You are on page 1of 35

የሰው ኃይል አስተዳደርና ልማት እቅድ

የ1ኛ ሩብ የ2ኛ ሩብ ዓመት የ3ኛ ሩብ


ተ. ዝርዝር ተግባራት ፈፃሚ ዓመት ዓመት
ቁ አካል ሐም ነሐሴ መስከረ ጥቅምት ህዳር ታህሳ ጥ የካቲ መጋ
ሌ ም ስ ር ት ት
1 የወጡና የሚወጡ        
መመሪያዎችን ሰራተኛው
ግንዛቤ እንዲያገኝ ማድረግ
2 ሰራተኛው የሚገቡትን        
ጥቅማጥቅሞች
ከሚመለከተው ጋር በመነጋገር
ተጠቃሚ እንዲሆን ማድረግ
3 በአመት ሁለት ግዜ የሰራተኛው  
ኢፈሸንሲ በየክፍሉ ግምገማ
እንዲደረግና ግምገማውንም
ለሚመለከተው አካል ሪፖርት
ማድረግ
4 በስራ ውጤታቸው ጠንካራ  
የሆኑ ሰራተኞች የሃላፊነት
ምልመላ በሚደረግበት ወቅት
ህጉና ደንቡ ተከትሎ ተግባራዊ
እንዲሆን ማድረግና
ምልመላውን ለዋናው ቢሮ
መላክ
5 ሰራተኛው በስራ ወቅት ጉዳት        
እንዳይደርስበት ግንዛቤ
መፍጠርና ሴፍቲ እቃዎችን
እንዲጠቀም ማድረግ
6 ከሰራተኛው የሚነሱ የመብት        
ጥያቄዎችን ከህግና ከደንብ
አንጣር ምላሽ እንዲሰጥ
ማድረግ
7 የኮንትራት ሰራተኞችን ውል  
እድሳት ማድረግ
8 የግዚያዊ(የቀን ሰራተኞች) ውል  
እድሳት ማድረግ
9 የአዲስ ሰራተኞች ቅፅር      
ሲፈፀም ህጉና ደንቡ ተጠብቆ
እንዲፈፀሙ ማድረግ
10 የካምፕ ምግብናው ፕሮግራም        
በአግባቡ እንዲመራ
መቆጣጠር
11 ዲሞክራሳዊ የስራ አካባቢ        
እንዲኖር ማድረግ
12 የዲሲፒሊን ጉዳይ ችግር       
ሲፈጠር መመሪያው
በሚያዘው መሰረት እንዲፈቱ
ማድርግ
14 የሰራተኛው መኖሪያ አካባቢና        
የግል ንፅህና እንዲጠብቅ
ቁጥጥር ማድረግ
15 የካንፑ መተዳደሪያ ደንብ        
ተፈፃሚ እንዲሆን ክትትል
ማድረግ
16 ቅድመ መከላከል ላይ ያተኮረ        
የበሽታ መከላክል ስራዎችን
መስራት
17 ፕሮጀክቱ ላይ ክሊኒክ        
እንዲከፈት ሁኔታዎችን
ማመቻቸት
18 የሰራተኛ ዳታ በአግባቡ        
እንዲያዝ ሪከርድና ማሀደር
ክፍሉን ማጠናከር
20 ሰራተኛው ለታለቁ ህዳሴ ግድብ 
የሚውል ቦንድ እንዲገዛ
ማድረግ
21 በፕሮጀክቱ ያሉ ክፍሎች        
የሚያስፈልጋቸውን የሰው
ሀይል እዲሟላ ማድረግ
22 ሰራተኞች በሰዓት ገብተው        
በሰዓት እንዲወጡ የቁጥጥር
ስራዓት መዘርጋት
23 በየወሩ ፔሮል በማዘጋጀት        
ለፋይናንስ ማቅረብ
አቅም ግንባታን በተመለከተ
1 የአቅም ውስንነት ያለባቸው        
ሰራተኞች በመለየት ስልጠና
እንዲያገኙ ማድረግ
2 የስራ ላይ ስልጠና ሰራተኛው
እንዲያገኝ ማድረግ
3 የአመራር ስልጠና አመራሮች
እንዲወስዱ ሁኔታዎችን
ማመቻቸት
4 የሴቶች አቅም ማጎልበት
ከሚመለክትው አካል ጋር
በመሆን መስራት

የፋይናንስ አስተዳደር እቅድ


የ1ኛ ሩብ የ2ኛ ሩብ ዓመት የ3ኛ ሩብ ዓመት
ተ. ዝርዝር ተግባራት ፈፃሚ ዓመት
ቁ አካል ሐም ነሐሴ መስከ ጥቅ ህዳር ታህሳ ጥር የካቲ መጋቢ
ሌ ረም ምት ስ ት ት
1 ከሎጀስቲክ ጋር በመተባበር         
የንብረት ምዝገባ ማድረግ
2 ወርሃዊ በጀትና ሌሎችም         
ክፍያዎች ከዋናው ቢሮ
እንዲላክ መጠየቅ
3 ተጠይቀው የሚጡ ክፍያዎችን         
መመሪያው በሚያዘው
መሰረት ክፍያ መፈፀመ
4 በግዢ መመሪያው መሰረት         
ለሚከናወኑ ግዥዎች ክፍያ
መፈፀም እና በህጉ መሰረት
የሂሳብ ማጠቃለያ ሪፖርት
መስራት
5 ደሞዝ፡ ስራ ማስኬጅ እና         
ሌሎች ተያያዥነት ያላቸው
ክፍያዎች መፈፀም
6 አጠቃላይ የፕሮጀክቱን ገቢና         
ወጪ መስራት
7 ከሰራተኞች የሚሰበሰብ         
ግብርን ለሚመለከተው አካል
በግዜው ገቢ ማድረግ
8 ወርሃዊ የሂሳብ ሪፖርት         
ለዋናው መስሪያ ቤት መላክ
9 የፕሮጀክቱን አጠቃላይ ወጪ         
ምዝገባ ማካሄድ
10 ወርሃዊ ሂሳብ ማስታረቅ ስራ         
መስራት
11 የሚገቡና የሚወጡ ንረቶች         
አስቶክ ኮነትሮል መስራት
12 የፕሮጀክቱን የሂሳብ         
እንቅስቃሴ እለት ከእለት
መመዝገብና መቆጣጠር
14 ግዢዎች የመንግስትን የግዢ         
ስራዓት ተከትለው እንዲገዙ
ማድረግ
15 ክፍያዎች ከመፈፀማቸው         
በፊት ለክፍያ የሚያበቁ ሰነዶች
መሟላታቸውን ማረጋገፅ
16 የእለት ከእለት ካሽፍሎ         
መከታተል(ፍሰቱን) መቆጣጠር
17 የፕሮጀክቱን አጠቃላይ ሃብት         
መዝግቦ መያዝ
18 ከሰራተኛው የተሰበሰበውን         
ጡረታ ወደ ዋናው ቢሮ ሪፖርት
መላክ
20 ባንክ ውሰጥ የሚገኘውን   
የጡረታ ብር በየ 3 ወር በባንክ
ማስተላለፍ
21
22
23

1
2
3
4

መግቢያ
አንደሚታወቀው ጥቅምት 6 በየአመቱ የሰንደቅ አላማ ቀን እንደሚከበር የሚታወቅ ነው፡፡ በዚህም
መሰረት ለ10ኛ ግዜ የሚከበረውን የሰንደቅ ኣላማ ቀን ”ራይ ሰንቀናል ለላቀ ድል ተነስተናል” በሚል
መሪ ቃል የሚከበረውን በዓል በሲዳሃ ፋጌ እን/ሃይ/ማ/ፕሮጀክቱ የሚገኙ አባላቶች እለቱን በደመቀ
ሁኔታ አክብረውት ውለዋል፡፡ ለባዓሉ ማድመቂያ የሚሆኑ ሰንደቅ አላማ ከአካባቢው በመግዛት
ሰንደቃችን ከፍ ብሎ እንዲወለበለብ ማድረግ ተችላል፡፡

የነበረው የበዓሉ አከባበር ፕሮግራም


 የውይይቱ ቦታ፡-ሲዳሃ ፋጌ እንፋሎት ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት
 አጠቃላይ በበዓሉ አከባበር ላይ የተሳተፈው የሰው ሃይል ብዛት 26
 በፕሮጀክቱ ስራ አስኪያጅ በዓሉን አስመልክቶ የመክፈቻ ንግግር ማድረግ
 የመወያያ ፁሁፍን በንባብ ማሰማትና እንዲወያዩበት ማድረግ
 በዓሉን አስመልክቶ የተዘጋጀውን ጥያቄና መልስ ማካሄድ
 ለአሸናፈ ተወዳዳሪዎች የሽልማት አሰጣጥ ስነስርዓትና የመዝጊያ ንግግር
የእለቱን ፕሮግራም እስመልከቶ የፕሮጀክቱ ስራ አስኪያጅ ለ10ኛ ግዜ እየተከበረ ያለውን
የሰንደቅ ዓላማ ቀን አስመልክቶ ሰፋ ያለ ማብራሪያ በማድረግ ስለ ሰንደቅ ዓላማ ታሪክና
አመጣጡ በተመለከተ በተዘጋጀው ፅሁፍ ላይ በሰፊው የተገለፅ ስለሆነ ከፅሁፉ ላይ እናገኘዋለን
በማለት የተዘጋጀውን መወያያ ጥሩ አንባቢ በመምረጥ ለቤቱ እንዲነበብ ተደርጋል ፡፡
ሰብሳቢው በተነበበው መወያያ ላይ ግልፅ ያልሆነ ነገር ካለ በማለት ለቤቱ ጥያቄ ያቀረቡ
ቢሆንም የቀረበው ግልፅ መሆኑን ቤቱ በመግልፀው ወደ አስተያየት ብንሄድ የተሸለ ነው የሚል
ሃሳብ ከቤቱ የተነሳ በመሆኑ በዚህም መሰረት ከቤቱ የተሰጡት አስተያየት እንደሚከተለው
ይቀርባል፡-

