቂት ሳምንታት እንዲቀመጥ ትፈቅድለታለህን?  

    ኃይለኛ ተናዳፊ ገዳይ እባብን በመኖሪያ ክፍላቸው ውስጥ እንዲኖር የሚፈቅዱን ሰዎች ልብ በላቸው! በጣም አስፈሪ ስህተቶችን እየሰሩ ነው! 

    ካንተ ጋር የሚላመዱ ሰዎችን ልብ በል! 

    ከቦታቸው የሚወጡን ሰዎች ልብ በል! እንደዚህ ያሉ ሰዎችን ለመምራት፣ ለመቆጣጠር ወይም የእግዚአብሔርን ሰው ለማረም ቦታቸው እንዳልሆነ እውነታውን ቶሎ ይረሳሉ።

    የእግዚአብሔርን ሰዎች ሰብአዊነት ስናይ ሊያደናግረን እና ከስርዓት እንድንወጣ ሊፈትነን ይችላል።

    2. ኢየሱስ ይሁዳን ያስተናገደው እርሱ ልክ ዲያብሎስ እንደነበር አድርጎ ነው።

    ኢየሱስም፦ እኔ እናንተን አሥራ ሁለታችሁን የመረጥኋችሁ አይደለምን? ከእናንተም አንዱ ዲያብሎስ ነው ብሎ መለሰላቸው።

    ዮሐንስ 670

    ደቀመዛሙርቱና ረዳቶቹ ወደ "ዲያቦሎስ" (ዲያብሎስ) ሊለወጡ እና ልክ እንደ ዲያብሎስ ሊሆኑ ይችላሉ።

    ኢየሱስ የራሱን የታመነ ገንዘብ ያዥ ዲያብሎስ ብሎታል። አስቆርቱ  ይሁዳ ዲያብሎስ ተባለ። እምነት ያጎደለን ከሃዲ በአካባቢህ እንዲሰራ መፍቀድ መርዛማ እባብ በቤትህ እንዲኖርና በነፃነት እንዲንቀሳቀስ መፍቀድ ነው።

    ታማኝ ያልሆነ ሰውን ወደ አንተ እንዲቀርብ አትፈቀድላት።  ከመጋቢዎች ጉባኤ መካከል ኮብራ እባብ እንዲቀመጥ አትፍቅድ። ለይተህ አውጣቸውና ፈጣን እርምጃ ውሰድባቸው።

    ኢየሱስ ይሁዳን እንደ ዲያብሎስ ጠቀሰው። ኢየሱስ ይሁዳ በሰይጣን ተፅእኖ ስር ወድቋል አላለም። ኢየሱስ ያለው ይሁዳ ዲያብሎስ ነው። እኔ እናንተን አስራሁለታችሁን የመገረጥኋችሁ አይደለምን ከእናንተም አንዱ ዲያብሎስ ነው። አለ። በሕይወታችሁ እና በአገልግሎታችሁ ዲያብሎስ በነፃነት እንዲንቀሳቀስ ከፈቀዳችሁ ያለጥርጥር ችግር ይገጥማችኋል። ታማኝ ያልሆነን ረዳት በነፃነት በቤተክርስቲያን እንዲንቀሳቀስ መፍቀድ ማለት ዲያብሎስ በቤተክርስቲያን ያሻውን እንዲያደርግ መፍቀድ ነው።

    በመኖሪያ ቤትህ ውስጥ መርዛማ እባብ ቢኖር ሊሆን የሚችለውን አስበህው ታውቃለህን? እዚያ እንዲኖርስ ትፈቅድለታለህን? እንደ

    Enjoying the preview?
    Page 1 of 1