You are on page 1of 26

የገበያ መረጃ አገባብ እና አላላክ ዙሪያ የሶፍትዌር

አጠቃቀም
ንግድ ኢንዱስትሪ ገበያ ልማት ቢሮ የገበያ ዋጋ መረጃ
ለህብረተሰቡ የሚሰጠውን ጠቀሜታ በመገንዘብ የገበያ
ዋጋ መረጃ ዎች በወቅቱና በጥራት ተሰብስበውና
ተደራጅተው ለተጠቃሚው ተደራሽ እንዲሆኑ
ለማድረግ የተለያዩ የመረጃ ማሰባሰቢያ እና ማሰራጫ
ሶፍትዌር ሲስተሞችን በማስለማት ወደ ስራ ተገብቶ
በመስራት ላይ ይገኛል፡፡
የማርኬቲንግ ኢንፎርሜሽን ሲስተም ስርዓት
ሶፍትዌር አጠቃቀም ቅደም ተከተል
• በመጀመሪያ የኢንተርኔት ብራውሰር መክፈት
(Mozilla, chrome) በመቀጠል ከብራውሰሩ የአድራሻ
መመዝገቢ ላይ 10.154.235.16
/mis.amharabotimd/ ብለው በመፃፍ enter tab
በመጫን የሚከተለው ገፅ ይመጣል
በመቀጠል መጠቀሚያ ስም እና የይለፍ ቃል
ከሚለው የተሰጠውን የመጠቀሚያስምና የይለፍ
ቃል በመፃፍ ግባ የሚለውን ኮማንድ በማጫን
የማስገቢያ ፔጅ ይመጣል፡፡
ገቢያና ቀን ሲያስገቡ የሚከተለው ገፅ ይመጣል
• የምርት ዋጋ ማስገቢ የሚለውን ሲጫኑት ቀንና ገቢያ
ፍጠር የሚል ይመጣል፤
• የዞን ስም፤የወረዳ ስም፤የገበያ ስም
• በመቀጠል ቀንና ገቢያ የሚለውን በመጫን
የተሰበሰበበትን ቀንና የገቢ ቦታውን መምረጥ፤
• በመቀጠል አስቀምጥ የሚለውን ሲጫኑ ለማስቀመጥ
መስማማትዎን የሚገልፅ ፔጅ ይመጣል፤
• ተስማማ የሚለውን መጫን ከዚያም
የተሰበሰበበትቀንና የገቢ ቦታ በትክክል ይፈጠራል
• ከዚያም የምድብ አይነት፤ የምርት አይነት፤ የምርት
ምድብ እና የምርት አይነት የሚሉትን በመምረጥ
በአምራች፤ በጅምላና በችርቻሮ የተሰበሰበውን መረጃ
በማስገባት አስቀምጥ የሚለውን ሲጫኑ መስማማትዎ
የሚረጋግጥ ይመጣል
• ከዚያም ተስማማ የሚለውን በመጫን የገቢያ መረጃ
ማስገባት ይጠናቀቃል፡፡
 ጠቅለል ባለ መልኩ የተቀናጀ የግብይት መረጃ
ሰርዓት /IMIS/ተብለው የተለሙትን ሲስተሞች
በሶስት ከፍሎ ማየት ይቻላል
እነርሱም፤
የገበያ ዋጋ መረጃ ማስገቢያና ማሰባሰቢያ
የገበያ ዋጋ መረጃ ማሰራጫ
የምርት ፍላጎት እና አቅርቦት ማስገቢያ /ትስስር
ለማካሄድ የሚረዳ/
የገበያ ዋጋ መረጃ ማስገቢያ እና ማሰባሰቢያ