1ኛ/ በፅሁፍ ላይ እንደተነበበልን ስንደቅ ዓላማችን አባቶቻችን ከፍተኛ የሆነ ተጋድሎ አድረገው
ሉዓላዊነታ የተከበረች አገር አስረከበውናል በዚህም መሰረት እኛም ለቀጣይ ለተውልድ
ተመሳሳይ ነገር ማድረግ ይገባናል
2ኛ/ መከላከያ ሰራዊታችን በአለም አቀፍ የሰላም ማስከበር ተግባር ላይ እፈፀመ ያለውን ስራ
ከፍተኛ መሆኑ ግልፅ ነው ፡፡ በዚህም ተግባሩ ባንድራችን ከፍ ብሎ ሲውለበለብ ማየት ከፍተኛ
የሆነ ኩራት ይሰማናል
3ኛ/ መሪዎቻችን በአለም አቀፍ መድረክ ላይ ለመመረፀጥ መብቃታቸው አገራችን
እየተከተለች ያለውን ፖሊሲ ማሳያ ነው በዚህም ታላቅ ኩራት ይሰማናል
4ኛ/ ሰንደቅ አላማችን የያዘው መልዕክት የህዝቦች፤የሀይማኖቶች እኩልነት የሚገልፅበት
በመሆኑ ሁላችንም ይህን በዓል ስናክብር ታላቅ ኩራት ይሰማናል
5ኛ/ የሰንደቅ አላማ ቀንን ስናከብር ሁላችንም ልናስባቸው የሚገቡ ጉዳዮች አሉ እነሱም ይህን
ታሪከ ላቆዩለን የታሪከ አባቶች ትለቅ ኩራት ይሰማናል
6ኛ/ ሰንደቅ አላማችን በተለያየ መድረክ ላይ ከፍ ብሎ ሲውለበለብ ማየት ከምንም በላይ
የሚያስደስት በመሆኑ ሁላችንም በተሰማራንበት የሞያ ዘርፍ ድርሻችንን ተወጥተን የአገራችን
መለያ ከፍ እንዲል እናደርጋለን
7ኛ/ ሁላችንም በዚህ በዓል የታደምን የባንድራውን ትርጉም በውሰጣችን ልናስገባው ይገባል
የሚሉ መሳሰሉትን ሃሳቦች ሰንዝረዋል፡፡ ሌላው የበዓሉ ማድመቂያ የነበረው የጥያቄና መልስ
ውድድር ማካሄድ ነበር በዚህም መሰረት የተዘጋጀውን የጥያቄና መልስ ፕሮግራም 3
ተወዳዳሪዎችን ከአባላቱ በመምረጥ ዳኞችን በመሰየም ለእያንዳነዱ ተወዳዳሪ 5 ጥያቄዎችን
በማቅረብ የዕለቱን ውድድር ማካሄድ ተችላል ለአሸናፊዎችም 1ኛ ለወጣው የ50 ብር 2ኛ
ለወጣው 25 ብር 3ኛ ለወጣው 15 ብር የሞባይ ካርድ ሽልማት ለተወዳዳሪዎች ሽልማት
ተበርክቶላቸዋል፡፡ከዚህ የሽልማት ስነስራዓት ቡኃላ የበዓሉን የመዝጊያ ንግር የፕሮጀክቱ ስራ
አስኪያጅ በማድግ የዕለቱን በዓል ፕሮግራም ፈፅመዋል፡፡

