Discover millions of ebooks, audiobooks, and so much more with a free trial

Only $11.99/month after trial. Cancel anytime.

እግዚአብሔርን ማገልገል ትልቅ ነገር ነው
እግዚአብሔርን ማገልገል ትልቅ ነገር ነው
እግዚአብሔርን ማገልገል ትልቅ ነገር ነው
Ebook82 pages1 hour

እግዚአብሔርን ማገልገል ትልቅ ነገር ነው

Rating: 3.5 out of 5 stars

3.5/5

()

Read preview

About this ebook

እግዚአብሔርን ማገልገል ትልቅ ነገር እንደሆን ሰምተህ ልታውቅ ትችላለህ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ማገልገል እንዴት ትልቅ ነገር እንደሆነ ጠለቅ ብልህ አስበህ ላታውቅ ትችላለህ። በዚህ ለየት ባልው የዳግ ሂዋርድ ሚልስ መጽሕፍ ውስጥ ማን የእግዚአብሔር አግልጋይ እንደሆነ እና እንዴት እግዚአብሔርን ማገልገል እንዳለብህ ትረዳለህ። እግዚአብሔርን ብሚያገለግሉት እና እግዚአብሔርን በማያገልግሉት መካክል ያልው ልዩነት ግልጽ ባለው መንገድ ይብራልህ!
እግዚአብሔርን ክሚያገለግሉት ውስጥ የምትቆጠር ሁን!

Languageአማርኛ
Release dateNov 8, 2018
ISBN9781641357562
እግዚአብሔርን ማገልገል ትልቅ ነገር ነው
Author

Dag Heward-Mills

Bishop Dag Heward-Mills is a medical doctor by profession and the founder of the United Denominations Originating from the Lighthouse Group of Churches (UD-OLGC). The UD-OLGC comprises over three thousand churches pastored by seasoned ministers, groomed and trained in-house. Bishop Dag Heward-Mills oversees this charismatic group of denominations, which operates in over 90 different countries in Africa, Asia, Europe, the Caribbean, Australia, and North and South America. With a ministry spanning over thirty years, Dag Heward-Mills has authored several books with bestsellers including ‘The Art of Leadership’, ‘Loyalty and Disloyalty’, and ‘The Mega Church’. He is considered to be the largest publishing author in Africa, having had his books translated into over 52 languages with more than 40 million copies in print.

Related to እግዚአብሔርን ማገልገል ትልቅ ነገር ነው

Related ebooks

Reviews for እግዚአብሔርን ማገልገል ትልቅ ነገር ነው

Rating: 3.6666666666666665 out of 5 stars
3.5/5

3 ratings0 reviews

What did you think?

Tap to rate

Review must be at least 10 words

    Book preview

    እግዚአብሔርን ማገልገል ትልቅ ነገር ነው - Dag Heward-Mills

     ምዕራፍ 1

    የእግዚአብሔር አገልጋይ ማነው?

    የእግዚአብሔር አገልጋይ ለመሆን መጋቢ ወይም ሚሲዮናዊ መሆን አያስፈልግህም፡፡ ሁላችን ካህናት፣ ነቢያት፣ ወንጌላዊያን እና መጋቢዎች የጌታ አገልጋይ እንደሆኑ እናውቃለን፡፡ እንደነዚህ አይነት ሰዎች ታዲያ የልዑል አምላክ ባሪያዎች ተብለው በመጠራታቸው የታደሉ ናቸው፡፡ ፈጣሪያቸውን ለማገልገል በመቻላቸው ምንኛ ተባርከዋል! መልካሙ ዜና ግን የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል የሚያገለግሉ ሌሎች ሰዎች ሁሉ የእግዚአብሔር አገልጋይ መሆን ይችላሉ፡፡

    በርግጥም መጽሐፍ ቅዱስ ምንም እንኳ መጋቢዎች ባይሆኑም የእግዚአብሔር አገልጋዮች በሆኑ ሰዎች ታሪክ የተሞላ ነው፡፡ እግዚአብሔር የእርሱ አገልጋዮች እንዲሆኑ ጠራቸው እንደዚያም ነበሩ፡፡ ከነዚህ ሰዎች ጥቂቶቹ ነገስታት፣ ፖለቲከኞች፣ ነጋዴዎች፣ ሚሲዮነዊያን፣ ገበሬዎች እንዲሁም አይሁዳውያን ያልሆኑ ይገኙበታል፡፡

    ከካህናት እና ከወንጌላውያን ውጪ የሆኑትም የእግዚአብሔር አገልጋዮች ናቸው የሚለው ሃሳብ ታላቅ አንድምታ አለው፡፡ ይህ ማለት አንተም የእግዚአብሔር አገልጋይ መሆን ትችላለህ ማለት ነው! ባንክ ሰራተኛ፣ የህግ ባለሙያ፣ ዶክተር፣ ፖለቲከኛ፣ ፋርማሲስት እና ግብር ሰብሳቢ የእግዚአብሔር አገልጋይ መሆን ይችላል፡፡

    የእግዚአብሔር አገልጋይ ለመሆን የግድ የሙሉ ጊዜ አገልጋይ መሆን የለብህም፡፡ በማንኛው የገሃዱ ዓለም የስራ መስክ ተሰማርተህ የእግዚአብሔር አገልጋይ መሆነ ትችላለህ፡፡ የእግዚአብሔር ህዝብ ሁሉ የእርሱ አገልጋዮች እንደሆኑ ልብ ማለት ያስፈልጋል፡፡