በዳታ ቤዝ ሲስተም መረጃ ማስገቢያ
ሞባይል አፕሊኬሽን መረጃ ማስገቢያ
 በዳታ ቤዝ ሲስተም መረጃ ማስገቢያ
የገበያ ዋጋ መረጃ ከገበያ በሶስቱም አይነት
(በግብርና፤ በኢንዱስትሪ እና በጽ/መሳሪያ እና የቢሮ
እቃዎች) ከተሰበሰቡ በኋላ ወደ ዳታ ቤዝ ሲስተሙ
ኮምፒተርን በመጠቀም ማስገባት
 አንድሮይድ ሞባይልን በመጠቀም ዳታን ኦን
በማድረግ ማስገባት
የገበያ ዋጋ መረጃ ማሰራጫ
ድረገጽ/ዌብሳይት/www.amharabotimd.gov.et፣
የድምጽ መልዕክት ማስተላለፊያ/IVR 8092/፣
በአጭር የጽሁፍ መልዕክት ማስተላለፍ/SMS 8096/
የጥቆማ መስጫ(8092)፣
ኤል.ኢ.ዴ ማስተላለፊያ ሲስተም/LED system/
የምርት ፍላጎት እና አቅርቦት ማስገቢያ /ትስስር
ለማካሄድ የሚረዳ/
• የምርት አቅርቦት ማስገቢያ ፤ በዚህ ገጽ
አምራቶች፤አግሮ ፕሮሰሰሮች፤ ጅምላ ሻጭ ነጋዲዎች እና
ሌሎችም ምርቶቻቸውን ለመሸት በመፈልጉበት ጊዜ
ወደ ቢሮው በመምጣት በቢሮው በኩል ወይም
በራሳቸው አካውንት ተፈጥሮላቸው ምርቶቻቸው
እንዲገቡላቸው በማድረግ ትስስር መፈጸም እንዲችሉ
ያግዛል፡፡
• በተሳሳይ የምርት ፍላጎትም ማስገቢያ በዚሁ መንገድ
ድርጅቶች/ተቋማት መግዛት የሚፈለረጉትን የምርት
አይነት ፤ መጠን፤ የሚቀርብበትን ቦታ በማስገባትን
ትስስር በመፍጠር ግዝ መፈፀም የሚያስችል ሲስተም
ነው፡፡
 እነዚህን የተለሙ ሶፍትዌር ሲስተሞችን
ስንጠቀም እያጋጠሙ ያሉ ችግሮች በሁለት
መልኩ ይፈረጃሉ፤
በዳታ ቤዝ ሲስተም ዙሪያ ያሉ ችግሮች
በባለሙያው በኩል የሚታዩ ክፍተቶች /ችግሮች/
በሲስተሙ ላይ እያጋጠሙ ያሉ ችግሮች
የመብራት መቆራረጥ/ መብራቱ ጠፍቶ ተመልሶ ሲበራ
ኔትወርኩ ለመምጣት ብዙ ጊዜ መውሰድ/
የዳታ ቤዝ ኔት ወርክ መቆራረጥ
ዳታ ቤዝ ሲስተሙ ይከፍትና ኮኔክት ሳያደርግ በጣም
ብዙ መዞር እና ኮኔክት አለማድረግ፤
በዚህም፤
The connection has time out
Server mis.amharabotimd.gov.et is taking too
long to respond
The site could be temporarily unavailable or
too busy. በማለት ማቆም፤
የቀጠለ---