ጥቅምት 6/2010 ዓ.ም


ሲዳሃ ፋጌ እንፋሎት ሃይል ማመንጫ
ፕሮጀክት
1.የስራ መደቡ
1.1 መጠሪያ፡-ፕሮጀክት ሎጀስቲክስ ኃላፊ

1.2 ተጠሪነቱ፡- ለፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ

1.3 የሚገኝበት የስራ ክፍል፡- ሲ/እ/ሃ/ማ/ፕሮ

1.4 የሙያ ዘርፍ፡- የስራ ኃላፊ


2. የስራ መደቡ ዋና ዋና ተግባራት
የፕሮጀክቱን የንብረት ርክክብ፤የአካባቢ ግዢ እንዲሁም የንብረት አስተዳደር ፤

የማቴሪያል፤ፕላኒንግ እና ኢንቨተሪ ማኔጅመንት ስራዎችን ያቅዳል፤ያደራጃል፤ይመራል፤

ይቆጣጠራል፤የግዢ እና የንብረት አስተዳደር ፖሊሲዎችና ፕሮሲጀሮች ስራ ላይ ያውላል፤

የፕሮጀክቱን ንብረት ማከማቻዎችን በበላይነት ይቆጣጠራል፤ዘመናዊ የማቴሪያል ፍላጎት

መወሰኛ ስልቶች መሰረት በማድረግ ኣመታዊ የግዚ ፍላጎቶችን መዘጋጀቱን ይከታተላል ፤

የተቆራረጠ ግዢዎችን ይቆጣጠራል፤ተገቢ የሆነ ክትትል በማድረግ አቅርቦታቸውን

አስተማማኝ መሆኑን ያረጋግጣል፤የፕሮጀክቱን ንብረት ምዝገባና ቁጥጥር(inventory

control) መረጃዎችን ተዓማኒ እና ወቅታዊ መሆናቸውን ያረጋግጣል፤


3. የስራ መደቡ ዝርዝር ተግባራትና ኃላፊነቶች
3.1 የፕሮጀክቱን የግዢና ንብረት አስተዳደር፤ የማቴሪያል ፕላኒንግና ኢንቨተሪ

ማኔጅመንት ስራዎችን ያቅዳል፤ያደራጃል፤ይመራል፤ያስተባብራል፤ይቆጣጠራል፤ ፖሊሲና

3.2 በጨረታ ለሚፈጸሙ የአካባቢ ግዢዎች ተገቢውን የቅድሚያ ዝግጅት መደረጉንና

መረጃዎች በቅድሚያ ተሟልተው መቅረባቸውን፤በአጠቃላይ ጨረታው በድርጅቱ

የግዢ ፖሊስና መመሪያ መሰረት መፈጸሙን ይቆጣጠራል፤

ብኢኮ የሚያወጣቸውን የአካባቢ ግዢና የንብረት አስተዳደር ፖሊሲዎችና ፕሮሲጀሮች

ስራ ላይ ያውላል፤

3.3 ዘመናዊ የማቴሪያል ፍላጎት መወሰኛ ስልቶች መሰረት በማድረግ የግዢ ፍላጎቶችን

ይከታተላል፤ግዢዎች ሳይቆራረጡ ድርጅቱን የጥቅል ግዢ ተጠቃሚ ማድረግ

በሚያስችል ሁኔታ መከናወኑን ይከታተላል፤

3.4 የፕሮጀክቱን የስራ ሂደት የሚያስተጓጉሉ ወሳኝ ጥሬ እቃዎችን በክምችት

መኖራቸውን ተገቢ ክትትል በማድረግ በአግባቡ በክምችት መያዛቸውን ያረጋግጣል፤

3.5 የፕሮጀክቱን የንብረት ምዝገባና ቁጥጥር መረጃዎች ተዓማኒ እና ወቅታዊ

መሆናቸውን ይከታተላል፤

3.6 የፕሮጀክቱ እቃዎች(እሰቶክ) ወጪና ገቢ እንቅስቃሴ በትክክል እየተካሄደ መሆኑን

ይከታተላል፤

3.7 የፕሮጀክቱ ቋሚ ንብረቶች እቅስቃሴ፤አያያዝና ጥገና ይከታተላል፤ወደ አገልግሎት

የሚገቡትን በተዘረጋው የምዝገባ ስራዓት መሆኑን ይታተላል፤

3.8 አገልግሎት የማይሰጡ ንብረቶች በድርጅቱ የንብረት አወጋገድ መመሪያ መሰረት

እንዲወገዱ ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን ይሰራል፤

3.9 በተጨማሪም የቅርብ ኃላፊው የሚሰጠውን ተመሳሳይ ተግባራት ያከናውናል፤


1.የስራ መደቡ

1.1 መጠሪያ፡-ፕሮጀክት አስተዳደርና ሰው ሀይል ልማት ኃላፊ

1.2 ተጠሪነቱ፡- ለፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ

1.3 የሚገኝበት የስራ ክፍል፡- ሲ/እ/ሃ/ማ/ፕሮ

1.4 የሙያ ዘርፍ፡- የስራ ኃላፊ


2. የስራ መደቡ ዋና ዋና ተግባራት

የፕሮጀከቱን የሰው ሃብት ልማትና የሰራተኛ ህክምና ጉዳይ ያቅዳል፤ያደራጃል፤ይመራል፤ያስተባብራል፤

ይቆጣጠራል በሚሰጠው የስልጣን ውከልና መሰረት የዝውውር፤የደረጃ እድገት፤የቅጥር፤የዲሲፒሊን፤

የሰራተኛ ጥቅማ ጥቅም፤የስንብት ሌሎችም የሰው ሃይል አስተዳደር ጉዳዬችን ያስፈፅማል፤የአሰሪና

ሰራተኛ አዋጅና ከዋነው መስሪያ ቤት የሚተላለፉ የሰው ሃብት ስራ አመራር መመሪያዎችን ተፈፃሚ

ያደርጋል፤የፕሮጀክቱን የአስተዳደርና የሰው ኃይል ልማት፤ዕቅድና የስራ ፕሮግራም ያዘጋጃል፤

አፈጻጸሙን ያስተባብራል፤ይቆጣጠራል የፕሮጀክቱን የሪከርድና ማህደር ያደራጃል፤የሰራተኞች

ማህበራዊ መድን ዋስትና የጤና ና መህበራዊ ጉዳዬችን ይከታተላል ያስፈፅማል ፤

3.የስራ መደቡ ዝርዝር ተግባራትና ኃላፊነቶች

3.1 የፕሮጀክቱን የሰራተኛ እስተዳደር፤የሰው ሃብት ልማትና የሰራተኛ ህክምና ስራዎችን

ያቅዳል፤ያደራጃል፤ይመራል፤ያስተባብራል፤የቆጣጠራል፤

3.2 በሚሰጠው የስልጣን ውክልና መሰረት የዝውውር፤የደረጃ እድገት፤የቅጥር፤የዲሲፕሊን፤

የሰራተኛ ጥቅማጥቅም፤የስንብትና ሌሎች የሰው ሃይል ሃይል አስተዳደር ጉዳዬችን

ያስፈፅማል፤

3.3 የፕሮጀክቱን የየአስተዳደርና የሰው ሀይል ልማት፤ዕቅድና የስራ ፕሮግራም ያዘጋጃል፤

አፈጻጸሙን ያስተባብራል፤ይቆጣጠራል፤

3.4 የፕሮጀክቱን የአጭርና የረጅም ግዘ ዕቅዶችን ለማሰፈጸም የሚያስፈልገውን የሰው ሃይል

ዕቅድ ያዘጋጃል፤ሲፈቀድም በድርጅቱ ደንብ መስረት በእድገት፤በቅጥር ወይም

በዝውውር ያሟላል
3.5 የፕሮጀክቱን የሰው ሃይል ፍላጎት የማሟላት ስራዎችን በቅርብ ይመራል፤ያስተባብራል፤

ይቆጣጠራል፤

3.6 የፕሮጀክቱን የሰው ሃይል መረጃ እና የሰራተኞች የግል ማህደር እና ሌሎች ሪከርዶች

በተሟላ ሁኔታ መያዙን ይቆጣጣራል፤ያረጋግጣል፤

3.7 ከሰራተኞች የሚቀርቡ ቅሬታዎችን እና ጥያቄዎችን በመቀበል መርምሮ ከአሰሪና ሰራተኛ

ጉዳይ ከድርጅቱ የሰው ሃብት መተዳደሪያ ደንብን መሰረት በመድረግ ተገቢውን

መልስ ውሳኔ ይሰጣል፤

3.8 በፕሮጀከቱ የሚፈጠሩ የአስተዳደር ችግሮችን በማጥናት የመፍቴሄ ሃሳብ ያቀርባል፤

3.9 የደመወዝ ጭማሪ፤ልዩ ልዩ ጥቅማ ጥቅሞች፤ፍቃዶችና መሰል ጉዳዬች ተሟልተው

በደንባ መመሪያ መሰረት ለሰራተኛው መሰጠታቸውን ያረጋግጣል

3.10 የሰራተኛው የግል ማህደርና ሪከርድ ተሟልተው መገኘታቸውን፤በስነ ስራዓት

መጠበቃቸውን፤እንዲሁም ሰራተኞችን በተመለከተቱ ስታስቲካል መረጃፀመፀዎችን

እንዲጠናከሩ ያደርጋል፤የሰራተኞች የስራ አፈፃፀም ሪፖርት በወቅቱ ተሞልቶ መተላለፉን

ያረጋግጣል፤

3.11 የፕሮጀክቱን ሰራተኞች የሙያ ብቃትና የስራ አፈፃፀም ለማሻሻል የሚያስችል

ስልጠናዎችና የስራ አካባቢ ምቹና ተስማሚ የሚሆንበትን ዘዴ እያጠና ለኃላፊው

ያቀርባል ፤ሲፈቀድለትም በስራ ላይ ያውላል፤

3.12 የስራ ሰዓት እንዲከበር፤የስራ ዲሲፕሊን እንዲሻሻል ያደርጋል፤ከሰራተኞች ለሚቀርቡ

ቅሬታዎች ተገቢውን ውሳኔ ይሰጣል፤ለእያንዳንዱ ሰራተኛ የስራ ዝርዝር

ተዘጋጅቶ መድረሱን ያረጋግጣል፤

3.13 ሰራተኛውና የድርጅቱ ደህንነት የሚጠበቅበት ስራዓት ይቀይሳል፤አደጋ ከመድረሱ

በፊት ለመከላከል የሚያስችሉ ዘዴዎች ተቀይሰው ተግባራዊ መሆናቸውን

ይከታተላል፤የድርጅቱ ሰራተኞች ተገቢውን የህክምና አገልግሎት ማግኘታቸውን

ያረጋግጣል
3.14 የፕሮጀክቱን መዋቅር ማሻሻያ፤የስራ ዝርዝር አዘገጃጀትና ስራና ሰራተኛን ለማገናኘት

ዘመናዊ የማኔጅመንት ሲስተም በድርጅቱ ውስጥ እንዲሰፍን እያጠና ያቀረርባል

ሲፈቀድም በተግባር ላይ ያውላል

3.15 ለስራው አፈፃፀም ሰለአጋጠመው ችግርና ስለተውሰደው የመፍቴሄ እርምጃዎችን

በየግዜው ሪፖርት እያዘጋጀ ያቀ ርባል

3.16 በተጨማሪም የቅርብ ኃላፊው የ፣ሰጠውን ሌሎች ተመሳሳይ ተግባራት ያከናውናል፡፡

1.የስራ መደቡ

1.1 መጠሪያ፡-ፕሮጀክት ፋይናንስ አስተዳደር ኃላፊ

1.2 ተጠሪነቱ፡- ለፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ

1.3 የሚገኝበት የስራ ክፍል፡- ሲ/እ/ሃ/ማ/ፕሮ

1.4 የሙያ ዘርፍ፡- የስራ ኃላፊ


2. የስራ መደቡ ዋና ዋና ተግባራት

የፕሮጀክቱን የጠቅላላ ሂሳብ፤ኮስትና በጀት ስራዎች ያቅዳል ያደራጃል፤ይመራል፤

ያስተባብራል፤ይቆጣጠራል የፕሮጀክቱን የስራ ክፍሎች በማስተባበር የፋይናንስ እቅድና

በጀት ያዘጋጃል፤ገቢና ወጨዎች በዕቅዱ መሰረት መከናወናቸውን ያረጋግጣል፤የፕሮጀክቱን

የፋይናንስ፤ሂሳብ አያያዝ፤የበጀትና ኮስት ትንተናዎችን በአግባቡ መከናወናቸውን


ያረጋግጣል፤የድርጅቱን የፋይናንስ መመሪያዎችና ደንቦች ተግባራዊ መሆናቸውን

ይከታተላል የፕሮጀክቱ ሂሳብ በወቅቱ እንዲዘጋ በማድረግ በኦዲተሮች የስመረምራል

ከኦዲተሮች በተጠቆመው ድክመቶች ላይ የእርምት እርምጃዎች ይወስዳል፤ለአሰራር

አመቺ፤የተጠናከረና ዘመናዊ የሆነ የሂሳብ አያያዝ፤የፋይናንስና ኮስት ትንተና ሲስተሞች

ይዘረጋል የሂሳብ መግለጫ ሪፖርቶችን በየግዜው ያዘጋጃል፤ፋይናንስን በሚመለከት

ለመኔጅመንቱ ምክር ይሰጣል፤

3.የስራ መደቡ ዝርዝር ተግባራትና ኃላፊነቶች

3.1 የፕሮጀክቱን የጠቅላላ ሂሳብና የኮስትና በጀት ስራዎችን ያቅዳል፤ያደራጃል፤ይመራል፤

ያስተባብራል፤ይቆጣጠራል፤

3.2 የፕሮጀክቱን የመካከለኛ የረጅም ጊዜ የፋይናንስ ዕቅድና በጀት ያዘጋጃል፤ሲፈቀድም

ተግባራዊነቱን ይከታተላል፤

3.3 የፕሮጀከቱን የስራ ዘርፎች በማስተባብር የፋይናንስ ዕቅድና በጀት ወጪዎችን ያዘጋጃል፤

ገቢና ወጪዎች በዕቅድ መሰረት መከናወናቸውን ያረጋግጣል፤ይቆጣጠራል፤

3.4 የፕሮጀክቱ የፋይናንስ አስተዳደር ስራዎች የሚከናወኑበትን ስራዐትና መመሪያ ያዘጋጃል፤

ሲፈቀድም ተግባራዊነቱን ይከታተላል፤ይቆጣጠራል፤

3.5 የፕሮጀክቱ የፋይናንስ አስተዳደር ስራዎች የሚከናወኑበትነ ስርዐትና መመሪያው ያዘጋጃል፤

ሲፈቀድም ተግባራዊነቱን ይከታተላል፤

3.6 የፋይናንሽያል በጀት ቁጥጥርና የኮስት ትንተና ያካሂዳል፤እንደአስፈላጊነቱ የማስተካከያ

እርምጃ እንዲወስድ ሃሳብ ያቀርባል፤

3.7 የፕሮጀክቱን ሂሳብ በወቅቱ መዘጋቱንና በኦደተሮች እንዲመረመር ያደርጋል፤

3.8 የፕሮጀከቱን ተሰብሳቢ ሂሳቦች በወቅቱ ገቢ መደረጋቸውን ይከታተላል፤ይቆጣጠራል፤

3.9 ደመወዝና ልዩ ልዩ ክፍያዎች በወቅቱ መዘጋጀታቸውንና መከፈላቸውን ይከታተላል፤

ይቆጣጠራል
3.10 የፕሮጀክቱ ንብረቶች በፋይናንስ ደንብና ስራዓት መሰረት ተመዝግበው መያዛቸውን፤

ይከታተላል

3.11 በስሩ ለሚገኙ ሰራተኞች ስራ ያከፋፍላል፤የስራ ፕሮግራም ያወጣል፤የስራ

አፈፃፀማቸውን ይገመግማል፤አስቸጋሪ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ መፍቴሄ ይስጣል፤የማስተካከያ