    አገልጋይ የሌላውን ሰው መሻት የሚፈጽም ማለት ነው፡፡ አገልጋይ የሌላውን ፍላጎት የሚያገለግል ነው፡፡ ዛሬ እና ከዚህ ጀምሮ ራስህን የእግዚአብሔር አገልጋይ አድርገህ ቁጠር፡፡ ተማሪ የእግዚአብሔር አገልጋይ መሆን ይችላል!  ነጋዴም የእግዚአብሔር አገልጋይ መሆን ይችላል! አስተማሪ አገልጋይ መሆን ይችላል! የስራህ ሙያ ምንም አይነት ቢሆን የሁሉን ቻዩን አምላክ ፈቃድ መፈጸም ትችላለህ፡፡ በህይወትህ ታላቅ ስራ ሰራህ የሚባለው የእግዚአብሔር አገልጋይ ስትሆን ነው፡፡

    ካህናት፣ ሌዋውያን እና ነቢየት የእግዚአብሔር አገልጋዮች ተብለው መጠራታቸው የሚያስገርም ነገር አይደለም፡፡ አብርሃም፣ ይስሃቅ እና ያዕቆብ መጋቢዎች አልነበሩም እግዚአብሔር ግን የእርሱ አገልጋዮች እንደሆኑ ጠቅሷቸዋል፡፡ አብርሃምን እንደ መጋቢ አድርጋችሁ ማየት እንደምትፈልጉ አውቃለሁ፡፡ አብርሃም ግን መጋቢ አልነበረም፡፡ የእግዚአብሔር አገልጋይ ብቻ ነበር፡፡ ሙሴንም እንዲሁ መጋቢ አድርጋችሁ መቁጠር ትፈልጋላችሁ፡፡ ሙሴ ግን የእስራኤል መራሔ መንግስት ነበር፡፡ እግዚአብሔር ዳዊትን አገልጋዩ እንደሆነ ጠቅሶታል፡፡ በርግጥም ሁለቱም ማለትም ሙሴ እና ዳዊት ቀደምት የእስራእል መራሔ መንግስት ማለትም ከቤን ጉሪየን፣ ከሺሞን ፔሬዝ፣ ከይስሃቅ ራቢን፣ ከኤሁድ ባራክ፣ ከኤሪየል ሻሮን እና ከቤንያሚን ናታንያሁ በፊት የነበሩ ናቸው፡፡ መራሔ መንግስት መጋቢ አይደለም፡፡ መራሔ መንግስት ግን የእግዚአብሔር አገልጋይ መሆን ይችላል፡፡ ሁለቱም ማለትም ዳዊት እና ሙሴ ድንቅ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ነበሩ፡፡ ምንም አይነት ስፍራ ላይ ብትሆን የእግዚአብሔር አገልጋይ እንደሆንክ ልብ በል፡፡

    ኢዮብ በምስራቅ ካሉት ነጋዴዎች ታላቅ ነበር፡፡ ኢዮብ ከምስራቅ ስለነበር ምናልባትም ቻይናዊ፣ ኮሪያዊ ወይንም ጃፓናዊ ሊሆን ይችላል፡፡ ኢዮብ ባላጸጋ የነበረ ቢሆንም እንኳ የእግዚአብሔር አገልጋይ ተብሏል፡፡ እግዚአብሔር እንኳ በኢዮብ እንደሚተማመንበት ለዲያብሎስ አስታውቆታል፡፡ ዛሬ ዛሬ ባለጸጋ ነጋዴዎች ጌታን ለማገልገል እጅግ ይቸገራሉ፡፡ ነጋዴ ከሆንክ እንደ ኢዮብ የእግዚአብሔር አገልጋይ መሆን ትችላለህ፡፡ ይህ መጽሐፍም የተጻፈው የእግዚአብሔር አገልጋይ መሆን እንድትችል ነው፡፡ እግዚአብሔር የእርሱ አገልጋይ እንድትሆን ይሻል፡፡ እኔም የእግዚአብሔር አገልጋይ እንድትሆን እመክርሃለሁ፡፡ የእግዚአብሔር አገልጋይ መሆን በርካታ ጥቅማ ጥቅሞች አሉት፡፡ ይህም መጽሐፍ የሚያወሳው ስለዚያ ነው! የእግዚአብሔር አገልጋይ ለመሆን ወስን፡፡ ከእግዚአብሔር አገልጋዮች እንደ አንዱ ለመጠራት ወስን፡፡ ሰማይ እንደ እግዚአብሔር አገልጋይ ይቀበልህ፣ ያክብርህም፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ተደርገው የተጠሩትን ሰዎች ዝርዝር እንመልከት፡፡

    1. ካህናት እና ሌዋውያን የእግዚአብሔር አገልጋዮች ናቸው

    እነሆም፥ ለእግዚአብሔር ቤት አገልግሎት ሁሉ የሚሆኑ የካህናትና የሌዋውያን ክፍሎች በዚህ አሉ ለሁሉም ዓይነት አገልግሎትና ሥር በብልሃትና በነፍሱ ፈቃድ የሚሠራ ሁሉ ከአንተ ጋር ይሆናል አለቆችና ሕዝቡም ሁሉ ፈጽመው ይታዘዙሃል አለው። 1ኛ ዜና 28፡21

    2. ነቢያት የእግዚአብሔር አገልጋዮች ናቸው

    የባሪያዎቼን የነቢያትን ደም፥ የእግዚአብሔርንም ባሪያዎች ሁሉ ደም ከኤልዛቤል እጅ እበቀል ዘንድ የጌታህን የአክዓብን ቤት ትመታለህ።     2ኛ ነገስት 9፡7

    ለባሪያዎቼስ ለነቢያት ያዘዝኋቸው ቃሎቼና ሥርዓቴ በአባቶቻችሁ ላይ አልደረሱምን? እነርሱም ተመልሰው። የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በመንገዳችንና

    Enjoying the preview?
    Page 1 of 1