IVR (8092) አለመስራት (ስልኩ ይጠራል ግን አይነሳም/


ምላሽ አይሰጥም)
SMS (8096) አለመስራት/ምላሽ አለመስጠት፤
Website በፊት የተወሰኑ ምርቶችን በተወሰኑ ከተሞች
በራሱ እየሳበ በመውሰድ ዲስፕለይ ያደርግ ነበር አሁን
ደግሞ ጭራሹን አለመስራት፤
ፎገራ እና ሜጫ(ወረታ እና መራዊ) ላይ የተተከለው LED
አለመስራት፤
በባለሙያዎች በኩል የሚታዩ ክፍተቶች
መረጃው የተሰበሰበበት ቀን እና ወደ ዳታቤዝ
የሚገባባት ቀን ልዩነት መስፋት፤
መረጃው የገባባት ቀን ከተሰበሰበበት ቀን መቅደም፤
አልፎ አልፎ ከአንዳንድ ወረዳዎች የሚመጡ የገበያ ዋጋ
መረጃዎች በትክክል የገበያውን ዋጋ የሚገልፁ
አለመሆን (ትኩረት በመስጠት በአካል ተገኝቶ መረጃአ
ለመሰብስብ፤
መረጃ የሚሰበሰብባቸው ምርቶችን ዋጋ እና
መለኪያዎችን ትኩረት ሰጥቶ መረጃውን
አለመሙላት፤
የቀጠለ----

ኔትወርክ የለም በሚል ሰበብ ተከታትሎ ኔትወርክ ሲመጣ


ጠብቆ መረጃ አለማስገባጥ፤
ተሰብስቦ የሚላከው የገበያ ዋጋ መረጃ የጥራት እና
ወቅታዊነት ችግሮች፤
የዞን ባለሙያዎችም በዳታ ቤዝ ያሉ ችግሮችችን በቅርበት
እየተከታተሉ እንዲስተካከል የማድረግ ውስንነት መኖር፤
ወረዳዎች መረጃ ያላስገቡበትንና ጀምረው የተውበትን
ምክንያት በትክክል ለይቶ በየሳምንቱ አለማሳወቅ፤
የሚታዩ ችግሮችን በምን መልኩ ማስተካከል/መቀነስ ይቻላል???

• በሲስተሙ ላይ እያጋጠሙ ያሉ ችግሮች


የመብራት ጠፍቶ ተመልሶ ሲበራ ኔትወርኩ ኮኔክት
ለማድረግ የሚወስደውን ጊዜ፤የዳታ ቤዝ ኔት ወርክ
መቆራረጥ እና ዳታ ቤዝ ሲስተሙ ከፍቶ ኮኔክት
ለማድረግ ብዙ መዞር እና ኮኔክት አለማድረግን
በተመለከተ፤
ከቢሮው አይሲቲ ባለሙያዎች ጋር ሳይሰለቹ ዘወትር
በመነጋገር እና ችግሩን በማሳየት ሲስተሙን ካለሙት
እና ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ተነጋግረው እንዲፈቱልን
መወያየት፤
የቀጠለ---