እርምጃዎችን ይወስዳል፡

3.12የፕሮጀክቱን የፋይናንስ፤በጀት፤የሂሳብ አያያዝና የኮስት ትንተናዎችን በሂሳብ አሰራር

መርሆችና ደንቦች መሰረት መከናወናቸውን ያረጋግጣል፤ከመንግስት የሚተላለፉ

የፋይናንስ ህጎች፤ደንቦችነ መመሪያዎች በአግባቡ ስራ ላይ መዋላቸውን ይቆጣጠራል፤

አስተማማኝና ለቁጥጥር አመቺ የሆነ የሂሳብ አያያዝ ስረዓት እንዲኖር ያደርጋል፡፡

3.13 የፕሮጀክቱን የካፒታል፤የስራ ማስኬጃና የደመወዝ በጀት ከስራ ሃላፊዎች ጋር በመመካከጀር

ያዘጋጃል፤ሲፈቀድም በአግባቡ ስራ ላይ መዋሉን ይቆጣጠራል፤

3.14 የፕሮጀክቱን የገቢና የወጪ የሂሳብ መግለጫዎችን፤የትርፍና ኪሳራ መግለጫ፤የሂሳብ

ሚዛንና ትንታኔ በየግዜው እያዘጋጀ ያቀርባል፤

3.15 የጥሬ ገንዘብና የባንክ ሁኔታን በየግዜው እየመረመረ የድርጅቱ ገንዘብ እንዲታወቅ ያደርጋል፤

ጉድለት ቢኖር ተገቢውን እርምጃ ይወስዳል፤በሚሰጠውም ስልጣን ውክልና

መሰርት ክፍያዎችን ያፀድቃል፤ቼክ ይፈርማል፤ማንኛውንም ወጪዎች በሰነድ መደገፋቸውን

ያረጋግጣል፤

3.16 በየበጀት ዓመቱ መጨረሻ ለሚደረገው የንብረት ቆጠራ ያስተባብራል፤ይመራል፤የቆጠራውን

አፈፃፀም ይከታተላል ውጤቱን ያሳውቃል

3.17 ስለስራው እንቅስቃሴ፤ስለአጋጠመው ችግሮችና ስለተወሰዱ የመፍቴሄ እርምጃዎች ወቅተዊ

ሪፖረት እያዘጋጀ ለኃላፊው ያቀርባል

3.18 በተጨማሪም የቅርብ ኃላፊው የ፣ሰጠውንሌሎች ተመሳሳይ ተግባራት ያከናውናል


1 .የስራ መደቡ
1.1 መጠሪያ፡-ኮስትና በጀት ሃላፊ

1.2 ተጠሪነቱ፡- ለፕሮጀክት ፋይናንስ አስተዳደር

1.3 የሚገኝበት የስራ ክፍል፡- ሲ/እ/ሃ/ማ/ፕሮ

1.4 የሙያ ዘርፍ፡- የስራ ኃላፊ


2. የስራ መደቡ ዋና ዋና ተግባራት

የፕሮጀክቱን ኮስትና በጀት ስራዎች ያቅዳል፤ያደራጃል፤ይመራል፤ያስተባብራል፤

ይቆጣጠራል፤የፕሮጀክቱን ነጠላና ጠቅላላወጪዎች ለማስላት የሚያስችል የአሰራር ስልት

መቀየስ ሲጸድቅ ተግባራዊ ያደርጋል፤የፕሮጀክቱን የተለያዩ የስራ ክፍሎች በጀት

በማሰባሰብ አጠቃላይ በጀት ያዘጋጃል ሲጸድቅም አፈጻጸሙን መከታተል፤የኮስትና በጀት

ክትል ስራዎችን በተመለከተ መግለጫዎችን በማዘጋጀት ሪፖርት ለኃላፊው ያቀርባል፤

3.የስራ መደቡ ዝርዝር ተግባራትና ኃላፊነቶች

3.1 የፕሮጀክቱን የኮስትና በጀት ስራዎችን ያቅዳል፤ያደራጃል፤ይመራል፤ያስተባብራል፤

ይቆጣጠራል፤
3.2 የፕሮጀክቱን የነጠላና ጠቅላላ ወጪ ለማስላት የሚያስችል የአሰራር ስልት ይቀይሳል፤

የአሰራር ለውጥና ማሻሻል የሚያስልግ ሆኖ ሲገኝ የማሻሻያ ሃሳብ ያቀርባል፤

ሲፈቀድም በተግባር ላይ መዋሉን ይቆጣጠራል፤

3.3 ለኮስትና በጀት ቁጥጥር የሚዘጋጁ ጆርናል ቫውቸሮች በወቅቱ መዘጋጀታቸውንና

ትክክለኛነታቸውን ያረጋግጣል፤ለጠቅላላ ሂሳብ ቡድን እንዲተላለፍ ያደርጋል፤

3.4 በስታንዳርድ ኮስትና በትክክለኛ ዋጋ መካከል የጎላ ልዩነት ከታየ የማስተካከያ እርምጃ

እንዲወሰድ ያቀርባል

3.5 አስፈላጊ የሂሳብ ደንብና የመቆጣጠሪያ ዘዴዎችን በመጠቀም በክፍሉ ውስጥ ያሉ

መዝገቦች በአግባቡ መያዛቸውንና መጠበቃቸውን ያረጋግጣል

3.6 የፕሮጀክቱን ወጪዎች በቀጥትታና በተዘዋዋሪ የዋለውን ማናቸውንም የዕቃ ፍጆታ

በየአርስታቸው የመለያ ቁጥርመያዛቸውንና በስቶክ ካርድመስፈራቸውን ይቆጣጠ

ራል፤ያረጋግጣል

3.7 የበጀት ፎርሞችን በማዘጋጀት የፕሮጀክቱን ልዩ ልየ ክፍሎች የበጀት ጥያቄዎችን

በወቅቱ እንዲያቀርቡ ያደርጋል፤በየክፍሉ የተዘጋጀውን በጀት በወቅቱ እንዲሰበሰብ

በማድረግ አጠቃላይ የፕሮጀክቱን በጀት ዝግጅት ያስተባብራል፤ተጠቃሚ የስራ

ክፍሎች በጠየቁት በጀት መጠን መጠቀማቸውን ያሰተባብራል፤ይቆጣጠራል፤

3.8 አመታዊ ንብረት ቆጠራን በሃላፊነት ይመራል ያስተባብራል፤ሂሳብ በሚዘጋበት

ወቅት ቢን ካርድና አስቶክ ካርደ መታረቃቸውን እየተከታተለ ያረጋግጣል፤

3.9 በጀትና ኮስትን በተመለከተ ዓመታዊ፤ሩብ ዓመታዊና ወርሃዊ ሪፖርት ያቀርባል፤

3.10 የፕሮጀክቱን ቋሚ ንብረቶች ምዝገባ ከነዋጋቸው በጥንቃቄ መከናወኑን

ይከታተላል፤ዓመታዊ የንብረት ቆጠራ መካሄዱን ያረጋግጣል በንብረት ቆጠራ ወቅት

ወቅት አሰፈላገዊን ድጋፍ ያደርጋል፤

3.11 በተጨማሪም የቅረብ ሃላፊው የሚሰጠውን ሌሎች ተመሳሳይ ተግባራት

ያከናናል፡፡
1.የስራ መደቡ
1.1 መጠሪያ፡-ኮስትና በጀት አካውንታንት

1.2ተጠሪነቱ፡- ለኮስትና በጀት ሃላፊ

1.3 የሚገኝበት የስራ ክፍል፡- ሲ/እ/ሃ/ማ/ፕሮ

1.4 የሙያ ዘርፍ፡- ፕሮፍሽናል

2. የስራ መደቡ ዋና ዋና ተግባራት


የፕሮጀክቱን ካፒታል፤የሰው ሃይል ወጪዎችንና የትርፍና ኪሳራ ክንውኖችን ከእቅድ ጋር

በማነጻጸር ማጠቃለያ ሰንጠረዥ አዘጋጅቶ ያቀርባል፤በቀጥታ በወጪ መክፍያ የሚከፈሉ

ማናቸውም ወጪዎችና በክፍያ ቫውቸሮች የሚዘጋጁትን ወጪዎች በኮስት ሴንተሩ ተንትኖ

የሂሳብ መለያ በመስጠት ለጠቅላላ ሂሳብ ያስተላልፋል፡፡

3.የስራ መደቡ ዝርዝር ተግባራትና ኃላፊነቶች

3.1 የካፒታል የሰው ሃይል ወጪዎችንና የትርፍና ኪሳራ ክንውኖችን ከእቅድ ጋር

በማነጻጸር ማጠቃለያ ሰንጠረዥአዘጋጅቶ ያቀርባል፤የደመወዝና የትረፍ ሰዓት

ወጪዎችን በደመወዝ መክፈያ ሊስት መሰረት ቀጥተኛ ያልሆነ ወጪን ለይቶ በሂሳብ

አርዕስትና በየወጭ ማዕከል(ኮስት ሴንተር) ይመዘግባል

3.2 በቀጥታ የወጪ መክፈያ የሚከፈሉ ማናቸው ወጪዎችንና በክፍያ ቫውቸሮች

የሚዘጋጁትን ወጪዎች በኮስት ሴንተሩ ተንትኖ የሂሳብ መለያ በመስጠት

ለጠቅላላ ሂሳብ ያስተላልፋል

3.3 እስቶር ገቢ ለሆኑ እቃዎችና መለዋወጫዎች ዩኒት ኮስት ለማውጣት የሚረዱ

መረጃዎችን አዘጋጅቶ ያቀርባል፤

3.4 የሂሳብ ሰነዶችን ይመዘግባል፤ኮድ ያደርጋል፤

3.5 የስቶክ ካርድ ከማቴሪያል ፕሮግራሚንግ ጋር ያስታርቃል፤የመብለጥና የማነስ

ዝርዝሮችን ያዘጋጃል፤

3.6 የፕሮጀክቱ ቋሚና ተንቀሳቃሽ ንብረቶች የመድህን ዋስትና እንዲገባላቸው

ለማድግ ተፈላጊውን መረጃ በወቅቱ አዘጋጅቶ ያቀርባል፤

3.7 ለፕሮጀክቱ በቀጥታና በተዘዋዋሪ መንገድ የዋለውን ማናቸውንም የእቃ ፍጆታ

በየአርስቱ የመለያ ቁጥር መያዛቸውንና በስቶክ ካርድ መስፈራቸውን

ያረጋግጣል፤

3.8 በየወሩ፤በየሩብ ዓመቱና በየዓመቱ መጨረሻ በጀትና በአፈፃፀም መካከል ያለውን

ልዩነት ያነፃፅራል፤ይተነትናል፤
3.9 ዓመታዊ የንብረት ቆጠራ ላይ ይሳተፋል፤

3.10 የተለያዪ የኮስት መግለጫዎ(ኮስት አስቴትመንት)ያዘጋጃል፤ መዘጋጀታቸውን

ያረጋግጣል

3.15 በየወሩ፤በየሩብ ዓመቱ እና በየአመቱ መጨረሻ ወጪዎችን በየወጪ

አርእስታቸው ሌጀር እየመዘገበ በየኮስቱ ሴንተሩ በማጠቃለል ለሂሳብ መግለጫ ዝግጅት

የሚረዳ መረጃ ያዘጋጃል፤

3.16 በተጨማሪም የቅርብ ሃላፊው የሚሰጠውን ሌሎች ተመሳሳይ ተግባራት

ያከናውናል፡፡
1.የስራ መደቡ

1.1 መጠሪያ፡-ጠቅላላ ሂሳብ ሃላፊ

1.2 ተጠሪነቱ፡- ለፕሮጀክት ፋይናንስ አስተዳደር

1.3 የሚገኝበት የስራ ክፍል፡- ሲ/እ/ሃ/ማ/ፕሮ

1.4 የሙያ ዘርፍ፡- ፕሮፍሽናል

2. የስራ መደቡ ዋና ዋና ተግባራት

የፕሮጀክቱን ጠቅላላ ሂሳብ ስራዎችን ያቅዳል፤ያደራጃል፤ይመራል፤ያስተባብራል፤

ይቀጣጠራል፤የሂሳብ መዛግብቶችና ሰነዶች በአግባቡ መያዛቸውን ያረጋግጣል፤

የሂሳብ አሰራር ደንቦችና መመሪያዎችን መከበራቸውን እየተከታተለ የቆጣጠራል፤ልዩ

ክፍያዎች በደንቡ መሰረት መፈጸማቸውን እየተከታተለ ያረጋግጣል፤ዓመታዊ የሂሳብ

ማጠቃለያ ስራ ይስራል፤የድርጅቱን የሂሳብ ሪፖርቶችን፤መደበኛ የሂሳብ መግለጫዎችን

ያዘጋጃል፡፡

3. የስራ መደቡ ዝርዝር ተግባራትና ኃላፊነቶች

3.1 የፕሮጀክቱን የጠቅላላ ሂሳብ ስራዎችን ያቅዳል፤የደራጃል፤ይመራል፤ያስተባብራል፤

ይቆጣጠራ፤

3.2 የባንክ ክፍያ ቫውቸሮችን በሂሳብ መመሪያ መሰረት በትክክለኛው የውጪ አርእስት

መመዝገባቸውን ኮድ መደረጋቸውን ይከታተላል፤ይቆጣጠራል፤በህጋዊና በበቂ መረጃ

የተወራረዱና የተደገፉ መሆናቸውን ያረጋግጣል፤

3.3 ክፍያ ከመፈጸሙ በፊት የክፍያውን ተገቢነት በማረጋገጥ ለቅረብ ሃላፊው ያቀርባል፤

እንዲሁም ለመንግስት የሚከፈሉ ታክሶችንና ግብሮችን መከፈላቸውን ይከታተላል፤

ይቆጣጠራል፤ደመወዝ በወቅቱና በመመሪያው መሰረት መዘጋጀታቸውንና መከፈሉን

ያረጋግጣል፤
3.4 የፕሮጀክቱን የገንዘብ ሁኔታ በተመለከተ የሂሳብ መግለጫ በየወቅቱ በማዘጋጀት በየወቅቱ

ሃላፊው ያቀርባል፤የገንዘብ ፍሰት(ካሽ ፍሎው) በወቅቱ መዘጋጀቱን ይከታተላል፤

ይቆጣጠራል፤

3.5 ወርሃዊ የባንክ ሂሳብ መግለጫዎች ከመዝገቡ ጋር መመሳከራቸውንና መታረቃቸውን

ያረጋግጣል፤

3.6 በቅድሚያ የተክፈሉ ሂሳቦች በተገቢው ጊዜ መወራረዳቸውን ይከታተላል፤ያረጋግጣል፤

3.7 በገንዘብ ያዞች እጅ ያለ ቀሪ ገንዘብ በየዕለቱ ባንክ ገቢ/ተመላሽ መደረጉን በቅርብ

ይከታተላል፤ባልተጠበቀ ግዜ በዋናና በጥቃቅን ገንዘብ ላይ ድንገተኛ ቆጠራ እንዲካሄድ

ያደርጋል

3.8 የቋሚ ንብረት መዝገብና የእርጅና ቅናሽ በመመሪያው መሰረት መዘጋጀቱን ያረጋግጣል፤

በቆጠራ የሚገኘውን ቋሚ ንብረት መዝገብና በሂሳብ ቋት ላይ ከተመዘገበው መጠን

እኩል መሆኑን ያረጋግጣል፤ልዩነት ሲገኝ እንዲታረቅና ማስተካከያ እንዲደረግበት ያደርጋል

3.9 የጥቃቅን ወጪ ክፍያዎች ሂሳብ ሰራተኛ ሰነዱን በጭ አርእስት ቁጥር በመስጠት በመልክ

በመልኩ ኮድ መደረጉን ይቆጣጠራል፤

3.10 የሂሳብ መመሪያዎችና፤መዛግብቶችና ሰነዶች በትክክል ፋይል ተደርገው በተገቢው ቦታ

መቀመጣቸው ያረጋግጣል፤

3.11 በየዓመቱ መጨረሻ የሚዘጋጀውን የሚዘጋጀው የፕሮጀክቱ ሂሳብ ወጪዎችን እንዲመረመር

በማድረግ የምርመራ ሂደቱን ተከታትሎ ያስፈጽማል፤

3.12 ለሂሳብ ስራው መሻሻልና አደረጃጀት የሚረዱ አስተያየቶች በማቅረብ ስምምነት ላይ

የተደረሰባቸውን ተግባራዊ ያደርጋል፤

3.13 የጠቅላላ ሂሳብን የስራ እንቅስቃሴ አስመልክቶ የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ያዘጋጃል በስሩ

ለሚገኙ ሰራተኞች የስራ አፈጻጸም ግምገማ በማድረግ ሪፖርት ያዘጋጃል፤

3.13 በስሩ ያሉ ሰራተኞች በስራ ሂደት በሚያጋጥማቸው ችግሮች ላይ በመወያየት የመፍቴሆ

አቅጣጫ በማስቀመጥ ያግዛል የስራ አፈፃፀማቸው ይገመግማል፤


3.14 በተጨማሪም የቅርብ ሃላፊው የሚሰጠውን ሌሎች ተመሳሳይ ተግባራት ያከናውናል፡፡

1.የስራ መደቡ

1.1 መጠሪያ፡- ሲኒየር አካውንታንት

1.2 ተጠሪነቱ፡- ለጠቅላላ ሂሳብ

1.3 የሚገኝበት የስራ ክፍል፡- ሲ/እ/ሃ/ማ/ፕሮ

1.4 የሙያ ዘርፍ፡- ፕሮፍሽናል

2. የስራ መደቡ ዋና ዋና ተግባራት


የተዘጋጁ የሂሳብ ስራዎችን፤የደመወዝ መክፈያ (payroll) ዝግጅትንና የሌሎች የሂሳብ ስሌቶች

ትክክለኛነት በመመርመር ያረጋግጣል፤በኮምፒተር የሂሳብ ስራዎችን ያከናውናል::

የፋይናንስ መግለጫዎችንና ሪሪፖርቶችን ያዘጋጃል፤ልየ ልዩ የፋይናንስ ትንተና ስራዎችን

ያከናውናል፤ሌሎችም የሂሳብ ሰራተኞች ያከናወኗቸውን ስራዎች በመርመር ያረጋግጣል፤

3. የስራ መደቡ ዝርዝር ተግባራትና ኃላፊነቶች

3.1 በየዕለቱ በሂሳብ ሰራተኞች የተዘጋጀውን የሂሳብ ዝርዝር፤ የኮዲንግ፤የማጠቃለያዎችን

መሟላትና የትንተናዎችን ትክክለኛነት ያረጋግጣል፤

3.2 ከስራ ክፍሉ ወደ ሌሎች መላክ የሚገባቸውን የሂሳብ ሰነዶች በወቅቱ ይልካል፤ወደ ስራ ክፍሉ

ወደ ሌሎች መላክ የሚገባቸውን የሂሳብ ሰነዶች በወቅቱ ይልካል፤ወደ ስራ

ክፍሉ መምጣት የሚገባቸውን ይከታተላል፤

3.3 የደመወዝ ሊስት ከተዘጋጀ በኋለ ከደመወዝ መቀነስ የሚገባቸውን የስራ ግብር፤የጡረታ

መዋጮ፤በድር፤ወዘተ.በትክክል መቀነሳቸውንና በአጠቃላይ ክፍያ ትክክል መሆኑን

ይመራል፤ያረጋግጣል፤

3.4 የፋይናንስ የኮምፒዩተር ሲስተም በተሳካ ሁኔታ እየሰራ መሆኑን ይከታተላል፤የኮምፒዩተር

መረጃዎችን በመጠባበቂያ መሳሪያዎችን (backups) ይይዛል፤

3.5 የክፍያ ጥያቄዎች በውል መሰረት መሆናቸውንና አስፈላጊ የክፍያ ደጋፊ ሰነዶች ()