IVR (8092)፤ SMS (8096)፤Website እና LEDውን


በተመለከተ፤
 ሁሉም በተገቢው መንገድ ለታለመላቸው ዓለማ እንዲውሉ
ችግሩን ለዳሬክቶሬቱ እና ለዘርፉ ኃላፊ በየሳምንቱ በማሳወቅ
እንዲስተካከል ሁሉም በየደረጃው ጥረት ማድረግ
 መረጃው የገባባት ቀን ከተሰበሰበበት ቀን መቅደምን በተመለከተ
ሲስተሙ እንዲመልሰው ካለሙት ባለሙያዎች ጋር በመነጋገር
መፍትሄ መስጠት፤
የቀጠለ---
በባለሙያዎች በኩል የሚታዩ ክፍተቶች/ችግሮች
መረጃው የተሰበሰበበት ቀን እና ወደ ዳታቤዝ የሚገባባት
ቀን ልዩነት እንዳይሰፋ ለማድረግ መረጃወ ከተሰበሰነ ከ3-4
ቀን ውስጥ ማስገባት እንዳለባቸው ግንዛቤ መፍጠር፤
ከአንዳንድ ወረዳዎች የሚመጡ የገበያ ዋጋ መረጃዎች
ትክክለኛ የገበያውን ዋጋ የሚገልፁ አለመሆን (ትኩረት
በመስጠት በአካል ተገኝቶ መረጃ አለመሰብስብን
በተመለከተ፤
 ወረዳዎችን ለይቶ በመጥቀስ ለዞኑ ጠንከር ያለ ግብረ
መልስ በመስጠት ለቀጣይ እንዳይደገም ክትትል እና ድጋፍ
እንዲያደርጉ ማድረግ
የቀጠለ---
መረጃ የሚሰበሰብባቸውን ምርቶች ዋጋ እና መለኪያዎችን
ትኩረት ሰጥቶ መረጃውን አለመሙላትን በተመለከተ፤
 ወረዳዎች ለሚሰሩት ስራ እና ለሚሞሉት መረጃ ጥንቃቄ
አድርገው እና ትኩረት ሰጥተው እንዲሞሉ ማድረግ
 ዞኖች እየተከታተሉ ችግሩን እንዲያሳዩአቸው እና
እንዲያስተካክሉት በቅርበት በጥንቃቄ የገባውን መረጃ
መከታታል አለባቸው፤
ኔትወርክ የለም በሚል ሰበብ ተከታትሎ ኔትወርክ ሲመጣ ጠብቆ
መረጃ አለማስገባጥ በተመለከተ፤
 ኔት ወርክ ሲወጣ ከወረዳዎች የአይሲቲ ባለሙያዎች ጋር
በቆመበት ቁጥር በመነጋገር ችግሩን ይቶ መፍታት፤ከአቅም በላይ
ከሆነ በየደረጃው ካሉት ባለሙያዎች ጋር በመነጋገር አፋጣኝ
ምላሽ መስጠት፤
የቀጠለ---
የዞን ባለሙያዎችም በዳታ ቤዝ ያሉ ችግሮችችን
በቅርበት እየተከታተሉ እንዲስተካከል የማድረግ
ውስንነትን በተመለከተ፤
ስራዎችን/ወረዳዎችን ተከፋፍለው በሀላፊነት ክትትል
እንዲያደርጉ አቅጣጫ በመስጠት መከታተል፤
ወረዳዎች መረጃ ያላስገቡበትንና ጀምረው የተውበትን
ምክንያት በትክክል ለይቶ በየሳምንቱ አለማሳወቅን
በተመለከተ፤
ተከታታይነት ባለው መልኩ በጽሁፍ እና በስልክ
ጠንከር ያለ በትክክል ድክመታቸውን ሊያሳይ በመችል
መልኩ ግብረ መልስ መስጠት
በአጠቃላይ በሲስተሙ ዙሪያ ያሉ ችግሮችን
ለመፍታት
 ሁሉም በየደረጃው ያለው የሚመለከታቸው አካላት
ችግሩን በማሳየት እንዲስተካኩሉና ስራው
የሚፈለገውን ውጤት እንዲያመጣ ጥረት ማድረግ
አለበት
በባለሙያዎች በኩል ያሉትን ችግሮች ለመፍታት፤
 የባለሙያዎችን የእውቀት እና የክህሎት ክፍተት እየለዩ
የአቅም ማጎልበት ስራ በሰፊው መስራት ይገባል፤
• ይህም የክህሎት ክፍተት የሚሞላው
 የዳታ ቤዝ ስልጠና ላልወሰዱ በቢሮው በኩል ስልጠና
በመስጠት ፤
 ከዚህ ቀደም ስልጠና የሰለጠኑት እና በየወረዳው ያሉ
የአይሲቲ ባለሙያዎች ስልጠና እንዲሰጧቸውና
እንዲያገዟቸው በማድረግ፤
 በመስክ በመገኘት በተግባር እያሳዩ በመደገፍ፤
 ከሚያስገቧቸው እና ከሚልኳቸው ሪፖርቶች በመነሳት ግብረ
መልስ በስልክ እና በጽሁፍ እንዲሁም በሌሎች በተለያየየ
ውይይጦች በመስጠት አቅማቸውን በማጎልበት የተሻለ ስራ
እንዲሰሩ ማድረግ፡፡
አመሰግናለሁ!!!

You might also like