መያያዛቸውንና የክፍያ ጥያቄዎችን ትክክለኛነት ይመረምራል፤ያረጋግጣል፤

3.6 ለመንግስት የሚከፈሉ ሂሳቦችን በተቀመጠው ጊዜ አዘጋጅቶ ያቀርባል፤መከፈሉን ይከታተላል፤

3.7 በደረሰኝ የሚሰበሰብ ገንዘብ ደረሰኙ ተከታታይ መሆኑንና በተሰበሰበ ማግስት ተጠቃሎ ባንክ

መግባቱን አግባብነት ያላቸውን ሰነዶች በመመርመር ያረጋግጣል፤

3.8 የባንክ ኢንቮይሶች በወቅቱ እንዲመዘገቡ ያደርጋል፤ተመላሽ ቼክ፤ሌሎችም ያልተጣሩ ገቢዎች

ወይም ወጪዎች ካሉ ወቅታዊ ማጣራት አካሂዶ ለቅርብ ሃላፊው ያቀርባል፤


3.9 በኮምፒተር ፕሮግራሞች አሰፈላጊውን መረጃ () ያስገባል፤የሂሳብ ትንተና ይሰራል፤ሪፖርቶችን

ያዘጋጃል፤

3.10 የቆዩ ተስብሳቢና ተከፋይ ሂሳቦችን እያጣራ ለውሳኔ ያቀርባል፤

3.11 በቅድሚያ የሚከፈሉ ሂሳቦች በተገቢው ጊዜ መወራረዳቸውን ይከታተላል፤ያረጋግጣል፤

3.12 የቋሚ ንብረት መዝገብና የእርጅና ቅናሽ በመመሪያው መሰረት ያዘጋጃል፤በቆጠራ የሚገኘው

በቋሚ ንብረት መዝገብና በሂሳብ ቋት ላይ ከተመዘገበው ጋር እኩል መሆኑን ያረጋ

ግጣል፤ልዩነት ሲገኝ ልዩነቱን ያስታርቃል፤

3.13 የፕሮጀክቱን የስራ አፈፃፀምና የፋይናንስ አቋም እንዲሁም ሌሎች መግለጫዎች () ከሌሎች

የዘርፍ ባለሞያዎች ጋር በመተባበር እያዘጋጀ ያቀርባል፤በሚሰጠው መመሪያ መሰረ

ት እንደ አስፈላጊነቱ ማስተካከያዎችን ያደርጋል፤

3.14 ሌሎች የስራ ክፍሉ የሂሳብ ሰራተኞች በተለያዪ ምክናያቶች በስራ ቦታቸው በማይገኙበት

ወቅት የእነሱን ስራ ሸፍኖ ይሰራል፤

3.15 ወርሃዊ የባንክ ሂሳብ መግለጫዎችን ከድርጅቱ የሂሳብ መዝገብ ጋር በማመሳከርና

በማስታረቅ ሪፖርቱን ለሃላፊው ያቀርባል፤

3.16 የውስጥና የውጭ ኦዲተሮች ለሚያድርጉት የሂሳብ ምርመራ አስፈላጊው መረጃ መቅረቡን

ይከታተላል፤መዛግብቱን ያስመረምራል፤

3.17 ልዩ ልዩ የፋይናንስ ትንተና ስራዎች ላይ ሙያዊ ድጋፍ ይሰጣል፤

3.18 በተጨማሪም የቅርብ ኃላፊው የሚሰጠውን ሌሎች ተመሳሳይ ተግባራት ያከናውናል፤


1.የስራ መደቡ

1.1 መጠሪያ፡- የእቅድ ዝግጅትና ግምገማ ባለሞያ

1.2 ተጠሪነቱ፡- ለፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ

1.3 የሚገኝበት የስራ ክፍል፡- ሲ/እ/ሃ/ማ/ፕሮ

1.4 የሙያ ዘርፍ፡- ፕሮፍሽናል

2. የስራ መደቡ ዋና ዋና ተግባራት

የፕሮጀክቱን የአጭርና የረጅምና የመካከለኛ ጊዜ እቅድ ዝግጅት የጥሬ እቃ የሰው ሃይልና ሌሎች

አስፈላጊ፤መረጃዎችን ማጠናከርነ፤መተንተን፤ማጠቃለል፤ፕሮጀክቱን

የሚመለከቱ መረጃዎችን ማሰባሰብ፤መተንተን፤መገምገም፤ወቅታዊ ስራዎችን እቅድና አፈጻጸም

ሪፖርትም ተቀብሎ ያጠናክራል፤

3. የስራ መደቡ ዝርዝር ተግባራትና ኃላፊነቶች

3.1 በሚሰጠው መመሪያ መሰረት የፕሮጀክቱን የኦፕሬሽን እቅድና የአፈጻጸም ፕሮግራም ያዘጋጃል፤

ሲፈቀድም ለየስራ ዘርፎች ያስተላልፋል፤የአፈጻጸም ሪፖርትም ተቀብሎ

ያጠናክራል

3.2 የፕሮጀክቱን የጥሬ እቃ፤የሰው ሃይል፤የመሳሪያና የፋይናንስ አቅረቦትና አጠቃቀም መረጃዎችን

ያሰባስባል፤ለመረጃ ማሰባሰቢያ የሚሆኑ ቅፆችን ያዘጋጃል፤የተሰበሰቡ መረጃዎችን

ይተነትናል፤ያጠናክራል፤ሪፖርት ያቀርባል፤

3.3 የየስራ ክፍሉን የስራ እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት፤ከተያዘው እቅድ ጋር ያነጻጽራል፤ይተነትናል፤

ይገመግማል፤የእቅድና የአፈጻጸምልዩነቶችን ምክናያት በማጥናት የመፍትሄ ሃሳብ

ያቀርባል፤

3.4 የፕሮጀክቱን የአችርና የረዥም ግዜ እቅዶች መረጃ በማሰባሰብ የታቀደው የካፒታል

ኢንቨስትመንት እቅድ ተመጣጣኝ ጠቀሜታ ማስገኘቱንና አዋጭነቱን ይገመግማል


አስተያየት ያቀርባል

3.5 የፕሮጀክቱን ለውስጥና ለውጭ አካላት የሚዘጋጀውን እቅዶችና የአፈጻጸም ሪፖርቶች

በተፈላጊው ጊዜና ጥራት ያዘጋጀል፤ለሚመለከተው አካል እነዲተላለፍ ለሃላፊው ያቀርባል፤

3.6 ለፕሮጀክቱ ስራ በቀጥታና በተዘዋዋሪ መንገድ በስራ ላይ የዋለውን የጥሬ እቃ፤የመሳሪያና የሰው

ሃይል ጊዜና ያስከተለውን ወጪ መረጃ ያሰባስባል፤ይተነትናል፤ቀጥተኛ የሆኑና

የኦቨር ሄድ ወጨዎችን በማመዛዘን የሚጣጠሙበት ሙያዊ አስተያየት ያቀርባል፤

3.7 የፕሮጀክቱን የግዢ፤የሰው ሃየልና ሌሎች ወጪዎችን መረጃ በማሰባሰብና

በመተንተንየፕሮጀክቱን ውጤታማና ኢኮኖሚያዊ የሆነ የሃብት አጠቃቀም ስራዓት

እንዲዘረጋ አስተያየት ያቀርባል፤

3.8 በማንኛውም የፕሮጀክቱ እቅድ አፈፃፀም ግምገማ ላይ ሙያዊ አስተያየት ይሰጣል፤

3.9 የፕሮጀክቱን ልየ ልዩ የስራ ክፈሎች የስራ እቅድና የስራ አፈጻጸም ይከታተላል፤እንደ አስፈላጊነቱ

የፕሮጀክቱን አጠቃላይ የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ያዘጋጃል፤

3.10 በተጨማሪም የቅርብ ሃላፊው የሚሰጠውን ሌሎች ተመሳሳይ ተግባራት ያከናውናል፤


1.የስራ መደቡ

1.1 መጠሪያ፡- የደህንነትና ጥበቃ ሃላፊ

1.2 ተጠሪነቱ፡- ለፕሮጀክቱ ስራ አስኪያጅ

1.3 የሚገኝበት የስራ ክፍል፡- ሲ/እ/ሃ/ማ/ፕሮ

1.4 የሙያ ዘርፍ፡- የስራ ሃላፊ

2. የስራ መደቡ ዋና ዋና ተግባራት

የፕሮጀክቱን ቢሮዎች፤ንብረቶች፤የፋብሪካውን ማሽኖች፤ሰራተኞችና ሃላፊዎችን፤ደህንነት

በመጠበቅ ተግባር ላይ የተሰማሩ የጥበቃ ሰራተኞቹን መቆጣጠር፤እለታዊና ወርሃዊ

የፈረቃ ጥበቃ መርሃ ግብር ማዘጋጀት፤የየእለቱን ፈረቃ መቆጣጠር፤የጥበቃ ሰራተኞች በተገበው

የጥበቃ ክልል መመደባቸውን ማረጋገጥ፤ስለ ድርጅቱ የደህንነት ሁኔታ ወቅታዊ

ሪፖርት ማቅረብ

3. የስራ መደቡ ዝርዝር ተግባራትና ኃላፊነቶች

3.1 የፕሮጀክቱን ቢሮዎች፤መጋዘኖች፤የፋብሪካውን ማሽኖች፤ሰራተኞችንና ሃላፊዎችን በመጠበቅ

ተግባር ላይ የተሰማሩ የጥበቃ ሰራተኞችን የቆጣጠራል፤

3.2 የፈረቃ መሪዎችንና የጥበቃ ሰራተኞችን ስራ ላይ ይመድባል፤የየእለት ሪፖርቶችን በማሰባሰብና

በማጠቃለል ለስራ አስኪያጁ ሪፖርት ያቀርባል፤

3.3 የፕሮጀክቱን አጠቃላይ ንብረቶች ከስርቆትና ከሌሎች ውድመት እንዲጠበቅና ጉዳት

እንዳይደርስባቸው ይከላከላል፤
3.4 የጥበቃ ሰራተኞችና የስራ ሰዓት ሪኮርዶችን ያጣራል፤ያረጋግጣል፤በወጣው የፈረቃ

ፕሮግራምና በተሰጡ መመሪያዎች መሰረት በስራቸው ላይ መገኘታቸውን ይቆጣጠራል፤

ሁሉም የጥበቃ ሰራተኞች በስራ ሰዓት ስነ ስራዓትን ማክበራቸውን ያጣራል፤

3.5 የድርጅቱን እንግዶችና ሰራተኞች መታወቂያ በአግባቡ መፈተሸን፤ያልተፈቀደ የጦር መሳሪያ

የያዙ ሰዎች ወደ ድርጅቱ እንዳይገቡ ተገቢውን ቁጥጥር መደረጉን ይከታተላል፤

3.6 ከስራ ሰዓት በኋላ የቢሮ መብራት መጥፋቱን፤መስኮቶችና ቢሮዎች መቆለፋቸውንና የዉሃ

ቧንቧዎች መዘጋታቸውን ያረጋግጣል፤በፕሮጀክቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ የስራ ላይ

ደህንነት ደንቦች መከበራቸውን ያረጋግጣል፤

3.7 የፕሮጀክቱ የሚንቀሳቀሱና የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች በአግባቡ መጠበቃቸውን ያረጋግጣል፤

3.8 የጥበቃ ሰራተኞች በስራ ሰዓት የደንብ ልብሳቸውን ማድረጋቸውን፤የተሰጣቸውን መሳሪያዎች

በሰርዓት መያዛቸውን ያጣራል፤ያረጋግጣል፤

3.9 ቀሪ በሆኑ ሰራተኞች ምትክ ሌሎች ጥበቃዎችን ይመድባል፤

3.10 የስራ ላይ ደህንነት ደንቦች መከበራቸውንና በስራ ላይ መዋላቸውን ያረጋግጣል፤

3.11 የፕሮጀክቱ ንብረት አለ አግባብ ከድርጅቱ ፍቃድ ውጪ እንዳይወጣ ይቆጣጠራል፤ የኬላ

መውጫ ፈቃድ ይሰጣል፤

3.12 በፕሮጀክቱ ግቢ ውስጥ የሚገኝ ህገ ወጥ የቤት እንሰሳዎችን ይቆጣጠራል፤

3.13 ያለ ፍቃድ ስራ ትቶ የሚወጡ ሰራተቦችን ይከታተላል፤ይቆጣጠራል

3.14 ስለ ስራው አፈፃፀም ሪፖርቶችን ያዘጋጃል

3.15 በተጨማሪም የቅርብ ሃላፊው የሚሰጠውን ሌሎች ተመሳሳይ ተግባራት ያከናውናል፤


1.የስራ መደቡ

1.1 መጠሪያ፡- የንብረት አስተዳደር ሃላፊ

1.2 ተጠሪነቱ፡- ለፕሮጀክቱ ሎጀስቲክስ

1.3 የሚገኝበት የስራ ክፍል፡- ሲ/እ/ሃ/ማ/ፕሮ

1.4 የሙያ ዘርፍ፡- ፕሮፌሽናል

2. የስራ መደቡ ዋና ዋና ተግባራት

የንብረት ክፍሉን ተግባራት ያቅዳል፤ያደራጃል፤ይመራል፤ያስተባብራል፤ይቆጣጠራል፤ለስራ

የሚያስፈልጉ እቃዎችን በወቅቱ እንዲገቡ ይጠይቃል፤ያስገዛል፤ርክክቡን ይቆጣጠራል፤

የስርጭቱን መጠን ይወስናል፤የእቃዎች ርክክብ በአይነት፤በሞዴልና በብዛት ትክክል መሆኑን

ያረጋግጣል፤ገቢና ወጪ የሚሆኑ እቃዎች አስፈላጊውን ፎርማሊቲ ማሟለታቸውን

ያረጋግጣል፤ቋሚና አላቂ እቃዎች ቀልጣፋና ኢኮኖሚያዊ በሆነ መንገድ በተገቢው ቦታ

መቀመጣቸውንና መደርደራቸውን ያረጋግጣል፤የንብረት ክፍሉን አመታዊ የስራ ፕሮግራም

ያዘጋጃል
3. የስራ መደቡ ዝርዝር ተግባራትና ኃላፊነቶች

3.1 የንብረት ክፍሉን ስራ ያቅዳል፤ያደራጃል፤ይመራል፤ያስተባብራል፤ይቆጣጠራል፤

3.2 ለፕሮጀክቱ አገልግሎት ለሚመጡ መሳሪያዎች፤የመለዋወጫ እቃዎችና ሌሎች ቁሳቁሶች

ተገቢው ርክክብ መፈፀሙን፤የርክክብ ሪፖርቶችንና ሰነዶች በወቅቱ በተሟላ ሁኔታ

መዘጋጀታቸውን ይቆጣጠራል፤

3.3 ወጪ የሚደረጉ እቃዎች፤ምርቶችና መሳሪያዎች በወጪ ሰነድ ለጠያቂው ክፍል መደረጋቸውን

ያረጋግጣል፤

3.4 በእቃ ግምጃ ቤት ውስጥ ያሉ መሳሪያዎች፤የመለዋወጫና ሌሎች እቃዎች ክምችትና አያያዝ

አስተማማኝ መሆኑን፤የእሳትና አደጋ መከላከያዎች በአስፈላጊ ቦታዎች

መቀመጣቸውን፤እቃዎቹ ከአቧራከፀሀይና ከዝናብ ከሚደርስ ጉዳት መጠበቃቸውን ያረጋግጣል፤

ይቆጣጠራል

3.5 በሚወጣው ፕሮግራም መሰረት የውስጥ ንብረት ቆጠራ መካሄዱን ይከታተላል፤ለዓመታዊ

ቆጠራም ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ቆጠራው በወቅቱ መካሄዱን ይከታተላል፤

3.6 ንብረት ክፍል ውስጥ የማይፈለጉና እቅስቃሴ የሌላቸው እቃዎችና መሳሪያዎች በአይነታቸው

በመለየት እንዲነሱለት ዝርዝር አቅርቦ ያስወስናል፤

3.7 የንብረት እንቅስቃሴን በተመለከተ ወቅታዊ ሪፖርቶችን እያዘጋጀ ለሃላፊው ያቀርባል

3.8 ቋሚና አላቂ እቃዎች ቀልጣፋና ኢኮኒሚያዊ በሆነ መንገድ በተገቢው መንገድ በተገቢው ቦታ

መቀመጣቸውንና መደርደራቸውን ይከታተላል፤

3.9 አመታዊ ቆጠራ ያስቆጥራል፤በስራ ክፍሉ ይዞታ የንብረት ቆጠራ በሚደረግ ወቅት ለሚከሰተው

መብለጥ እና ማነስ ተገቢ የሆነ ማብራሪያ ያቀርባል

3.10 የግምጃ ቤቱ ደህንነት እንዲጠበቅ ያደርጋል፤የእሳት አደጋ መከላከያዎች በተገቢው ቦታ

እንዲቀመጡ ያደርጋል፤ከስራ ሰዓት ውጭ ግ/ቤቱ መቆሎፉንና መብራቶች

መጥፋታቸውን ይቆጣጠራል፤
3.11 በየእለቱ የተሰራበትን ሰነድ ኮፒ በሰነድ ስርጭት መመሪያ መሰረት ለሚመለከተው በወቅቱ

እንዲደርስ ያደርጋል፤

3.12 የግምጃ ቤቱን እለታዊ፤ሳምታዊ፤ወርሃዊ፤የሩብ አመት፤የመንፈቅ እና አመታዊ እቅድና የስራ

ፕሮግራም ያዘጋጃል፤ለቅርብ ሃላፊውም ያሳውቃል፤

3.13 በተጨማሪም የቅርብ ሃላፊው የሚሰጠውን ሌሎች ተመሳሳይ ተግባራትን ያከናውናል

1.የስራ መደቡ

1.1 መጠሪያ፡- የጥገና ሃላፊ

1.2 ተጠሪነቱ፡- ለፕሮጀክቱ ሎጀስቲክስ

1.3 የሚገኝበት የስራ ክፍል፡- ሲ/እ/ሃ/ማ/ፕሮ

1.4 የሙያ ዘርፍ፡- ፕሮፌሽናል


2. የስራ መደቡ ዋና ዋና ተግባራት

በሚሰጠው አጠቃላይ መመሪያ መሰረት የማአከላዊ ጋራጁን የመሳሪያዎችና እቃዎች ጥገና ስራዎችን

ያቅዳል፤ያደራጃል፤ይመራል፤ያስተባብራል፤ይቆጣጠራል፤ይገመግማል፤የፕሮጀክቱን ማዕከላዊ ጋራዥ

በሃላፊነት ይመራል፤ያስተባብራል፤ይቆጣጠራል፤ይገመግማል፤የድርጅቱን ማዕከላዊ ጋራዥ በሃላፊነት

ይመራል፤የጥገና ስራ ፕሮግራም ያወጣል፤ለጥገና ስራው የሚያስፈልገው የሰው ሃይል መሳሪያዎች

ቁሳቁሶችን መለዋወጫዎችን እንዲሟሉ ያደርጋል፤የጥገናው ስራ በወጣው ፕሮግራም መሰረት

መከናወኑን ይቆጣጠራል፤ያረጋግጣል፤

ለመካኒካልና ለኤሌክተሪካል ጥገና ስራዎች የአሰራር ስልት ይቀየሳል፤ለስራ ላይ ችግሮች መፍትሄ

ይሰጣል፤ለማይገኙ መለዋወጫዎች ንድፍ እንዲዘጋጅና በሞዶፊክ ተሰርቶ ጥቅም ላይ እንዲውል

ያደርጋል፤ስራውን በአግባቡ ስለማከናወኑ በሃላፊው የተወሰነ ቁጥጥር ይደረግበታል፤

3. የስራ መደቡ ዝርዝር ተግባራትና ኃላፊነቶች

3.1 የማዕከላዊ ገራጁን የመሳሪያዎችና እቃዎች ጥገና ስራዎችን ያቅዳል ያደራጃል፤ይመራል፤

ያስተባብራል፤ይቆጣጠራል፤

3.2 የማከላዊ ገራጁን የጥገና ስራ ፕሮግራም ያወጣል፤በሃላፊነት ይመራል፤ያስተባብራል፤

ይቆጣጠራል፤

3.3 በስራ ክፍሉ ውስጥ የተቀናጀ የስራ አመራር ስርዓት እነዲተገበር ያደርጋል፤አፈፃፀሙንም

ይከታተላል፤ይቆጣጠራል፤ይመግማል፤

3.4 የጥገና ፕሮግራም ያወጣል ለጥገና ስራው የሚያስፈልጉ የሰው ሃይልና የመሳሪያዎች

የመለዋወጫና መሰል ቁሳቁሶች እንዲሟሉ ያደርጋል፤የጥገናው ስራ በፕሮግራሙ መሰረት

መከናወኑን ይቆጣጠራል፤

3.5 በስራ ክፍሉ ውስጥ የሚደረጉ ጥገናዎችን በሚፈለገው የጥራት ደረጃ፤መጠንና ወጪ

መሆናቸውን ይከታተላል፤ያረጋግጣል

3.6 በስራ ክፍሉ ውስጥ አስፈላጊውን የአደጋ መከላከያዎች እንዲኖሩ ያደርጋል፤

3.7 በድርጅቱ ደረጃ ለመካኒኮች የሚሰጥ ስልጠናንን ያስከብራል፤ያደራጃል


3.8 በስራ ክፍሉ ውስጥ የመገልገያ መሳሪያዎች አያያዝና አጠቃቀም ላይ ክትትል ያደርጋል

3.9 ከፍተኛ በሆነ የጥገና ስራ ላይ ሰራተኞች ለሚያጋጥማቸው ችግሮች መፍቴሄ ይሰጣል፤ሰርቶ

ያሳያል፤የቴክኒክ ምክር ይሰጣል፤ለጥገና ስራው የሚያስፈልገውን የቴክኖሎጂ ዶክመንት

ያዘጋጃል፤

3.10 የመለዋወጫ ዕቃዎች ገበያ ላይ የማይገኙ መሆኑ ሲረጋገጥ ንድፍ በማውጣት ሞዶፊክ

እንዲሰራና ስራ ላይ እንዲውል ያደርጋል፤

3.11 የመለዋወጫ እቃዎችንና መገልገያ መሳሪያዎችን ፍላጎት እያጠና ዝርዝሩን ለሃላፊው

ያቀርባል፤ሲፈቀድ አፈፃፀሙን ይከታተላል፤የመለዋወጫ እቃዎችንና ቁሳቁሶችን ፍጆታ

ይቆጣጠራል፤

3.12 በስራ ክፍሉ ስለተከናወኑ ስራዎች ስለአጋጠሙ ችግሮችና ስለተወሰዱ የመፍትሄ እርምጃዎች

ወቅታዊ ሪፖርት እያዘጋጀ ለሃላፊው ያቀርባል፤

3.13 በተጨማሪም የቅርብ ሃላፊው የሚሰጠውን ሌሎች ተመሳሳይ ተግባራት ያከናውናል፤


1.የስራ መደቡ

1.1 መጠሪያ፡- የግዢ ሃላፊ

1.2 ተጠሪነቱ፡- ለፕሮጀክቱ ሎጀስቲክስ

1.3 የሚገኝበት የስራ ክፍል፡- ሲ/እ/ሃ/ማ/ፕሮ

1.4 የሙያ ዘርፍ፡- ፕሮፌሽናል

2. የስራ መደቡ ዋና ዋና ተግባራት

በሚሰጠው መመሪያና የስራ ትዕዛዝ መሰረት የፕሮጀክቱን የአከባቢ እቃና የአገልግሎት ግዢ

ስራዎችን ያስፅማል፡፡የፕሮጀክቱን የስራ ዘርፎች የእቃ ፍላጎት መሰረት በማድረግ የእቃ

ግዢ ጥያቄ ያቀርባል፤የግዢ መጠየቂያና ትዕዛዝ ለተዘጋጀላቸው እቃዎች የዕቃ ዋጋ

ማቅረቢያ/ፕሮፎርማ እንዲሰበሰብ ያደርጋል፡፡ እቃዎች በወቅቱ ተገዝተው መቅረባቸውንና ርክክብ

የተፈፀመባቸውን ይከታተላል፡፡

3. የስራ መደቡ ዝርዝር ተግባራትና ኃላፊነቶች

3.1 በሚሰጠው መመሪያና የስራ ትዕዛዝ መሰረት የድርጅቱን የአካባቢ የእቃና የአገልግሎት ግዢ

ስራዎችን ያስፈፅማል፤

3.2 የፕሮጀክቱን የስራ ዘርፎች የእቃ ፍላጎት መሰረት በማድረግ የእቃ ግዢ ጥያቄ ያቀርባል፤የግዢ

መጠየቂያና ትዕዛዝ ለተዘጋጀላቸው እቃዎች የእቃ ዋጋ ማቅረቢያ/ፕሮፎርማ

እንዲሰበሰብ ያደርጋል፤ በመከታተል ያስፈፅማል፡፡

3.3 የእቃና የአገልግሎት ግዢ ክፍያ መፈፀሙን ይከታተላል፤ይቆጣጠራል

3.4 በትዕዛዝ የሚሰሩ/የሚጠገኑ ወይም የሚቀርቡ እቃዎች በወቅቱ እንዲደርሱ በየግዜው

ይከታተላል፤ሂደቱን ሪፖርት ያደርጋል፤

3.5 በሚሰጠው መመሪያ መሰረት ከደንበኞች ጋር የሚደረጉ የግዢ ጉዳዮችን በመከታተል

ያስፈፅማል፡፡ከደንበኞች ለሚቀርቡ ጥያቄዎች ማብራሪያ ይሰጣል፤


3.6 በጨረታ ግዢ ሰነዶችና ማስታወቂያዎች ዝግጅት ላይ ይሳተፋል፤

3.7 የግዢ መረጃዎችን በትክክል እየመዘገበ ይይዛል፤መረጃዎችንና ሰነዶችን በጥንቃቄ ይይዛል፤

3.8 የግዢና የሽያጭ ስራዎችን ክንውን የሚመለከቱ ሪፖርቶችን እያዘጋጀ በወቅቱ ያቀርባል፤

1.የስራ መደቡ

1.1 መጠሪያ፡- የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሞያ

1.2 ተጠሪነቱ፡- ለፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ

1.3 የሚገኝበት የስራ ክፍል፡- ሲ/እ/ሃ/ማ/ፕሮ

1.4 የሙያ ዘርፍ፡- ፕሮፌሽናል

2. የስራ መደቡ ዋና ዋና ተግባራት

በሚሰጠው መመሪያና የስራ ፕሮግራም መሰረት ለማኔጅመንት አገልግሎት የሚረዱ የእቅድ፤

የአገልግሎቶች/የግዢና ክምችት፤የፋይናንስ፤የሰው ሃይልና ሌሎች ተጓዳኝ መረጃዎችን

ያጠናቅራል፤ኮምፒውተር ውስጥ ያስገባል፤ያስተካክላል፤ፕሮግራም ያደርጋል፡፡ለእያንዳነዱ ፕሮግራም

ኮድ ሰጥቶ ሲፈለግ ፕሪነት አውት አድርጎ ለፈላጊው

ክፍል በቅርብ ሃላፊው በኩል እንዲሰጥ ያደርጋል፤ፕሮግራሞችን በየግዜው ከሚከሰት ለውጠች ጋር

ያስተካክላል፡፡የሚሰራባቸውን ኮምፒዩተሮች ይንከባከባል፤አስፈላጊ ጥገናና ሰርቪስ

እንዲደርግላቸው ያደርጋል፡፡ለድርጅቱ የስራ ሃላፊዎችና ሰራተኛዎች የኮመምፒዩተር ስልጠና

እንደየአስፈላጊነቱ ይሰጣል፡፡ ለስራ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችንና ዶክመንቶችን በጥንቃቄ

ይይዛል፤

3. የስራ መደቡ ዝርዝር ተግባራትና ኃላፊነቶች


3.1 ለማኔጅመንት አገልግሎት የሚረዱ የእቅድ የአገልግሎቶች፤የግዢ፤የክምችትና የስርጭት፤

የፋይናንስ፤የሰው ሃይልና የሌሎች ተጓዳኝ መረጃዎችን በማጠናከር በኮምፒዩተር ውስጥ

ያስገባል፤ፕሮግራም ያደርጋል፡፡መረጃዎችን ጠብቆ ሲጠየቅና ሲታዘዝ ይሰጣል፤

3.2 የኮምፒዩተር ኦፕረሽን አገልግሎት ተግባር በአግባቡ እንዲካሄድ ቅድመ ኮምፒዩተር ስልጠና

ይሰጣል፤ኦፕሬሽኑን ይከታተላል፤ይገመግማል፤ይቆጣጠራል፤

3.3 ለእያንዳንዱ ፕሮግራም ኮድ ይሰጣል፡፡መረጃው ሲፈለግ ፕሪነት አውት አድርጎ ይሰጣል፤

3.4 በኮምፒውተር ውስጥ የተጠናከሩና የተያዙ መረጃዎችን በየግዜው ከሚከሰቱ ለውጦች ጋር

ያስተካክላል፤

3.5 የሚሰራባቸውን ኮምፒውተርችንና ሌሎች የድርጅቱ ንብረት የሆኑ ኮምፐውተሮችናንና ተጓዳኝ

መሳሪያዎችን ደህንነት ይንከባከባል፤አስፈላጊ ጥገናና ሰርቪስ እንዲደርግላቸው

ያደርጋል፡፡

3.6 አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ለፕሮጀክቱ የስራ ሃላፊዎችና ሰራተኞች የኮምፒውተር ኦፕሬሽን ስልጠና

ይሰጣል፤

3.7 ለስራው አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችንና ዶክመንቶችን በጥንቃቄ ይይዛል፤

3.8 ፕሮግራሞችን በየግዜው ከሚከሰቱ ለውጦች ጋር ያስተካክላል፤

3.9 የኮምፒውተር ኢንፑትና አውትፑት ፕሪንት አውቶችን ትክክለኛነት ይከታተላል፤ ያረጋግጣል፤

3.10 ለስረው የሚያስፈልገውን ቁሳቁሶችና/ቶነር፤ወረቀት-------ወዘተ/መለዋወጫዎችን እነዲሟሉ

ያደርጋል፤

3.11 የኮምፒውተር ደህንነትና የስራ አካባቢ ንጽህና መጠበቁን ይቆጣጠራል፤

3.12 በኮምፒውተር ቴክኖሎጂ የሚከሰቱ አዳዲስ የአሰራር ለውጦችና እውቀቶችን አእየተከታተለ

ይማራል፤ተግባር ላይም ያውላል፤

3.13 ኮምፒውተር በሚንቀሳቀስበት ወቅት እክል ካጋጠመ ወይም ከቆመ ማኑዋል በመጠቀም

ችግሩን እንዲወገድ ያደርጋል፡፡ከአቅም በላይ


ከሆነ ለሃላፊው ሪፖርት ያደርጋል፤

3.14 በተጨማሪም የቅርብ ሃላፊው የሚሰጠውን ሌሎች ተመሳሳይ ተግባራትን ያከናውናል፤

You might also like